2015-07-27 15:46:00

ዓለም አቀፍ የመጽሓፍ ቅዱስ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 30 እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2015 ዓ.ም. በኮሎምቢያ መደሊን ከተማ ዓለም አቀፍ የመጽሓፍ ቅዱስ ጉባኤ የቃለ እግዚአብሔር- Dei Verbum የአንቀጸ እምነት ድንጋጌ ዝክረ 50ኛው ዓመት በሚል ርእስ ሥር ጳጳሳዊ ቦሊቫሪያን መንበረ ጥበብ አዘጋጅነት የዕብራውያን መልእክት ምዕራፍ አራት ቁጥር 12 “የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነው። ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ ስለታም ነው። ነፍስንና መንፈስን ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ የሚቈራርጥ ነው፣ በልብ ውስጥ የተሰወረውንም አሳብና ምኞት መርምሮ የሚፈርድ ነው” በሚል ቃል አስተንፎ ተመርቶ እንደሚካሄድ የኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያና ትርጉም

በዚህ በኮሎምቢያ ሊካሄድ በተወሰነው ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጉባኤ ድኅረ ቃለ እግዚአብሔር ድንጋጌ የመጽሓፍ ቅዱስ ማብራሪያና ትርጉም፣ ትላንትናና ዛሬ የቅዱስ መጽሐፍ ሥነ ትንተና ሂደት፣ በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ሰፊ ውይይት እንደሚደረግና አስተምህሮ እንደሚቀርብ የገለጠው የኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ አክሎ፣ ሊካሄድ የተወሰነው ዓውደ ጉባኤ የጳጳሳዊ ቦሊቫሪያን መንበር ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ አባ ኹሊዮ ኻይሮ ቸባሎስ ሰፑልቨዳና በዚያ መንበረ ጥበብ የሥነ ክርስቲያናዊ ሰብአዊነት ጥናት ዘርፍ አስተዳዳሪ አባ ጉይለርሞ ለኦን ዙለታ ሳላስ በሚያሰሙት ንግግር እንደሚከፈት አስታወቀ።

ቅዱሳን ጉባኤዎች በመለኮታዊ ግልጸት ዙሪያ

ቃለ እግዚአብሔር አንዱ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የአንቀጸ እምነት ድንጋጌ እ.ኤ.አ. ሕዳር 18 ቀን 1965 ዓመት በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድተኛ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን ሥር፦ የትረደንዚዮ ጉባኤና አንደኛው የቫቲካን ጉባኤ ዱካ በመከተል የተደነገገ በመለኮታዊ ግልጸት ርእሰ ሥር  የተሰጠ የአንቀጸ እምነት ትክክለኛና እውነተኛ ድንጋጌ ሲሆን፣ እርሱም መላው ዓለም የመዳን እቅድ ትክክለኛውና እውነተኛውን ትርጉምን በማዳመጥ እንዲያምን በመታመን ተስፈኛ እንዲሆን ተሰፈኛ በመሆን እንዲያፈቅር፣ እንዲያምን የሚመራ መሆኑ የኮሎምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.