2015-08-28 15:34:00

ብፁዕ ካርዲናል ሞንተነግሮ፦ የስደተኛው ጸዓት የሚገታው ኢፍትሓዊነት በመዋጋት ነው


በኢጣሊያ የአግሪጀንቶ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፍራንቸስኮ ሞንተነግሮ የስደተኛው ጸዓት የሚገታው በዓለም የተረጋገጠው ሕዝቦች ለተለያየ አደጋ የሚያጋልጠው ኢፍታሐዊነት ማስገድ ብቻ ነው እንዳሉ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰየመው ማኅበር ያሰራጨው መግልጫ ጠቁሞ፣ ብፁዕነታቸው ክፋቱ ስደተኛው ወይንም መሰደድ ሳይሆን ኢፍትሓዊነት ነው። በዓለም እየተስፋፋ ያለው ኢፍትሓዊነት እስካልተወገደ ድረስ የስደተኛው ጸኣት መፍትሔ ያገኛል ማለት ዘበት ነው። በአሁኑ ወቅት የሚታየው ስደት፣ ስደተኛው በኤኮኖሚ ችግር ተገፋፍቶ ኑሮውን ለማሻሻል በሚል ምክንያት የተነቃቃ ሳይሆን ከጦርነት ከእርሃብ የሃይማኖት አድልዎ ከሚያስከትለው ስቃይና መከራ ለማምለጥ የሚል ምክንያት የሚያስከተለው ውሳኔ ነው እንዳሉ አስታወቀ።

መጽሓፍ ቅዱስና ቁርአን በላምፔዱዛ

በሜዲትራኒያን የባህር በር በኩል ወደ ኤውሮጳ የሚሰደዱት ብዙዎቻቸው እንደ እምነታቸው መጽሓፍ ቅዱስና ቁርአን ይዘው እንደሚገኙ ገልጠው። ስደተኞች ስለ ሃይማኖታቸውና እምነታቸው ሃሳብ ለሃሳብ እንዲለዋወጡና በሃይማኖቶች መካከል መቀራርብና መተዋወቅ እንዲኖርም በላምፔዱዛ ቅዱስ መጽሓፍና ቁርአን በሚል ርእስ ዙሪያ ዓውደ ጉባኤ መካሄዱ አስታውሰው፣ ፍትሕ መጓደል አቢይ ለስደት የሚዳርግ ምክንያት ነው እንዳሉ የሚሰቃዩት አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰኘው ማኅበር አስታወቀ።

መስተንግዶ አለ የሃይማኖት ልዩነት

ሓበሻ የተሰየመው ማኅበር በሰጠው መግለጫ ባለፉት የመጨረሻ ዓመታት ውስጥ ወደ ኤውሮጳ በሜዲትራኒያን የባህር በር በኵል ከሚስደደው በጠቅላላ የክርስቲያን ስደተኞች ብዛት በቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱና ብዛቱም 30% የሚሸፍን መሆኑ ሲያመለክት፣ ለስደተኛው አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ተገቢ መስተንግዶ የሚሰጥ መሆኑ ብፁዕነታቸ ገልጠው፣ የምትከተለው ሃይማኖት አባል በሞት ሲለይ እጅግ ይነካሃል፣ ሆኖም የሚሰማህ ስቃይ የሚያዋህድ እምነት መኖር የአንተ እምነት የማይከተለውን እንድትጠላ የሚያደርግ ሳይሆን ለሚሰቃየው ሁሉ ቅርብ እንድትሆን የሚያነቃቃ ነው። የቋንቋ የጎሳና የሃይማኖት ልዩነት ለመቀራረብና ለመደጋገፍ ምክንያት መሆን አለበት። ክርስቲያን በክርስቶስ የተገለጠለት ፍቅር የማያዳላ የማይነጥልና ሌላውን በማፍቅር የሚኖር ፍቅር ነው የሚል እምነት የሚከተል ነው እንዳሉ የሚሰቃዩት አቢያተ ክርስቲያን እንርዳ የተሰኘው ማኅበር አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.