2015-09-09 18:04:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!

ዛሬ በቤተሰብና በክርስትያን ማኅበር መካከል ስላለው መተሳሰር ልናተኩር እወዳለሁ፣ ይህ መተሳሰር ባህርያዊ ነው፤ ምክንያቱም ቤተክርስትያን መንፈሳዊ ቤተሰብ ናት፤ ቤተሰብም ትንሿ ቤተክርስትያን ናት (ብርሃነ አሕዛብ ቍ.9 ተመልከት)፣ ማኅበረ ክርስትያን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆች ሁሉ የወንድማማችነት ምንጭ መሆኑን የሚያምኑ ቤት ናት፣ ቤተክርስትያን በሰውልጆች ማለትም በወንዶችን ሴቶች እናቶችና አባቶች ልጆችና ልጃገርዶች ታሪክ ትጓዛለች፣ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ታሪክም ይህ ነው፣ የዓለም ኃይለኞች ታላላቅ ፍጻሜዎች በታሪክ መጻሕፍት ይጻፋሉ እዛም ይቀራሉ፣ የሰው ልጆች የፍቅር ታሪክ ግን በእግዚአብሔር ልብ ይጻፋል፣ ይህ ታሪክ ደግሞ ለዘለዓለም እዛ ይኖራል፣ የሕይወትና የእምነት ቦታም ይህ ነው፣ ቤተሰብም ምትክ የሌለበት የማይደመሰስ ታሪክ ቦታ ነው፣ ታሪክ ማለትም ይህ ነው፣ በዚህ ታሪክ መላው የሕይወት ዘመን የእግዚአብሔር ቃል በማስተንተን ሲፈጸም ለዘለዓለም በሰማይ ይኖራል ነገር ግን ይህ አስተንትኖ በቤተሰብ ይጀምራል ስለዚህ ቤተሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው፣

ወልደ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ታሪክ የተማረው በዚህ መንገድ ነው፤ እስከ መጨረሻም ተከተለው (ዕብ 2፡18፤ 5፡8)፣ ስለኢየሱስ አንዴ ማስተንተንና የዚህ ትስስር ምልክቶች ማጥናት ጥሩ ይመስለኛል፣ እርሱ ከአንድ ቤተሰብ ተወለደ ዓለምንም በዚሁ አጠናው፣ በአንድ ትንሽ መንደር አራት ቤቶች ብቻ የነበሩት ነበር፣ ለሰላሳ ዓመት በዚህ መንደር እየኖረ የሰው ልጅ ሁኔታን ለበሰው፣ ይህን ሲያደርግ ከአባቱ ጋር በማወሃሃድና የተሰጠውን ሓዋርያዊ ተልእኮ በመቀበል ነበር፣ ናዝሬትን ትቶ ሕዝባዊ ሕይወቱን በጀመረበት ጊዜ በዙርያው አንድ ማኅበር ማለትም አንድ ጉባኤ ሰዎችን በመጥራት መሠረተ፣ ቤተክርስትያን የሚል ቃል ትርጓሜም ይህ ነው፣ በወንጌል እንደተመለከተው የኢየሱስ ማኅበር የአንድ ቤተሰብ መልክ ነበረው፣ አስተናጋጅ ቤተሰብ እንጂ በገዛ ራሱ ብቻ ተወስኖ የሚቀር የተዘጋና ወገኖቹን ብቻ ያካተተ ማኅበር አይደለም፣ በዚሁ ማኅበር ጴጥሮስንና ዮሓንስን እናገኛለን፤ እነኚህን ብቻ ሳይሆን የተጠማውን እንግዳውን የተሰደደውን ኃጢአተኞችንና መጸበሓውያንን ፈረሳውያንንና ሌሎች ሕዝቦችን እናገኛለን፣ ኢየሱስም ሁሉንም ለመቀበልና ከሁሉም ጋር እንዲያው በሕይወቱ ከእግዚአብሔር ጋር ሊገናኝ ከማይጠበቀውም ሳይቀር  ከመናገር አይቦዝንም፣ ይህ ለቤተክርስትያናችን ታላቅ ትምህርት ነው፣ ደቀመዛሙርት የተጠሩትም የዚች ማኅበር የዚች የእግዚአብሔር እንግዶች ቤተሰብ እረኞች እንዲሆኑ ነው፣

ይህ የኢየሱስ ማኅበር መንፈስ ዛሬም ሕያው እንዲሆን በቤተሰብና በማኅበረክርስትያን መካከል ያለውን ኪዳን እንደገና መቀስቀስ የግድ ይሆናል፣ ከእግዚአብሔር የሚገኘው ፍቅር ውህደት እውን የሚሆንባቸው ሁለት ቦታዎች ቤተሰብና ቍምስና ናቸው ለማለት ይቻላል፣ እንደወንጌል ደምብ የተቋቋመች ቤተክርስትያን ዘወትር በሮችዋን ክፍት በማድረግ የመስተንግዶ ቤት ከመሆን ሌላ መልክ ሊኖራት አይቻልም፣ አብያተ ክርስትያን ቍምስናዎችና ገዳማት በሮቻቸውን የዘጉ እንደሆነ ቤተክርስትያን ተብለው ሊጠሩ አይገባም፤ ቤተመዘከር ተብለው መጠራት አለባቸው፣

በዘመናችን ዛሬ ይህ ኪዳን መሠረታዊ ነው፣ ምክንያቱም በዘመናችን የሚታዩ የኃይል ማእከሎች ማለትም የርእዮተ ዓለም የምጣኔ ሃብትና የፖሎቲካ የኃይል ማእከሎችን እምቢ በማለት የገዛ ራሳችን ተስፋ የሆነው ፍቅርን ማእከል ያደረጉ የስብከተወንጌል ማእከሎችና በሰብአዊ ፍቅር የምቁ በመደጋገፍና በሱታፌ የተመሠረቱ ማእከሎች እናቅርብ፣ እንዲሁም እርስ በእርሳችን ይቅር በማለት ምሳሌ እንሁን፣

በቤተሰብና በማኅበረ ክርስትያን መካከል ያለውን መተሳሰር መጠንከር የግድና በአስቸኳይ የሚያስፈልግ ጉዳይ ነው፣ እርግጥ ነው ይህንን ኪዳን ለማሳደስ የሚረዳን እውቀትንና ብርታትን ለማግኘት እምነት ያስፈልጋል፣ አንዳንዴ ቤተሰቦች ብቃቱ የለንም በማለት ያንፈግፍጋሉ፤ “አባ ቤተሰባችን ድኃ ነው እንዲሁም ትንሽ ተበታትነን እንገኛለ! ይህንን ልናደርገው አንችልም! በቤታችን ውስጥ በቂ ችግር አለን፣ ለዚህ የሚሆን ኃይል የለንም” የሚሉም አሉ፣ እውነት ነው ነገር ግን ለዚህ ብቁ የሆነ ማንም የለም በቂ ኃይል ያለውም የለም! እግዚአብሔር በጸጋው ያልረዳን እንድሆነ ምንም ማድረግ አንችልም፣ ሁሉ በነጻ የተሰጠን ነው፣ ያልተቀበልነው ነገር የለም፣ ጌታም አንድ ተአምር ሳያደርግ አዲስ ቤተሰብን አይጎበኝም፣ በቃና ዘገሊላ ሰርግ የፈጸመውን ተአምር እናስታውስ! አዎ ሁሉንም ነገር በእጆቹ ያኖርነው እንደሆነ ጌታ ተአምር ይፈጽማል፣ በየዕለቱ ጌታ በመካከልዋ ያለች ቤተሰብ የምታገኛቸውን ተአምሮች ማስታወስ በቂ ነው፣

ማኅበረ ክርስትያንዋም የበኩልዋን ማበርከት እንዳለባትም ግልጽ ነው፣ ለምሳሌ ያህል ሕጎችንና ደንበችን ለሁሉ እንደሚመች ማድረግ ውይይትንና እውቀትን በመፍቀድ ተከባብሮ የመኖር ሁኔታ መፍጠር ሲሆን ቤተሰቦችም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ በመሆን የተቻላቸውን ማበርከት አለባቸው፣ ሁላችን ማወቅ ያለብን የክርስትና እምነት ክፍት በሆነ ሜዳ ከሁላቸው ጋር በማከፋፈል ነው፣ ቤተሰብና ቍምስና ለማኅበራዊ ኑሮ ተአምራዊ ሕይወት መፍጠር አለባቸው፣

በቃና ዘገሊላ የመልካም ምክር እናት የሆነቸው የኢየሱስ እናት እመቤታችን ድንግል ማርያም ነበረች፣ እርሷ የምትለንን እናዳምጥ “እርሱ ያላችሁን ሁሉ አድርጉ” (ዮሓ 2፤5) ብላ መልካም ምክር ትሰጠናለች፣ ውድ ቤተሰቦችና ውድ የቍምስና ማኅበሮች የዚህች እናት ምክር እንዲመራን ይሁን ኢየሱስ የሚለንን ሁሉ እናድርግ፣ እንዲህ ያደረግን እንደሆነ ተአምር ሲፈጸም እናያለን! በየዕለቱ ተአምር እናያለን፣ እግዚአብሔር ይስጥልን ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.