2015-09-21 16:06:00

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በኵባ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 9 ሰዓት ሃቫና ኾሰ ማርቲ የአብዮት አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እንዳበቁ እኩለ ቀን ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ የዕለቱ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 9 ከቁጥር 30 እስከ 37 የተወሰደውን ምንባብ ተንተርሰው፣ በቅድሚያ የሃቫና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኻይመ ኦርተጋ አላሚኖ ላስደመጡት የወንድማዊ ቃል እንዲሁም ወድሞቼ በማለት ለገለጡዋቸው በጠቅውላላ ለሁሉም የኵባ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ገዳማውያን ዓለማውያን ምእመናን ለአገሪቱ ርእሰ ብሔርና ለመንግሥት አካላት አመስግነው፦ ኢየሱስ ስለ ሚቀበለው ስቃይና መከራ ሞት ሲናገር፣ ምን ማለቱ ይሆን የሚለው ጥያቄ በማቅረብ ደቀ መዛሙርት የተሰማቸው ፍርሃት ገሃድ ያደርጋሉ፣ ኢየሱስ በመስቀል እንደሚሰቃይ የተናገረው ቃል ያስፈራቸዋል፣ ትርጉሙንም ሊረዱት አልቻሉ፣ እኛም ከገዛ እራሳችንና ከሌሎች መስቀል ከሚሰቃየው ፊት ሁሉ እንሸሻለን፣ ኢየሱስ ሥጋውና ደሙን ሰጥቶናል፣ በዚህች ሰዓት መንፈሳዊ እይታችን እናታችን ወደ ሆነቸው ቅድስት ድንግል ማርያም እናቅና፣ በሚስቃየው የወድምና የእህት መስቀል አጠገብ እንድንገኝ ታስተምረን እርሷን እንማጠን። በእያንዳንዱ በመንገድ ዝሎ በሚገኘው ኃይሉ በተሟጠጠ በሚሰቃየው ሰው በእያንዳንዱ በተጠማው በተራቆተው በእስር በኅመም በሚሰቃየው ወንድም ሁሉ ውስጥ ኢየሱስን እንድናይ የበቃን እንድሆን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም እንማጠን፣ ከእናታችን ጋር ሆነን እጅግ ከፍ ያለው ዓቢይ ማን መሆኑ እንድናውቅና ከጌታ ጋር አንድ መሆንንና ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች ለመሆን በመስቀል ሥር እንገኝ።

ለሌላው ችግርና ለሚያስፈልገው ሁሉ ንቁ ሆነን ለመገኘት የነቃ ልብ መኖር ከማርያም እንማር። በቃና ዘገሊላ ሰርግ ለእያንዳንዷ ተናንሽ ለሕይወት ሁነት ማንም ከዚያ ገዛ እራሱን ከሚሰጠው ጌታ የሚመነጨው የፍቅር ወይን የሚሰጠው ደስታ የተነፍገ እንዳይኖር ስለ ሁሉም ከመጸለይ እንዳንዝል ማርያም ታስተምረን።

በዚህ አጋጣሚም ሃሳባቸውም ወደ ዚያች ልጆችዋ ሰላም የተካናት አገር ለመገንባት የሚሹት መስቀለኛ ሕይወት በመኖር ላይ ወደ የሚገኙባት አገር ኮሎምቢያ ለማቅናት ኃላፊነቱ እንደሚሰማቸው የገለጡት ቅዱስ አባታችን፣ በዚህች ረዥም አመታት ያስቆጠረው የትጥቅ ትግል ምክንያት የሚፈሰው የልጆችዋ ንፁሕ ደም ከዚያ በመስቀል ላይ ከፈሰሰው ከኢየሱስ ደም ጋር ተዋህዶ ሰላም እንዲረጋገጥና ሰላም ለማረጋገጥ ጥረት የሚያደርጉ በኵባ የሰላም ውይይት የሚያካሂዱት ሁሉ የሚፈለገው ወሳኝ እርቅ ለማረጋገጥ እንዲቻል ይደግፍ።

ያ ረዥም የስቃይ ሌሊት የዓመጽ ስቃይ  የመንግሥታት መከባበር ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የሕግ ሉአላዊነት ወደ ሚከበርበት  ዘላቂ ሰላም የሚሸኝ እንዲሆን ከሚመኘው የኮሎምቢያ ዜጎች ፍላጎት ፍትህ ወንድማማችነት ፍቅር ወደ የማይጠልቅበት ስምምነት ያድርስ። ይኽ ለሰላምና ለእቅር የሚደረገው ጉዞ እንዲከሽፍ እንፍቀድ፣ የኵባ ርእሰ ብሔር በኮሎምቢያ እርቅ እንዲረጋገጥ እያካሂዱት ያለው የገላጋይነት ሚና ቅዱስነታቸው በዚህ አጋጣሚም አመስግነዋል።

የሚያሳስበን የሚያስጨንቀን ሁሉ አስተንፎሷችን ጭምር በቅዱስ ልበ ኢየሱስ ለማኖር በማርያማዊ ጸሎት ሁባሬ እናድርግ፣ ተስፋ ስለ ቆረጡት ለመኖር ከመታገል ወደ ኋላ ስላሉት ፍትህ በመጓደሉም ስለ ሚሰቃዩት፣ በችግር ላይ ለብቻቸው ወደ ተተዉት በብቸኝነት ስለ ሚሰቃዩት፣ አረጋውያን ሕፃናት ወጣቶች የሁሉም ቤተሰቦች እምባ ማርያ ታብስ በእናትነት ፍቅሯ ታጽናናቸው ተስፋና ደስታ እንዲጎናጸፉ ትደገፍ፣ ቅድስት እናት ሆይ የኩባን ሕዝብ መቼም ቢሆን ለብቻው እንዳይተዉ ላንቺው አወክፋለሁ በሚል ጸሎት የለገሱት ስብከት አጠቃለው አደራ ስለ እኔ ጸልዩ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.