2015-09-02 16:07:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የክርስቲያን ጽናት ኢየሱስ እንጂ ጉርምርምታ አይደለም


እ.ኤ.አ. መስከረም 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት እንደ ተለመደው ጧት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ከቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ የጻፈው ቀዳሜ መልእክት ምዕ. 5 ከቍ. 1-6፣ 9-11 እንዲሁም ከወንጌል ሉቃስ ምዕ. 4 ከቍ. 31-37 የተወሰደውን ንባባት በማስደገፍ፦ በመጨረሻም ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ያለው ተስፋ በቃልና በሰናይ ምግባር በተሸኘ በክርስቲያኖች መካከል በሚኖረው መጽናናት አማካኝነት ሊበራታ ይገባዋል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

በመጨረሻ ከክርስቶስ ጋር መገናኘት እንደሚኖር የሚያረጋግጥ እምነት እጅግ ከመጠራጠር የበረታ ነው። ስለዚህ ይኽ እምነት ዕለት በዕለት ደስታ የተካነ በክርስቲያኖች መካከል በሚኖረው ኢየሱሳዊ የጋራ መጽናናት ላይ የጸና እንጂ በጉሩምርምታና አርባና አልቦ በሆነ ነገር ላይ የተመሠረተ ሊሆን አይገባውም። ጥንታዊው የተሰሎንቄ ማኅበረ ክርስቲያን የክርስቶስ ዳግም መምጣት መቼና እንዴት ባለ ሁነት ነው የሚል፣ የሞት ዕጣ እድልስ ምን ይሆን፣ እንዳውም የማይሰራ አይብላ የሚል ሕግ እንዳለም በማስታወስ ለቅዱስ ጳውሎስ ያቀረበው ያነበረው ጥያቄ ያ ማኅበረ ክርስቲያን የታወከ  የተጨነቀ እንደነበር እናስተውላለን።

ጉርምርምታ መጽናናትን አያሰጥም

ቅዱስ ጳውሎስ ይላሉ ቅዱስ ኣባታችን፣ የጌታ መምጣት የማይቀር ነገር ግን መቼ መሆኑ የሚታወቅ አይደለም፣ ልክ ሌባ የሚመጣበት ቀን እንደማይታወቀው ዓይነት ነውና። ኢየሱስ በእርሱ ላመኑት ድህነት ለማጎናጸፍ ዳግም ይመጣል። እርስ በእርሳችሁ ተጽናኑ ይኽ የጋራ መጽናናት ነው ተስፋ የሚያሰጠን እንዳሉ የገለጡት ደ ካሮሊስ አክለው፦ ምክሩም እርስ በእርሳችሁ ተጸናኑ የሚል ነው። እኛስ ስለ ክርስቶስ ዳግም መምጣት በተመለከተ እርስ በእርሳችን እንነጋገራለ ወይንም ስለ ቲዮሎጊያ ስለ ካህናት ስለ ደናግል ስለ ቤተ ክርስቲያን ስለ አቡናት በመሳሰሉት አሉ ባልታ ርእሰ ጉዳያች ላይ በማተኮር የምንወያየው? እርስ በእርሳችን እንዲህ ባለ አሉ ባልታዊ በሆነ ውይይት ነው የምንጽናናው? ተስፋችን የዚህ ዓይነት አሉ ባልታ ነውን? በቁምስናችን የኢየሱስ ዳግም የመምጣት ጉዳይ ነው የምንወያየው? እስቲ ገዛ እራሳን እንጠይቅ እንዳሉ ገለጡ።

የመጨረሻው ፍርድና የጌታ እቅፍ

የዕለቱ መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 26(27) በተለይ ደግሞ ቍ. 13 “ሕያዋን በሚኖርቱባት ምድር የእግዚአብሔር ቸርነት እንደማይ እተማመናለሁ” አንተ አንቺ እኔ ይኽ አይነቱ የተረጋገጠ እምነት አለን ወይ? ኢዮብን መምሰል፣ “አዎ እግዚአብሔር ሕያው መሆኑ እታመናለሁ፣ በመጨርሻም እንደማየው እርግኘኛ ነኝ፣ በእነዚህ አይኖቼ አየዋለሁኝ” እንላለን ወይ?

እውነት ነው እርሱ ሊፈርድ ዳግም ይመጣል፣ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ሲስቲና ቤተ ጸሎት ያለው የመጨረሻ ፍርድ የሚያወሳው የስነ ቅብ ድንቅ ሥራ እናያለን። በእነዚህ አይኖቼ አየዋለሁኝ፣ በእቅፉም እኖራለሁኝ የሚል ተስፋ ያለን መሆን ይገባናል፣ የዚህ ተስፋ በቃልና በምግባር መስካሪያን መሆን ይጠበቅብናል፣ የጌታ ቸርነት እንደማይ እተማመናለሁ” እንበል።

መጽናናት በቃልና በሰናይ ምግባር

እንደ ጥንቱ ቅዱስ ጳውሎስ ለማኅበረ ክርስቲያን እንደመከረው ሁሉ ዛሬም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዛሬይቱን ቤተ ክርስቲያን እርስ በእርስ በቃልና በሰናይ ምግባር በተካነ መጽናናት መደጋገፍ የምትኖር ትሆን ዘንድ ምዕዳን ያቀርባሉ።

ቅዱስነታቸው የዕለቱ ያስደመጡት ስብከትም፦ ጌታ ይኸንን ጸጋ እንለምነው፣ በእያንዳንዳችን ልብ የዘራው የተስፋ ዘር እንዲያብብ ከእርሱ ጋር እስከምንገናኝበት ቀንና ሰዓት ድረስ ያድግ ዘንድ ጸጋው ያብዛልን፣ እርግጠኛ ነኝ ጌታዮን አየዋለሁ። እርግጠኛ ነኝ ጌታ ሕያው ነው። እርግጠኛ ነኝ ሊገናኘኝ ይመጣል፣ ይኽ ነው የሕይወታችን አድማስ። ይኸንን ጸጋ ጌታን እንለምነው፣ በዚህ ጉዞ እርስ በእርሳችን በቃልና በምግባረ ሰናይ እንጸናና አደራ በሚል ጸሎት እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.