2015-07-15 16:22:00

የቅድስት መንበር የተራድኦ ማኅበር፦ መልካም ፈቃድና ተግባር


ኢጣሊያ ቀን በቀን የስደተኞች ሕይወት ከሞት አደጋ በማዳን የምትሰጠው ድጋፍ ሁሉም የሚያውቀው ነው። የኢጣሊያ ለሰብአዊ ተባባሪነት ያላት ዝግጁነት ጭምር የሚመሰከር ነው። ሆኖም ተስፋ ያጠቃለለ ትብብር እንዲሆን ሥራ በመፍጠር እድል ትብብርና ሰብአዊ ድጋፍ አማካኝነት ምሉእ ማድረግ እንደሚያስፈልግ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በሚጠናቀቀው በማደግ ላይ ለሚገኙት አገሮች ዓለም አቀፍ የትብብና የድጋፍ ድርጅቶች እያካሄዱት ባለው አውደ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ለጉባኤው ንግግር ያስደመጡት የኢጣሊያ መራሔ መንግሥት ማተዮ ረንዚ ያሰመሩበት ሃሳብ ሲሆን፣ ስለ ዓውደ ጉባኤውና ኢጣሊያ የምትሰጠው ድጋፍ በማስደገፍ የተለያዩ ካቶሊካውያን የትብብርና የተራድኦ ማኅበራት ለሚያቅፈው ለካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ ማርቲና ላይብሽ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በዓለም የሚታየው ድኽነት እርሃብ የመሳሰሉት ችግሮች ለማጉደል እያለም ለማጥፋት የሚወጠኑት እቅዶች ብዙ ናቸው፣ እቅዶቹ የተፈጥሮ አካባቢ ጤንነት ጭምር ያጠቃለለ ነው። ሆኖም እነዚህ ተገቢ እቅዶች ተጨባጭ ለማድረግ የገንዘብ ሃብት ያስፈልጋል፣ በዚሁ መስክ የሁሉም አገሮች ትብብርና የገንዘብ ድጋፍ የማያሻማ ጉዳይ ነው። ድኽነትና እርሃብ መቅረፍ ሓሳብዊ መልካም ፍቃድ ለብቻው መልስ አይሆንም፣ ድኽነትና እርሃብ ማጥፋት የሁሉም ፍላጎት ነው። ሆኖም ተቀባይነት ባለው የልማት እቅድ ተደግፎ እንዲረጋገጥና እቅዱ እግብር ላይ ለማዋል የውጪ እቅድ ያስፈልጋል። ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ በዚሁ መስክ በማነቃቃት ዋና ተወናያን በመሆን ጭምር በሁሉም መድረኮች የሚያስተጋባው ጥሪ ጭምር ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባው ዓውደ ጉባኤ ንግግር በማስደመጡ የከፈቱት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን የልማት እቅድ ተጨባጭ ለማድረግ የወጪ እቅድ ወሳኝ ነው እንድሉ ላይብሽ ገልጠው ለበለጠው ብሩህ መጻኢ የበለጸጉ አገሮችና ድጋፍ ሰጭ አገሮች የየግላችው ፍላጎትና ጥቅም ወደ ጎን በማድረግ የሚሰጠው ድጋፍና ትብብር ኅቡእ የግል ጥቅም ይዞ የሚጓዝ ከማድረግ ፍላጎት ነጻ መሆን አለበት። የተለያዩ አበይት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በሚገኙባቸው ድኾች አገሮች የእነዚያ አገሮች የተፈጥሮ ሃብት የሚጠቀሙና ለዓለም ንግድ የሚያቀርቡ ናቸው በመሆኑም ጥቅም ማካበት ብቻ ሳይሆን የተስተካከለና ተገቢ የግብር ክፍያ መፈጸምና ለሚገኙባቸው ድኾች አገሮች ልማት አቢይ አስተዋጽኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይኽ ጉዳይም የድኾች አገሮች የይገባኛልና የፍትህ ጥያቄ ነው ብለዋል።

መንግሥታት ለትብብርና ድጋፍ በሚያካሂዱት ጥረት ተራው ሕዝብ ጭምር ተሳታፊ መሆን አለበት። ተራው ሕዝብ በተለያየ መልኩ የትብብርና የድጋፍ እቅዶች እብግር ላይ እንዲውሉ ንቁ ተሳታፊ ሆኖ መገኘት አለበት።

እርሃብና ድኽነት ለመቅረፍ ከሚሰጠው የልማት ድጋፍ ጎን የሥራ ዕድል የመፍጠርና የሕንጸት እቅድ ተያይዞ መሄድ ይገባዋል፣ ይኽ ደግሞ ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ከቀጣይ ተመጽዋችነት ሕይወት ያላቀዋል። እርዳታ ማቅረብና እርዳታ የሚያስፈልገው ድኻው የኅብረተሰብ ክፍልና አግሮች ከድኽነት ማላቀቅ የሚል እቅድ ያካተተ መሆን አለበት። ይኽ ዓይነቱ አሠራር ድጋፍ ለሚያቀረበው አገር ጭምር አቢይ ድጋፍ ነው። ምክንያቱም ከዘወትር ድጋፍ አቅራቢነት ተግባር ያላቀዋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.