2015-08-19 15:27:00

ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአርጀንቲና፦ ሙስና የሕዝብ ተስፋ ስርቆት ነው


ሙስና የገዛ እራስ ያልሆነ ገንዘብ ቅጥፈት ማለት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ተስፋ መስረቅ ማለት መሆኑ የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር የጉኣለጉኣያቹ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኾርገ ላዛኖ በቅዱስ ኢሲደሮ መንበረ ጥበብ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር እንዳሰመሩበት ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

በሚከስቱት ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ እጅግ ተጠቂው ድኻው የኅበረተሰብ ክፍል ነው

ብፁዕ አቡነ ላዛኖ ባስደመጡት ንግግር የመዋቅራዊ ሓጢአት ጥልቅ ትርጉሙን አብራርተው፣ በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች በሚከስተው የተፈጥሮ አደጋ በስፋት ተጎጄው ድኻው ኅብረተሰብ መሆኑ ገልጠው። መዋቅራዊ ኃጢአት ሙስናን እንዲኖር የሚያደርግ፣ የሰው ልጅ በሕገ ወጥት ተግባር ከቦታ ቦታ ማዘዋወር፣ ሰውን ለአዲስ ባርነት እርሱም ጸረ ሰብአዊ ለሆነው ጸያፍ ተግባሮች መዳረግ የመሳሰሉት ሁሉ እንዲከሰት የሚያደርግ ነው። ለዚህ ለከፋው አደጋ በስፋት የሚሚጋለጠው ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ሙስና መዋቅራዊ ሐጢአት የሚወልደው ሐጢአት ነው

ማኅበራዊ መዋቅሮች መዋቅራዊ ኃጢአት የሚያነቃቃ የተለያየ ምግባረ ብልሽት የሚያበረታታ ሙስናና ብዝበዛ የሚያስፋፋ ነው፣ ስለዚህ መዋቅሮች ለኃጢአት የሚገፋፉ ድኽነት የሚያስፋፉ እንዳይሆኑ ኅብረተሰብ በግብረ ገብና በሥነ ምግባር ማነጽ ወሳኝ ነው። ስለዚህ መዋቅራዊ ኃዳሴና ለውጥ ያለው አስፈላጊነት ሲያብራሩም ፍትህና ትብብር ላይ የጸና መዋቅር ሲኖር መዋቅራዊ ኃጢአት እንደማይኖር ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.