2015-08-26 16:28:00

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፦ የስደተኞች ጸአት


ወደ ሰሜን ኤውሮጳ ለመግባት አንድ መቶ ሺሕ ስደተኞችና ተፈናቃዮች ሰርቢያን ማቋረጣቸውና ወደ አራት ሺሕ የሚገመቱት ደግሞ ለአገረ ሰርቢያ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠያቃቸው የአገሪቱ መግንሥት የሰጠው መግለጫ ይጠቁማል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መግለጫ የሰጠው ግምት እንደሚያመለክተውም በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ሦስት ሺሕ የሚገመቱ ስደተኞችና ተፈናቃዮች የግሪክንና የመቄዶንያ ድንበር እንደሚያቋርጡ ሲነገር፣ ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቡልጋሪያንና መቄዶንያ በሚያዋስነው ክልል ያለው ሁኔታ የሶፊያ መንግሥት የስደተኞችን ጸአት ለመግታት ሲል የወሰደው እርምጃ ምክንያት ውጥረት እየታየ መሆኑ ተገልጠዋል።

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ድርጅት እ.ኤ.አ 2015 ዓ.ም. ከተገባበት ወዲህ ብቻ በባህር ጉዞ ሁለት ሺሕ ሶስት መቶ ስደተኞች ሕይወታቸው እንዳጡ በማሳወቅ፣ ወደ 40 ሺሕ የሚገመቱ ስደተኞች ወደ ጠቅላላ የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ማከፋፈል የሚቻል ብቻ ሳይሆን በእውነቱ የሚዳረሰው ቁጥርም አነስተኛ መሆኑ በማሳወቅ፣ ያለው የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጸአት ግምት በመስጠትም የበርሊን መንግሥት የዱብሊን ውል እርሱም ስደተኛው በገባበት አገር የፖለቲካም ሆኖ የኤኮኖሚ ጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ ይኖርበታል የሚል ውሳኔ የተኖረበት የስምምነት ውል ለጊዜው እንዲቋረጥ በማለት ጥያቄ ማቅረቡ የኢጣሊያ የተፈናቃዮችና ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር አስተዳዳሪ ክሪስቶፈር ሃይን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ የስደተኞች ጸአት ግምት በመስጠት ሁሉም የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች መንግሥታት የዱብሊን የስምምነት ውል ገቢራዊ ሆኖ መቀጠል እንደማይችል የሚያወቁት እውነት ነው። በባብሕር ጉዞ በኩል 110 ሺሕ ስደተኞች ገብተዋል ከእነዚህ ውስጥ 40 ሺሕ የሚገመተው ብቻ ነው የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ያቀረበው ይኽ ደግሞ በባህር በር በኵል ከገባው ብዛው ውስጥ ሁለት ሦስተኛውን የሚሸፍነው ወደ ሌሎች የኤውሮጳ አገሮች ተሻግረዋል ማለት ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ የዱብሊኑ ስምምነት ገቢራዊ ሊሆን እንደማይችል የተረጋገጠ ነው። ስደተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ኢጣሊያና ግሪክ ነው የሚገባው፣ በገባበት አገር ጥገኝነት ይጠይቅ በማለት የዲቡሊን የስምምነት ውል እንዲከበር ችክ ማለት ትርጉም የለውም፣ በመሆኑም የሚገባው ስደተኛና ተፈናቃዩ ለገባበት አገር ሸክም አድርጎ መተው ሳይሆን ወደ ጠቅላላ 28 የኤውሮጳ አባል አገሮች ማዳረስ ያስፍልጋል ብለዋል።

ስለዚህ ስደተኛው ወደ ሁሉም የኤውሮጳ አባል አገሮች ማዳረስ የሚለው እቅድ የስደተኛው አገር ታሪክ እንዲሁም በኤውሮጳ አገሮች ቤተሰብ ወይንም ዘመድ አለው የለውም ቀድሞ ማወቅ፣ የፖለቲካ ጥገኝነት ያገኘው ስደተኛ እውቅና ባገኘበት የኤውሮጳ አገር ለመኖር መገደድ የለበትም ከዚህ በፊት እንደሚደረገው ለጉብኝት ወደ ሌሎች የኤውሮጳ አገሮች ለጉብኝት እርሱም የሦስት ወር የሚያገለግል የመግቢያ ፈቃድ መስጠት ሳይሆን በኤውሮጳ አባል አገሮች ውስጥ ኑሮው ለመመሥረትና ለሥራ ፍለጋ እንደ ማንኛውም የኤውሮጳ ዜጋ ሊፈቀድለት ይገባል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.