2015-07-27 15:37:00

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ.፦ ዳግም ነጻነት ለታገቱት ሰዎች ሁሉ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ተለመደው እሁድ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ከውጭና ከውስጥ የመጡ ምእመናን ተቀብለው ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በሶሪያ ያለው ውጥረት መለስ ብለው በማሰብ፣ በተለይ ደግሞ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ፓውሎ ዳሎሊዮ የሚገኙባቸው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ሌሎች ታጋቾች ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ እንዳቀረቡ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

በየዓመት በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ትውልድ አገር ፖላንድ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን ሁሉም በዚህ ልክ ካንድ ዓመት በኋላ በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ የሚሻ በይፋ የሚመዘገብበት ቀን የሚጀመርበት ዕለት መሆኑ ገልጠው፣ በይፋዊ የክራኮቪያ ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን ድረ ገጽ አማካኝነትም በምእመናን ፊት ሆነው ለመሳተፍ በመመዝገብ ወጣት ሁሉ እንዲሳተፍ ጥሪ እንዳቀረቡ ጂሶቲ አስታወቁ።

አባ ዳሎሊዮ የሚገኙባቸው በጠቅላላ በሶሪያ የታገቱት ሰዎች ነጻ እንዲለቀቁ

አባ ዳሎሊዮ ይኸው በአጋቾች እጅ ሁለተኛ ዓመታቸውን የሚያስቆጥሩበት ቀን መቃረቡ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን፣ እኚህ በሁሉም ተወዳጅ የሆኑት ኢየሱሳዊ ካህንና በአጋጆች እጅ የሚገኙት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት ነጻ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርበው፣ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብና መንግሥታት እነዚህ የታገቱት ዜጎች ሁሉ ነጻ እንዲለቀቁ ካለ መታከት ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበው ስለ ታገቱት ሁሉ መጸለያቸው ጂሶቲ አስታውቀዋል።

የሁሉም አገር ወጣቶች በክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንዲሳተፍ

ቅዱስነታቸው ልክ ከአንድ ዓመት በኋላ በፖላንድ ክራኮቪያ ከተማ ሊካሄድ የተወሰነው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በማስታወስ፣ ወጣቶች ሁሉ በዚህ ዓቢይ ዓለም አቀፋዊ መርሃ ግብር እንዲሳተፍ ጋብዘው፥ “2016 ዓ.ም. በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የምሕረት ዓመት የሚከበር ወቅት በመሆኑም የክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በዚህ የምሕረት ዓመት የሚኖር በመሆኑ “ምሕረት የሚያደርጉ ምሕረትን ስለሚያገኙ ደስ ይበላቸው” (ማቴ. 5፣7) በሚል ቃለ ወንጌል የሚመራ እንደሚሆን አስታሰው፣ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበው በዚህ ዕለተ ሰንበት ከዮሓንስ ወንጌል ምዕ. 6 ከቁጥር 1 እስከ 15 የተነበበውን ጠቅሰው፦

ኢየሱስ የንግድ አመክንዮ በነጻ መስጠት በሚለው አመክንዮ ይተካል

ደቀ መዛሙርት በገበያዊ አመክንዮ ሲያስቡ ኢየሱስ ግን መግዛት የሚለውን  በዚያ የመጨረሻው ማዕድ ገዛ እራሱ እንደ እንጀራ በነጻ በመስጠት ከእርሱ ጋር ሱታፌ እንዲኖረን ከሚያደርገው የፍጹም ፍቅር ተግባር ከወዲሁ በማሰብ በነጻ መስጠት በሚለው አመክንዮ እንዲተካ ያስተምራቸዋል። በእኛ ውስጥ የእርሱን ሕይወት እንቀበላለን፣ እንዲህ በመሆኑም የሰማያዊው አባታ ልጆች በመሆንም ወንድማማቾች እንድርጎናል፣ በቅዱስ ቁርባን መሳተፍ ማለት ወደ ኢየሱሳዊው አመክንዮ መግባት ማለት ነው። ተካፍሎ መኖርና በነጻ መስጠት ወደ ሚለው ፍጹም የለጋስነት አመክንዮ የሚያሸጋግር ነው። ስለዚህ ሁላችን ድኾች ነን፣ ድኾች በመሆናችንም በነጻ መስጠት እናውቃለን፣ ሱታፌ ማድረግ ማለት ደግሞ ያንን ከሁሉም ጋር ተካፍሎ ለመኖር የሚያበቃን ጸጋ ከኢየሱስ ማግኘት ማለት ነው።

እያንዳንዳችን ትብብርና ግብረ ሠናይ እንዲትረፈረ ለማድረግ እንችላለን

ኢየሱስ ጥቂቱን ዳቦ ለሁሉም እንዲዳረስ ማድረጉ ስለ ተመለክቱ ብዙዎች ተከተሉት፣ ኢየሱስ ዳቦውን በማብዛት እንዲትረፈረፍ በማድረግ ሁሉንም ሲመግብ እጅግ ለተራበው ሰው የሕይወት ምሉእነት ለገሰ፣ ሥጋዊ እርሃብ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን መጠማት የሕይወት ትርጉምን መራብን ያገላል፣ እውነተኛው መርካትን ያድለናል። በስቃይ በብቸኝነት በድኽነት የተጠቁትን በማየት መተከዝ ሳይሆን ጥቂትም ቢሆን ያለንን ማካፈል። አምላካችን ጥቂቱን ብዙ የሚያደርግ አምላክ ነው።

የምናካፍለው ጊዜ ችሎታ ስጦታ ብቃት ሊኖረን ይችላል፣ ከእኛ ውስጥ አምስት ዳቦና ሁለት አሳ የሌለው ማን ነው? ሁላችን አለን። ታዲያ ጥቂቱ ሕብስትና አሳው በጌታ ፊት እናቅርብ እርሱ ለሁሉም እንዲበቃ ብቻ ሳይሆን እንዲትረፈረም ያደርገዋል። በዓለም ፍቅር ሰላም ፍትህና በተለይ ደግሞ እውነተኛ ደስታን ያጎናጽፈናል። በዚህ በምንኖርበት ዓለም ደስታ አስፈላጊ ነው! እግዚአብሔር ያለንን አናሳው የመተባበር ብቃት በማትረፍረፍ በእርሱ ጸጋ የማደል ተግባር ተሳታፊዎች ያደርገናል ብለው የላቲን ሥርዓት በምትከተለው ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች ቅዱስ እያቄምና ቅድስት ሃና ዓመታዊ በዓል መሆኑ ዘክረው አያቶች ለመጪው ትውልድ ለቤተሰብ ሁሉ ዓቢይ ጸጋ ናችው ስለ አያያቶች ሁሉ እንዲጸለይ ጥሪ አቅርበው ጸሎት መልአከ እዚአብሔር አሳርገው ሐዋርያዊ ቡረኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.