2015-09-07 16:06:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ቤተ ክርስቲያን አለ ምንም ቅድመ ፍርድ ሁሉን ታስተናግድ


“ቤተ ክርስቲያ የአብ ቤት ሁሉንም ደጉም ይሁን ክፉውን ሁሉ አለ ምንም ቅድመ ፍርድ የምታስተናግድ የሁሉም ቤት ነች፣ ሁሉንም ማስተናገድ” ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በ1980 ዓ.ም. በኢጣሊያ በአባ ፒየርጆርጆ ፐሪኒ የሚላኖ ሰበካ ካህን የተመሠረተው ዓለም አቀፍ የሁሉም ቁምስናዎች የአስፍሆተ ወንጌል ማእከል ከመላ ዓለም የተወጣጡት በጠቅላላ አራት ሺሕ የሚገመቱት አባላት የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ከተሳተፉ በኋላ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርልይልኮ በተገኙበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው ወንጌላዊ ኃሴት የወንጌላዊ ልኡክነት ኃሴት ነው በሚል ርእስ ሥር በለገሱት ምዕዳን እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ ገለጡ።

አለ ምንም ቅድመ ፍርድ ሁሉንም ማስተናገድ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላችን ኅልው መሆኑ በመካከላችን የምንቋደስውን የሚቆረሰው ኅብስት በተጨባጭ የሚያረጋግጠው የቅዱስ ቁርባን ማኅበርሰብ መሆን የእግዚአብሔር የዋህነት ደግነት ለሁሉም ለእያንዳንዱ ሰው በተለይ ደግሞ በብቸኝነት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚኖረው ቅርብ መሆኑ የሚመሰከርበት ነው። ይኽ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. ሚያዝያ ወር ላይ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እውቅና ያገኘው የቁምስናዎች የአስፍሆተ ወንጌል ማእከል አለ ምንም ቅድመ ፍርድ ሁሉም የሰው ልጅ የሚስተናገድበት የእግዚአብሔር የመለኰታዊ ምኅረት ቤተ እንዲሆኑ ማሳሰባቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው፣ ፈራጁ ጌታ ብቻ ነው፣ ስለዚህ ለመፍረድ ቢቃጣህ አደራ አንድም ፈራጅ ቃል ከአፍህ አይውጣ፣ ጌታችን ኢየሱስ አትፍረድ ይፈረድብሃልና ብሎ ተናግሮናል። ከሁሉም ጋር አለ ምንም ውስስብነት አብረን እንኑር፣ መስተንግዶ መስጠት ማስተናገድ የእግዚአብሔር ኅልውናና የወንድሞች ፍቅር የመኖር ገጠመኝ ያሰጠናል። አስፍሆተ ወንጌል መስተንግዶና ቅርበት ያሰማል፣ ይህ ደግሞ ክርስቲያን የመሆኑ ተቀዳሚው ገጠመኝ ከክርስቶስ ጋር መገናኘትና እርሱን በልብ ማስተናገድ ማለት ነው እንዳሉ አመለከቱ።

መንፈስ ቅዱስ ባልተጠበቀና ባልታወቀ መንገድ እንጓዝ ዘንድ ያነቃቃናል

ቅድስነታቸው ቤተ ክርስቲያን በሮችዋ የተከፈተ ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የኅልውና ክልል ታቀና ዘንድ ደጋግመው የሚሰጡት ምዕዳን ዳግም በማበከር የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ከሁሉም ጋር በመገናኘት ለሁሉም የወንጌል ውበት ማበሰር የሚል ነው። ወንጌላዊ ልኡክነት በቅድሚያ ያ ካለ ማቋረጥ ለቤተ ክርስቲያን የሚናገረው ቤተ ክርስቲያንን ለወንጌላዊ ልኡክነት ባል ተለመደና ባልታሰበ  ሆኖም ለአስፍሆተ ወንጌል መሠረት በሆኑት መንገዶች ለሚመራው መንፈስ ቅዱስ ማዳመጥ ማለት መሆኑ እንዳብራሩ አኵይላኒ ገለጡ።

የማኅበር ሕጎችን ለማቀብ የመንፈሳዊ ማኅበር መንፈሳዊ መርሆ ማጣት አይኑር

ምንም’ኳ ድካም ዕለት በዕለት እክል በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮም ጭምር ቢያጋጥም ለጌታ ቃል ታማኝ መሆን ቃሉን ለማዳመጥ ክፍት መሆን አደራ፣ የመንፈሳዊ ማኅበሮች ደንቦች የመንፈሳዊ ማኅበራት መንፈሳዊ መርሆ እግብር ላይ ለማዋል የሚደገፍ እንጂ የሞተ ደንብ መሆን አይገባውም።

የቁምስና አባላት አንድ ቤተሰብ እንዲሆኑ

የተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች ያ የተለያየ ጥሪ መግለጫ የሆኑት የቁምስና አባላት መካከል በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ የተኖረው ደስታና ተስፋ ልክ እንደ ቀደምት ክርስቲያኖች የሚቋደስበት አንድ ቤተሰብ እንዲሆኑ የሚደግፉ መሆን ይገባቸዋል።

ቤተ ክርስቲያን የአብ ቤት የሁሉም ለሁልም ቤት ነች

ማኅበረ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን የሕይወት ማእከል በማድረግ ወንጌላዊ ተልእኮና ልኡክነት የማኅበረ ክርስቲያን የሕይወት ሥልት ሆኖ የወንጌል ውበትና የእምነት ውበት የሚመሰከርበት አለ ምንም ገደብ ፍቅር የሚኖር ነው። ቤተ ክርስቲያን የአብ ቤት ነች፣ በዚህች ቤት ለሁሉም ቦታ አለ፣ አለ ምንም ልዩነት ደጉም ክፉም በኢየሱስ ክርስቶስ ምኅረት ሥር በመሰባሰብ የሚኖርበት ቅዱስ ሥፍራ ነው በማለት ያስደመጡት ምዕዳን ማጠቃለላቸው አኵይላኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.