2015-09-23 16:28:00

ቅዱስ አባታችን በኦልጊን ከተማ፦ የኢየሱስ ምህረት ታሪክን ይለውጣል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በኵባ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ ሰባት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ሃቫና ከሚገኘው ከቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ሕንፃ ተነስተው ስምንት ሰዓት ሃቫና ከሚገኘው ከኾሰ ማርቲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የኵባ ሦስተኛ ታላቅ ከተማ ወደ ሆነችው ኦልጊን የዛሬ 100 ዓመት በፊት የኵባ ጠባቂ ቅድስት ተብላ የታወጀችው በ 1612 ዓ.ም በክልሉ አሳ አጥማጆች የተገኘቸው ፍቅርተ ማርያም ዘኮብረ ቅዱስ ትንሽ ሓወልት የተኖርበት በ 1720 ዓ.ም. ወደ የተባረከው የቅዱስ ኢሲደሮ ካቴድራል የሚገኝባት፣ በ 1978 ዓ.ም. የተገነባው ታዋዊው መንበረ ጥበብ የሚገኝባት ከተማ 28 ቁምስናዎች 56 ኣቢያተ ክርስቲያን 23 የሰበካ ካህናት፣ 10 ገዳማውያን ካህናት፣ 48 ደናግል 5 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች አንድ ዲያቆን በብፁዕ ኣቡነ ኤሚሊዮ አራንጉረን ኤትቸቨሪያ ኖላዊነት ወደ ሚመራው ሰበካ በአየር በረራ ተጉዘው በኵባ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 9 ሰዓት ከ 20 ደቂቃ ደርሰው በመኪና ጉዞ  በካሊክስቶ ጋርሲያ ኢኚገዝ ስም ወደ ሚጠራው የአብዮት አደባባይ ደርሰው እዛው በብዙ ሺሕ የሚገመት ሕዝብ እንዲሁም የኩባ ርእሰ ብሔር ራውል ካስትሮ ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ማቴዎስ መለወጥ በምታከብርበት ዕለት የተነበበውን የዕለቱን አንደኛው ምንባብ ከኤፈሶን መልእክት ምዕራፍ 4, ከቁጥር 1-7 ከ ቁጥር 11-13ና ከ ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 9 ከቍጥር 9-13 የተወሰደውን በማስደገፍ፦

የኢየሱስ እይታ ነጻ ያወጣናል

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢየሱስ መታየት፣ የኢየሱስ እይታ እርሱም ኢየሱስ ከሮማውያን ቀረጥ ይቀበል የነበረው በሮማውያን ከሃዲ ተብሎ የሚጠላውን ቀራጩ በቀረጥ መቀበያ ሥፍራ ተቀምጦ የነበረውን ማቴዎስ  “አየው”ና ተከተለኝ አለው፣ ማቴዎስም ተነሥቶ ተከተለው”፣ ታሪክ የሚለወጥ እይታ።

ኢየሱስ አየው። ማቴዎስ ኢየሱስን ለመከተል ያነቃቃውና ሕይወቱን የለወጠው የኢየሱስ ፍቅራዊው እይታ ምንኛ ኃያል መሆኑ ያረጋግጥልናል። የፍቅር ኃይል የተካነ እይታ። ማቴዎስ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ እንዲነሳ ያደረጉት የዚያ ያዩት ዓይነቶች ኃይል የሚያስደንቅ ነው። ከዚህ ቀደም ማንም እንዲህ አድርጎ አይቶት አያውቅም፣ ኢየሱስ በምህረት አይን ተመለከተው፣ ይኽ እይታ ማቴዎስ ልቡን እንዲከፍት አድርጎታል፣ ነጻ ያወጣዋል፣ ይፈውሰዋል፣ ተስፋ ሰጥቶታል፣ አዲስ ሕይወት፣ ልክ እንደ ዘኪዮስ እንደ በርጠለመዎስ እንደ ማርያም መግደላዊት እንደ ጴጥሪሮስ እንደ ታደሉት እይታ። እያንዳንዳችን የታደልነው እይታም ነው። ምንም’ኳ እኛ እይታችን ወደ ጌታ ያማናደርግ ብንሆንም እርሱ ዘወትር ቀድሞ እይታውን በእኛ ላይ ያኖራል።

ኢየሱስ ያንን ለእግዚአብሔር የተገባሁኝ አይደለሁም የሚለውን ይፈልጋል

ፍቅሩ በፊታችን ቀድሞ የሚገኝ ነው። የጌታ እይታ የሚያስፈልገንን ሁሉ ልቆ ይሄዳል፣ የጌታ እይት ከውጫዊው ገጽታ ወዲያ ማለትን የሚያውቅ ነው። ከኃጢአት ከውድቀት ካልተገባሁኝ ነኝ ባይነት ሁነት ተሻግሮ የሚሄድ ማየት ነው። በጌታ መታየት ይኸንን ሁሉ ልቆ የሚሄድ ከማንኛውም ወገን ከሆንበት ቦዳኝ ከማኅበራዊ ደረጃ ማዶ የሚደርስ እይታ ነው።

ከዚህ ሁሉ አጥር ልቆ ያንን ሁላችን ያለንን አልፎ በኃጢአት የሚበከል ቢሆንም ቅሉ በጥልቅ ነፍስ ኅያው የሆነውን የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ክብር የሚያይ እይታ ነው። እርሱ ለእግዚአብሔር ልጅ መሆን የተገባሁኝ አይደለሁኝም የሚሉትን በሌሎች የእግዚአብሔር ልጅ መሆን የተገቡ አይደሉም ተብሎ የሚፈረድባቸውን ሊፈልግ የመጣ ነው። በእርሱ እንታይ ዘንድ እንፍቀድ፣ የእርሱ እይታ ጉዞአችንን ይከተል ዘንድ እንፍቀድ፣ የእርሱ እይታ ደስታና ተስፋ ያመጣልን ዘንድ እንፍቀድ።

ምኅረት ተልእኮና አገልግሎትን ይወልዳል

ከምኅረት በኋላ ተልእኮ። ማቴዎስ ኢየሱስን ተከተለ። ከኢየሱስ ከመኃሪው ፍቅሩ ጋር መገናኘት ይለውጠዋል። ቀረጥ የመቀበያውን ሥፍራና መቀመጫውን ገንዘቡን በሌሎች እንደ ተጠላ ተገሎ መኖሩን ወደ ኋላ እርግፍ አድርጎ ይተዋል። በፊት እዛው ተቀምጦ ግብር ማስከፈል ከሌሎች ገንዘብ ለመንጠቅ የተቀመጠ ነበር። አሁን ግን በኢየሱስ እይታ ተነክቶ ለሌሎች ገዛ እራሱን ለመስጠትና ለመሰዋት ይነሣል። ኢየሱስ አየው፣ ማቴዎስም በመታየቱ ምክንያት በማገልገል ዘንድ ካለው ደስታ ጋር ተገናኘ። ማቴዎስ በቀራጭነት ሙያው ዜጎችን ለገዛ እራሱ ጥቅም ያውል ይበዘብዝ ነበር። የሚያገለግል ዜጎችን ለገዛ እራስ ጥቅም መሣሪያ አድርጎ አይመለከትም፣ አይበዘብዝም መገልገያ መሣሪያ አያደርግም። የኢየሱስ እይታ በኢየሱስ መታየት አዲስ ተልእኮ ያነቃቃል፣ የአገልጋይነት የውፉይነት ተልእኮ ይወልዳል። ፍቅሩ ጠባቡና አጭር ርቀት ያለውን እይታችንን ይፈውሳል፣ ከአጭር አመለካከት ማዶ እንድንል ያደርገናል። እይታችን በውጫዊው ገጽታ ላይ እንዲሁም ፖለቲካዊ ተገቢነት በሚለው አጭር እይታ ላይ እንዳይታጠር ያደርጋል።

አንድ ከሃዲ ለኢየሱስ ጸጋ

አንድ ቀረጫ ከሌላው ገንዘብ ነጣቂ ወደ አገልጋይነት ይለወጣል ብለን እናምናለን? አንድ ከሃዲ የነበረ ወዳጅ ለመሆን ይችላል ብለን እናምናለን? አንድ የአናጢ ልጅ አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ ሊሆን እንደሚችል እናምናለን? የጌታ እይታ እይታችንን ይለወጣል። ልቡ ልባችንን ይለውጣል። እግዚአብሔር አባት የሁሉም ልጆቹ ድህነት ነው የሚፈልገው። የኢየሱስ እይታ የእርሱ ርህራሄ ምህረቱ ከታመሙት ከታሰሩት ከአረአጋውያን በስቃይና በችግር ከሚገኙት አቢያተ ሰብ ጋር ተካፍለን እንድንኖር ያደርገናል።

የኩባ ቤተ ክርስቲያን መሥዋዕትነት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስደመጡት ስብከት የክርስቶስ ኅላዌና ቃሉ ወደ ጥጋ ጥግ ወደ ሁሉም በማድረስ ተልእኮ የኩባ ቤተ ክርስቲያን በታሪ የከፈለችው መሥዋዕትነትና ያሳለፈቸውን መከራ ሁሉ አስታውሰው፣ በዚያ ወቅት በልኡካን እጥረት በካህናት እጥረት በተለያዩ የኩባ ከተሞች የጽሎት ቤት ተብለው ይጠሩ የነበሩት የእግዚአብሔር ቃል ይደመጥባቸው፣ ትምህርተ ክርስቶስ ይሰጥባቸው ማኅበራዊ ሕይወት ይኖርባቸው የነበሩትን ቤቶችን አስታውሰው፣ ይኽ ደግሞ በከተሞቻችን የእግዚአብሔር ህላዌ የሚያረጋግጥ ሁነት ነው ብለው የለገሱት ስብከት እንዳጠቃለሉና በመጨረሻም የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት እንዳበቃም ቅዱስነታቸው የኦልጊን ጳጳስ እራንጉአረን ኤትቸቨሪያን ምእመናን ሁሉ አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.