2015-08-31 15:02:00

ቅድስት መንበር


በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕንጻ የጠቅላላ 193 አባል አገሮች ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ የሚውለበለብ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልምድ እንዲህ ቢሆንም ቅሉ የታዛቢ አገሮች ሰንደቅ አላማ ጭምር እንዲውለበለብ የፍልስጥኤም የራስ ገዝ መስተዳዳር መንግስት ልኡካን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 2015 ዓ.ም. ኒው ዮርክ በሚገኘው በድርጅቱ ሕንፃ የሚያካሂዱት ጉብኝት መሠረት በማድረግ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ ያቀረበው ጥያቄ የአገረ ቫቲካንና የፍልስጥኤም ስንደቅ ዓላማ የሚመለከተው ጉዳይ፣ አገረ ቫቲካን ምንም’ኳ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የታዛቢ አገሮች ሰንደቅ ዓላማ እንዲውለበለብ ማድረግ የድርጅቱ የቆየ ልምድ ባይሆንም ቅሉ ሃሳቡን እንደማይቃወም ከቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል የተሰጠው መግለጫ ይጠቁማል።

የአገረ ቫቲካን ይፋዊ መግለጫ ያቀረበው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል፦ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገር ሰንደቅ ዓላማ ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ ጥያቄ እንዳይቀርብ አባል አገሮችም ሆኑ ታዛቢ አገሮች የመቃወም ሕጋዊ መብት የላቸውም እንዲህ በመሆኑም ቅድስት መንበር የቀረበው ጥያቄ እንደማትቃወም አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. ከ 1945 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅዋሜ ወዲህ የድርጅቱ አባል አገሮች ሰንደቅ አላማ ብቻ በድርጅቱ ዋና ጽሕፈት ቤት ባለው አደባባይ እንዲውለበለብ ማድረጉ የቆየ ልምድ ቢሆንም ቅሉ የታዛቢ አባል አገሮች ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብ ለቀረበው ጥያቄ ጠቅላይ ጉባኤው ለሚሰጠው አሉታዊም ይሁን አወንታዊ ምላሽ ቅድስት መንበር ከወዲሁ እንደምትቀበለው የቅድስት መንበር መግለጫ የጠቆመ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ያሰራጨው ዜና ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.