2015-08-21 15:20:00

ኬንያ፦ ብፁዕ ካርዲናል ንጉወ፦ ቤተሰብ ለአደጋ ለሚያጋልጥ ምርጫ እምቢ


ማኅበረ ክርስቲያን ለክርስትናው እምነት ታማኝ በመሆን ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው አፍሪቃዊ ቤተሰብአዊ ባህልና ክብር የሚያናጋው የምዕራቡ አለም አመጣሽ አዲሱ በመዛመት ላይ ካለው ሃሴተኛ እሴትና የሕይወት ስልት እንዲታቀቡና በዚህ ምዕራባዊ ባህል ተጽእኖ እንዳይሳብ በቅርቡ በስዋህሊኛ ቋንቋ የኬንያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጆን ንጉወ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በደላዋረ ግዛት በምትገኘው በአር ከተማ ተገኝተው ለአመሪካ ኬናውያን ማኅበርሰብ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት አደራ እንዳሉ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

ብፁዕነታቸው ለአመሪካውያን የኬንያ ማኅበርሰብ በግላዊ ነጻነት ሥምና የግል ነጻነት ማረጋገጥ በሚለው ጽንሰ ሃሳብ አስባብ ለሚፈጠረው ባህል አደራ እጃቸውን እንዳይሰጡ ጥሪ በማቅረብ ብዙዎቻቸው በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከኬናውያን ቤተሰብ የተወለዱና በዚያች አገር ያደጉ ኬናውያን አመሪካውያን ሁሉ የአፍሪቃ ማኅበራዊ ሰብአዊ ባህል በማክበር ክርስትናው እምነታቸውን እንዲኖሩ አደራ በማለት፣ በምዕራቡ ዓለም እምነትን የሚጋፈጥ ለባህልንና ለእምነት ተግዳሮት የሆነውን ሁሉ ለክርስትያናው እምነታቸው ታማኝ በመሆን የማያሻማው ለገበያ የማይወርደው ክርስቲያናው እሴት እንዲኖሩና እንዳሻህና እንደ መረጥከው የሚለው እሴት ለሚያረማምደው አዲስ የነጻነት አመለካከት እምቢ እንዲሉ ጥሪ ማቅረባቸውንም የኬንያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አስታወቀ።

ቤተሰብ የማኅበረሰብና ኅብረተሰብ ማእከል

የክርስትናውና የአፍሪቃዊው እሴት የሚጻረሩ በምስፋፋት ላይ የሚገኙት ቤተሰብንና ቤተሰብአዊ ጥሪ የሚቀናቀኑ ጸረ ቤተሰብ አመለካከቶችና ምርጫዎች የሚያስፋፉ ርእዮተ ዓለም ሁሉ ለእምነትና ለአፍሪቃዊው እሴት ታማኝ በመሆን እምቢ በማለት ጤናማው ባህልና ክርስቲያናዊ እሴት ለመጪው ትውልዱ እንዲያስተልፉ አደራ እንዳሉ የኬንያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ያመለክታል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.