2015-09-21 16:00:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተሌግራም መልእክት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወደ ኵባና ወደ ተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ለማከናወን በተፈጸመው የበረራ ጉዞ ከኢጣሊያ በመጀመር የአየር ድንበሮቻቸውን ወደ ሚያቋርጡባቸው አገሮች ወደ ፈረንሳይ ስፐይን ፖርቱጋል የቴለግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው ለኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ሰርጆ ማታረላ ባስተላለፉት የቴለግራም መልእክት ለሳቸውና ለመላ የኢጣሊያ ሕዝብ ሰላምና የተሟላ ብልጽግ መመኘታቸው የገልጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ተመሳሳይ መልእክትም ለፈረንሳይ ለስፐይን ለፖርቱጋል መግንሥታት ጭምር ማስተላለፋቸው ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.