2015-08-05 19:34:00

የር.ሊ.ጳ ሳምታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ስለቤተሰብ የጀመርነውን አስተንትኖ በመቀጠል ያ ባለፈው ጊዜ የተመለክትነው ስለቈሰሉ ቤተሰቦችና በባልና ሚስት መካከል ስለሚከሠቱ አለመግባባቶችን ጋር በመያያዝ ዛሬ በዚሁ ችግር ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን መፈወስ ላልቻሉና አዲስ የሕይወት ጐዳና የጀመሩትን እንዴት መርዳት እንደሚቻል እንመለከታለን፣

ይህ ዓይነት ኑሮ የቤተክርስትያን ምሥጢራትን እንደሚቃወም ቤተ ክርስትያን ጠንቅቃ ታውቃለች፣ ይህንን ስታደርግ ግን እናት በመሆንዋ መጠን በእናታዊ ርኅራኄ በተሞላበት ልብ ሲሆን ይህም ልብ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የሁሉም ሰዎች መልካም ኑሮና ደህንነትን ይሻል፣ ስለዚህም ነው “ስለእውነት ፍቅር” ስንል ከሁኔታዎቹ ባሻገር ልንመለክትና ትርጉም ልናገኝ የምንጥረው፣ ቅ.ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ፋሚልያሪስ ኮንሶርስዮ በተሰኘው ሓዋርያዊ ም ዕዳናቸው ቍ.84 ላይ እንዳመለከቱት በቃል ኪዳን መፍረስ የተለያየ ሰውን የመለያየቱ ምክንያት ከሆነው አንጻር መመልከት ያስፈልጋል በማለት የገለጡት፣

እነኚህን መለያየቶች በትናንሽ ሕጻናት ዓይን የተመለከትናቸው እንደሆነ ምክንያቱም ትናንሾቹ በሕጻናት ዓይን ይመለከቱታልና፤ እኛም እንዲሁ ያስተዋልን እንደሆነ በዚሁ ሁኔታ የተጐዱ ብዙ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እንገነዘባለን፣ ስለዚህ ማኅበረሰቦቻችን እነኚህን በተመለከተ በተለይ ደግሞ የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ብዙ ከሚሰቃዩት ከትናንሾቹ በመጀመር በእነዚህ ሰዎች ላይ ያላቸውን አስተያየት ቋንቋ ዝንባሌና አመለካከት ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት፣ በተረፈው ዋነኛው ጥያቄ ማኅበረሰቦች እነኚህን ሰዎች እንደተወገዙ ከማኅበሩ ያገለላቸው እንደሆነ እነኚህ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት አድርገው ክርስትያናዊ አስተዳደግ ሊለግሱ እንደሚችሉና ምን ዓይነት የእምነት ምስክርነት ሊሰጡ እንደሚችሉ ነው? በመለያየቱና በጭቅጭቁ ከሚገጥማቸው ሥቃይ በላይ ሌላው የጨመርን እንደሆነ ለልጆቹ እጅግ ከባድ ነው፣ የሚያሳስበው ደግሞ ቍጥራቸው በየዕለቱ እያደገ መምጣቱ ነው፣ እነኚህ ልጆች ቤተ ክርስትያንን ነገሮችን ሁሉ በጥንቃቄ እንደምትመለት እናትና ሁሌ ልትቀበላቸውን ልትሰማቸው ዝግጁ እንደሆነች እናት ሊገነዘብዋት ያስፈልጋል፣

እንደእውነቱ ከሆነ በመጨረሻዎቹ አስር ዓመታት ቤተ ክርስትያን የተቻላትን ሁሉ በማበርከት እነኚህን ከመርዳት አልቦዘነችም፣ ከእኔ በፊት በነበሩ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት በመበረታታት በተለያዩ ቍምስናዎችና ሃገረስብከቶች የመፋታትና አዲስ ሕይወት የመጀመር ሰለባ ለሆኑ ክርስትያኖች ላሳዩት እርኝነትና ፍቅር የታከለበት መንፈሳዊ እንክብካቤ ላመሰግናቸው እወዳለሁ፣ ምሥጢረ ቃል ኪዳንን ያፈረሱ እነኚህ ሰዎች በምንም ተአምር የተወገዙ አይደሉም፤ እንደተወገዙም አንመለከታቸውም፣ ሁሌ የቤተ ክርስትያን ክፍል ናቸውና፣

ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓም በሚላኖ በተካሄደው 8ኛ ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ላይ ስለዚሁ ጉዳይ ተጠይቀው ሲመልሱ “ዝግጁ የሆነ መልስ” የለበትም ነገር ግን እረኞች ይህ ችግር ላላቸው ቤተሰብ ሲመሩ ልዩ ጥንቃቄና እውቀትና ጥንቃቄ የተሞላበት ሓዋርያዊ እርኝነት እንዲያካሄዱ አደራ ብለው ነው፣

ከዚህ በመቀጠል የተለያዩ እረኞች/ጳጳሳት በየቦታዎቻቸው ማኅበረሰቦቻቸው የዚህ ችግር ሰለባ ለሆኑት ሁሉ እንዲቀበልዋቸውና የክርስቶስ በመሆናቸው በጸሎት ሊሰኙና ከቤተክርስትያን ጋር እንዲጓዙ ቃለወንጌል በመስማትና በሥር ዓተ አምልኮ በመሳተፍ ለልጆቻቸው ክርስትያናዊ አስተዳደግ እንዲለግሱ ይህንንም ድሆችን በምግባረ ሠናይ በመርዳትና ለፍትሕና ለሰላም በማበርከት እንዲፈጽሙት አደራ ብለዋል፣

ስለመልካሙ እረኛ የሚናገረው የወንጌል ክፍል (ዮሐ 10.11-18) ኢየሱስ ከአባቱ የተቀበለውን ተልእኮ አጠር ባለ መንገድ ያቀርብልናል፣ ይህም ኢየሱስ ሕይወቱን ለበጎቹ ሲል መሥዋዕት ማቅረቡንና ልጆችዋን እንደ እናት ለምትቀበል ለቤተክርስትያንም ከዚህ በቀር ሌላ ምሳሌ እንደሌላት ያስተምረናል፣ በዚህም ቤተ ክርስትያን ሁሉንም ለመቀበል በርዋን ከፍታ ለምትጠባበቅ የእግዚአብሔር አብ ቤት መሆንዋን እንረዳለን፣ በሮችዋ በምንም ተአምር ሊዘጉ አይችሉም፣ “ሁላቸውም በተለያዩ ምክንያቶችና አገባቦች የዚሁ ማኅበር አካል ሊሆኑ ይችላሉ፣ በወንጌል ደስታ ማለትም ኢቫንጀሊ ጋውድዩም ቍ.47 እንደተመለከተው “ቤተክርስያን የአባት ቤት ሆና ለሁላችን አድካሚ ከሆነው የህይወት ጉዞአችን ጋር ቦታ እንዳለን የሚያመለክትነው”

በመልካሙ እረኛ ምሳሌ ሁላችን ክርስትያኖች እርሱን ለመምሰል የተጠራን ነን፣ በተለይ ደግሞ ከእርሱጋር ሊተባበሩ የሚችሉ ክርስትያናዊ ቤተሰቦችን በማጠቃለል እርሱ ራሱ የቈሰሉ ቤተሰቦች ኃላፊነት እንደሚወስድ በመረዳት በእምነት ጉዞ አቸውና በማኅበራዊ ሕይወታቸው እንድንተባበራቸው ይሁን፣ እያንዳንዳችን የመልካሙ እረኛ ምሳሌ በመከተል የተቻለንን ያህል እናድርግ፣ ምክንያቱም መልካሙ እረኛ የእያንዳንድዋን በግ ሁኔታ ስለሚያውቅና ወደር ከሌለው ፍቅሩ ማንም እንዲቀር አይፈልግምና፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.