2015-09-21 16:09:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለወጣቶች፦ የላቀውን ነገር አስቡ፣ በጉዞ ጎዳና ለብቻችሁ እትሁኑ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ሃቫና በሚገኘው በአባ ፈሊክስ ቫረላ ስም በሚጠራው የባህል ማእከል ፊት ባለው አደባባይ ከወጣጦች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን በዙሪያቸው ከተሰበሰቡት ወጣቶች የቀረበላቸው ጥያቄ ማእከል በማድረግ በሰጡት አስተምህሮ፣ በገዛ እራስ የተዘጋ ወጣት የላቀው አቢይ ነገር ሊያልም አይችልም፣ እናንተ ወጣቶች ጸንታችሁ የላቀውን ሁሉ ከሰጣችሁ የምንኖርበት ዓለም ይለወጣል። የበለጠውን ለመስጠት ተማሩ። እንደኛ የማያስበውን የተለየ አመለካከት ያለውን ማክበር እንወቅ፣ ብዙውን ጊዜ በገዝ እራስ መዘጋት እንመርጣለን። በተቀበልነው ባመንነው ፖለቲካዊ ርእዮት ወይንም ሃይማኖታዊ አመለካከት ውስጥ ገዛ እራሳችን እንዘጋለን፣ ሃይማኖት ለዚህ ዓይነት ተግባር ስንገለገልበት የሃይማኖት የላቀውን ክብሩን እናጠፋለን፣ በምንከተለው ርእዮት ዓለም በግብረ ግበና ሃይማኖት አመለካከት ገዛ ኣሳችንን አንዝጋ አደራ።

ክፍት ልብና አእምሮ ይኑረን፣ መገናኘትና መወያየት የጠፋው እኰ የሚለያየን ላይ ስለ ምናተኩር ነው። አንድ የሚያደርገንን የሚያዋህደንን እናስብ፣ በጋራ ለጋራ ጥቅም እንጠመድ። ዓለም የሚወድመው በጥላቻ መንፈስ ነው። እጅግ የከፋው የክፋት መንፈስም ጦርነት ነው። መከፋፈል ሲኖር ሞት ይኖራል። በልባችን አንድ የሚያደርገንን ለሞት እንዳርጋለን ስለዚህ ማኅበራዊ ወዳጅነት መሻት ይኖርብናል።

ወጣት የሕዝብ ተስፋ ነው። ተስፋ ሲባል ተሰፈኝነት ማለት አይደለም፣ ተስፈኝነት አንድ የመንፈስ ሁነት ነው። ተስፋ ማለት ግን አይደለም፣ ተስፋ ማለት የተወጠነው እግብ ለማድረስ መሰቃየት ማለት ነው። መስዋዕትነት ይጠይቃል። ፍጻሜው ደግሞ መልካማ ፍሬ ነው። ሁሉ መልካም ይሆናል ብሎ ማሰብ ሳይሆን መልካም እንደሚሆን አምኖ በመስቀል ማለፍ ጭምር የሚኖርበት ነው።

ተስፋን የሚጎዱ ተስፋ ለመግደል የሚራወጥ ብዙ ናቸው። እነዚህ ደግሞ ወጣቱን እንደ ጥራጊ የሚመለከቱ ናቸው። በዚህ በአሁኑ ወቅት ገንዘብ በሚመለከበት ዓለም ወጣቱን መዘንጋትና እንደ ጥራጊ መመልከት የተለመደ ነው። ገና ሳይወለዱ ተገድለዋል እየተገደሉም ናቸው። በእድሜ የገፉትን መርሳትና እንደ ጥራጊ የሚመለከት ባህል፣ መመዘኛው ምርት የሚል ገንዘብ የሚያመልክ ባህል ነው። ይህ ባህል ደግሞ ተስፋን ይሰርቃል።

ተስፋ ከማድረግና ከመኖር አትቆጠቡ፣ ተስፋ አለ ማድረግ ገና ወጣት እያለህ ጡረተኛ መሆን ማለት ነው። ፈጥኖ ለመሄድ የሚፈልግ ለብቻው ይሄዳል፣ እሩቅ ለመድረስ ዓልሞ የሚጓዝ ግን የጉዞ ጓደኛ አለው። የግኑኝነት ባህል መኖር የተለያየ አመለካከት ቢኖረንም መገናኘትና አብሮ መጓዝ ነው በማለት የለገሱት ምዕዳን እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.