2015-09-18 16:31:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የሚተዉትና የሚጣሉት ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር የሚያርግ እምባ ናቸው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የስደተኞችና የተጓዦች ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንክብካቤ ለጎዳና ተዳዳሪ ታዳጊ ወጣት በሚል ርእስ ሥር በጠራው ዓውደ ጉባኤ የሚሳተፉትን ተቀብለው፦ የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናትና ሴቶች ልክ እንደ ሁሉም ሰው ልጅ የእግዚአብሔር ልጆችና እንደ ማንኛውም ሰው የሰብአዊ መብትና ክብር ባለ ቤት ናቸው፣ ተገዶ ካልሆነ በስተቀረ ማንም ሕፃን የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን አይመርጥም፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት ጉዳይ እጅግ የሚያሳዝን የግድ የለሽነት የድኽነት በቤተሰብ በማኅበራዊ ደረጃም የሚከሰተው ዓመጽ የወላጆች መለያየት ከትዳር ውጭ የሚወለዱት ሕፃናት ጉዳይ የሚወልደው አሳዛኝ ሰብአዊ ሁነት መሆኑና፣ በስፋት የእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍል ችግር መፍትሄ እንዳያገኝ የሚዳርገው ድኽነት የሚያስፋፋው ምግባረ ብልሽት ኢፍትሓውነት የመሳሰሉት እየተስፋፋ ያለው የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት ሰውን የመሸጥና የመለወጥ ኢሰብአዊ ተግባር መሆኑ አብራርተው፣ የጎዳና ተዳዳሪነት ማኅበራዊ ሰብአዊ ቤተሰብአዊ ኢፍትሐዊነት የሚያስከትለው የግዴታ ምርጫ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።

የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናትና ሴቶች በጠቅላላ እንደ ዕቃ የሚታዩ የመጠሪያ ሥም ያላቸው ከእግዚአብሔር የተሰጠ መለያ ያላቸው፣ ከእኛ ጋር እኩል ሰብአዊ መብትና ክብር ያላቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው። ለእግዚአብሔር እጅግ ቅርብ ናቸው። የሚያሳዝነው የምንኖርበት የሰለጠው ዓለም ዓለማዊ ትሥሥር የተካነ ተብሎ የሚነገርለት ሆኖ እያለ የእነዚህ ሕፃናት ሁኔታ እጅግ እየከፋ እንዲሄድ ማድረጉ ነው። ለከፋ አደጋ እንዲጋለጡ በሚያደርግ ጉዳይ አስተዋጽኦም አለው። ምክንያቱም ትምህርት የማግኘት መብታቸው፣ በቤተሰብ የመኖር መብታቸው ህክምና የማግኘት ሰብአዊ መብታቸው ተነፍጓቸው እንዲኖሩ ያስገድዳቸውልና። ልንረሳው የማይገባን ነገር ቢኖርም፣ የሚጣል ለብቻው የሚተው ለጎዳና ተዳዳሪነት ተላልፎ የሚሰጠው ለወንጀል ቡድኖች ለም መሬት ለመሆን የሚገደደው ሕፃን ሰው ልጅ በእኩል ወንድና ሴት አድርጎ በእርሱ አርአያና አምሳያ ወደ ፈጠረው እግዚአብሔር የሚያርግ እንባ ናቸው። የእነዚህ ሕፃናት እምባ በዓለም እግብር ላይ እየዋለ ያለው ማኅበራዊና ሰብአዊ ኢፍትሃዊነት የሚከስ ወደ ኣብ የሚያርግ ሰቆቃ ነው። የጎዳና ተዳዳሪዎች ሕወታቸውን ለንግድ በማቅረብ ዕለታዊ የጎዳና ተዳዳሪነት ሕይወታቸውን ሲገፉ የሚታዩት እነርሱ በእግዚአብሔር ቤት የሚቀድሙን ናቸው፣ እግዚአብሔር አያዳላም ነገር ግን በማፍቅር ምርጫ ድኻው የሚሰቃየው ያስቀድማል።

የጎዳና ተዳዳሪ የሚታይበት ዓለም እንዴት ተብሎ ነው የሰለጠነ በባህልና በልማት የመነጠቀ ተብሎ የሚገለጠው። ሙስና ምግባረ ብልሽት ሰውን ከመንከባከብ ይልቅ በገንዘብ ሃብት ለመደለብ የሚመርጥ ስግብግብ የኤኮኖሚ ሂደት የመሳሰሉት በኢፍትሓዊነት የሚጠቃለሉ ምርጫዎችና ተግባሮች የድኻው የጎዳናው ተዳዳሪ ሁነት የተከናነበው ችግር እጅግ እንዲባባስ ያደርጋል። የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር እናነቃቃ እባካችሁ፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናትና ሴቶች እንክብካቤና ጥበቃ እናነቃቃ።

ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን ተቋሞች ይኸንን ማኅበራዊ ኢፍትሓዊነት እንዳላዩ ሆነው መኖር አይችሉም፣ የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናትና ሴቶችን እንዳላየን ሆነን መኖር አንችልም፣ ለእነዚህ ዜጎች የእግዚአብሔር ፍቅር ምሕረትና ቅርበት በቃልና በሕይወት ለመመስከር ተጠርተናል፣ ምኅረት እግዚአብሔር ወደ እኛ እጅግ በበለጠ የሚቀርብበት ዘወትር መፈቀራችን ለሚያረጋግጥልን ተስፋ ክፍት የሚያደርግ ጸጋ ነው። የዚህ ተስፋ ልኡካን እንሁን ብለው የጎዳና ተዳዳሪዎችን በመደገፍ በመንከባከብ ተልእኮ የተሰማሩትን በማበረታታት የተጨቆኑትን የሚበዘበዙትን ነጻ ለማውጣት ተጠርተናል፣ ለሰብአዊ መብታቸውን ክብራቸው ጠበቆች ለመሆን ተጠርተናል፣ ጎንበስ ብለን ፍቅር ልንገልጥላችው ተጠርተናል ብለው የለገሱት ምእዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.