2015-09-21 15:55:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አሥረኛው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት፣ ኵባ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት ልክ 10 ከ 32 ደቂቃ ሮማ ከሚገኘው ፊውሚቺኖ ዓለም አቀፋዊ የአየር ማረፊያ ወደ ኵባ በመጓዝ አሥረኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደታቸውን መጀመራቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው በሚበሩበት አይሮፕላን ለተገኙት የውጭና የውስጥ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በጠቅላላ 76 ልኡካን ጋዜጠኞች ሰላምታቸውን በማቅረብ፣ ከጋዜጠኞች መጠይቅ መሠረት በማድረግ በዚህ ሰላም በተጠማው ዓለም አገናኝ ድልድይ መገንባት ያለው አስፈላጊነት አበክረው፣ ይኽ ወደ ኩባ በመቀጠልምን ወደ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ዑደት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡ በኋላ የሚፈጽሙት ረዥም ጉዞ መሆኑ በማስታወስ፣ በዚህ ጉዞ የሚሸኙዋቸውና የመገናኛ ብዙኃን ልኡካን ጋዜጠኞች ማመስገናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ሰላም በተጠማው ዓለም ድልድይ መገንባት

ቅዱስነታቸው ወደ አይሮፕላኑ እንደገቡ በጋዜጠኞች ፊት ቅዱስ አባታችንን የእንኳን ደህና መጡ አጭር መልእክት እንዲሁም እዛው ለተገኙት ጋዜጠኞችን የሰላምታ መልእክት ያስደመጡት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቀጥለው ቅዱስ አባታችን ባስደመጡት አጭር መልእክት፣ አባ ሎምባርዲ የጠቀሱት ሰላም የሚለው ቃል አስደግፈው በዚህ ጦርነት ግጭት ይኽ ሁነት የሚወልደው ከሞት ገዛ እራሳ ለማዳን ሕይወት ለማግኘት የስደተኛ ጸአት ሁነት ጠቅሰው፣ ከዚሁ ጋር በማያያዝ ወደ ጉዞው ከመነሳታቸው ቀደም በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ሃና ቁምስና መስተንግዶ የተሰጣቸው ሁለት የሶርያ ስደተኞች ቤተሰብ ጋር መገናኘታቸውና ያ ግኑኝነት ልባቸው እንደነካውና በእነዚያ ስደተኞች ፊት የሰላም ጥማት ቦግ ብሎ እንደሚታይ ገልጠው፣  አስፈላጊው ሰላም ብቻ ነው ብለው፣ ሁሉም በዚህ ጉዞ የሚሸኙዋቸው ጋዜጠኞችን በሚያከናውኑት ተልእኮ ያዓቢይ ድልድይ የሚጸናው ትናንሽ የሰላም ድልድይ ገንቢዎች ናችሁ ብለው፣ ከእያንዳንዱ ልኡክ ጋዜጠኛ ጋር ልባዊ ሰላምታ መለዋወጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.