2015-09-14 15:46:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተሰብ ርእሥ ዙሪያ ሊመክር ስለ ተጠራው ሲኖዶስ መጸለይ የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ኅብረት


በቅድስት መሬት የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ባቀረቡት የግብዣ ጥሪ መሠረት የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ጉባኤ እ.ኤ.አ. እስከ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚዘልቀው ይፋዊ ዓመታዊው ጉባኤ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢየሩሳሌም እየተካሄደ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ማስትሮፊኒ ገለጡ።

ይኽ በኢየሩሳሌም በመካሄድ ላይ ያለው የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ኅብረት ይፋዊ ዓመታዊ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት አማካኝነት መከፈቱ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ማስትሮፊኒ አያይዘው፦ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ በዚህ የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር በቶች ሊቃነ መናብርት ኅብረት ጉባኤ ተሳታፊያን ብፁዓን ጳጳሳት አዲስ የፈጠራ ብቃት ያለው ለታደሰ መንገድ ምንጭ የሆነው ወንጌል የሚያስተጋባው ግልጽነትና እውነት ለመከተል የሚያበቃቸው የጸሎትና የትብብር ወቅት ይኖሩ ዘንድ ማሳሰባቸው አስታውቀዋል።

በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉአድ ትዋል ለጉባኤው በመካከለኛው ምስራቅ ስላለቸው ቤተ ክርስቲያንና የክርስቲያኖች ተጨባጭ እለታዊ ሁነት የሚያስተጋባ ንግግር እንዳስደመጡ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ማስትሮፊኒ አክለው፦ በቤየት ጃል የሚገኘው የፓትሪያርኩ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት አለቃ አባ ጃማል ክሃደር በመካከለኛው ምስራቅ የዘረአ ክህነት ተማሪዎች ሁነትና ጥሪ ርእስ ዙሪያ ለጉባኤው ንግግር ማሰማታቸው አስታውቀዋል።

መንፈሳዊ ንግደተ ወደ አናሥር

የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ኅብረት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዱራተ ዳ ኩኛ ፊርማ የተኖረበት ቀደም በማድረግ ስለ ጉባኤው በተመለከተ ተሰጥቶ በነበረው መግለጫ፣ በቅድስት መሬት ይፋዊ ዓመታዊው ጉባኤ ለማካሄድ የወሰነው የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ኅብረት፣ በቅድሚያ መንፈሳዊ ንግደት ወደ ቅዱሳት ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት ወደ የኤውሮጳ ባህላዊ አናሥር ክልል የሚል መሆኑ ገልጠዉት እንደነበር ያስታወሱት ማስትሮፊኒ በማያይዝ፣ ይኽ መካከለኛው ምሥራቅ የባህሎች አገናኝ ክልል የተለያዩ ኃይማኖቶች የተለያዩ ባህሎች የሚያገናኝ ክልል የክልሉ ህዝብ በሰላማዊ የጋራ ኑሮ ለመኖር ያገዘው ሆኖ እያለ በአሁኑ ወቅት ለተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ሆኖ ማየቱ ያሳዝናል፣ ስለዚህ በዚያ ክልል ማንኛውም ዓይነት ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሁሉ እንዲወገድ ጥሪ የሚስተጋባ ጉባኤ ነው እንዳሉ ያመለክታሉ።

የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ኅበረት የመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ ዓቢይ ግምት በመስጠት የጉባኤው መርህ ቃል የኢየሱስ ተክለ ሰብእነትና የኤውሮጳ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጋራ ተግዳሮት የሚል መሆኑ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ከተለያየው የቅድስት መሬት ተጨባጭ ሁነት ጋር ለመገናኘት በቅድስት መሬት የሚገኙትን ቅዱሳት ሥፍራዎች ከጋሊለያ ቀፈርናሆም እስከ ማግዳላ በመገኘት ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም በብሥራተ ገብርኤል ባዚሊካ. የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት የመሩት የዋዜማ ጸሎት መከናወኑ የጠቀሱት ልኡክ ጋዜጠኛ ማስትሮፊኒ አክለው፣ የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ሊቀ መናብርት ከክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር በቤተልሔም በቅድስት መሬት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ንብረትና ቅዱሳት ሥፍራ አቃቤ አባ ፒዛባላ ጋር እንዲሁም ከክልሉ ዓለማውያን ምእመናን ጋር እንደሚገናኝ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.