2015-07-27 15:51:00

ኢየሩሳሌም፦ የእስራኤል የጸጥታ ኃይል ወደ አል አቅሳ መስጊድ ጥሶ መግባት


የእስራኤል የጸጥታ ኃይል አባላት ከዚህ ቀደም ፈጽሞ ያልታየ በሙስሊሙ ዓለም ሦስተኛው ቅዱስ ስፍራ ተብሎ ወደ የሚገለጠው አል አቅሳ መስጊድ የፈጸመው ዘልቆ የመግባት ተግባር በጸጥታው ኃይልና በወጣት ፍልስጥኤማውያን መካከል ከባድ ግጭት ማነሳሳቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማርኮ ጉዌራ አስታወቁ።

የእስራኤል የጸጥታ ኃይል ቃል አቀባይ ሚክይ ሮሰንፈልድ የእስራኤል የጸጥታ ኃይል አባላት አንዳንድ ፍልስጥኤማውያን መስጊዱን ተገን በማድረግ ይወረውሩት የነበረውን የድንጋ ውርጅብኝና ጠብ ጫሪ ተግባር ለመግታት በሚል ውሳኔ መሠረት ጥቂት እርምጃ ወደ መስጊዱ ዘልቀው እንደገቡና አንዳንድ ፍልስጥኤማውያን ወጣቶች የእስራኤል የጸጥታው ኃይል እርምጃ በመቃወም በወረወሩት ድንጋይ አራት የጸጥታ ኃይል ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ገልጠው የእስራኤል የጸጥታው ኃይል አባላት አንድም ፍልስኤማዊ ወጣት ለእስር አለ መዳረጋቸው ሲያመልክቱ፣ ሆኖም አንዳንድ የፍልስእጥኤም ድረ ገጾች፣ የእስራኤል የጸጥታ ኃይል አባላት ወደ መስጊዱ ዘለቀው በመግባ አስለቃሽ ጋዝ መልቀቃቸውና አስር ፍልስኤማውያን ለጉዳት ማጋለጣቸው በሚያሰራጩት ዜናዎች ይጠቁማሉ።

የግጭቱ መንስኤ በመስጉዱ አደባባይ ክልል የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች እ.ኤ.አ. በ 70 ከክርስቶስ ልደት በኋላ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ በሮማውያን መውደም ለማሰብ የሚፈጽሙት መንፈሳዊ ዝክረ በዓል ለማገድ ፍልስጥኤማውያን የወሰዱት እርምጃ የቀሰቀሰው ውጥረት መሆኑ የተለያዩ የክልሉ የዜና አውታሮች ይናገራሉ።

የእስራኤል የጸጥታው ኃይል የወሰደው እርምጃ የእስላም ሃይማኖት ሥፍራ የሚያረክስ ነው የሚል የተለያዩ የሙስሊም አገሮች ድረ ገጾች እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. በወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አሪየል ሻሮን በመስጊዱ አደባባይ ክልል የፈጸሙት የጉብኝት ተግባር የቀሰቀሰው ሁለተኛው ፍልስጥኤማዊ ኢንቲፋድ በማስታወስ የተቃውሞ አስተያየት እየተሰነዘረ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.