2015-07-15 16:13:00

የቅድስት መንበር የተራድኦ ማኅበር፦ መልካም ፈቃድና ተግባር


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በኢራን የኑክለይር መርሃ ግብር ዙሪያ የተደረሰው ስምምነት ቅድስት መንበር በአወንታ እንደተመለከተቸውና ከዚህ ጋር በማያያዝም ስምምነቱ በኑክሊየር መርሃ ግብር ላይ ብቻ ሳይታጠር የሚያስጨብጠው ውጤት ለተለያዩ አወንታዊ ስምምነቶች የሚያነቃቃ እንዲሆን የቅድስት መንበር ፍላጎት መሆኑ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ያሳወቁ ሲሆን፣ ስምምነቱ በተመለከተ ጀነቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብትና ክብር በሚከታተለው ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የተደረሰው ስምምነት በዚህ በተለያየ የዓለማችን ክልል በተደጋጋሚና በቀጣይነት በተለያየ መልኩ ዓመጽ በሚታይበት በአሁኑ ወቅት ተስፈኛ መንገድ መጥረግና ሌሎች ጸረ ሰብአዊ የሆኑ ችግሮችና የተለያዩ ውጥረቶች መፍትሄ እንዲያገኙ የሚያበረታታ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታና የደኅንነት ምክር ቤትና በኢራን መካከል የተደረሰው ስምምነት ለሁለቱ ማለትም ለሁሉም የሚበጅ ነው። ስለዚህ ጉዳዩ አቢይ አወንታዊ እርምጃ ነው። ለማንኛውም ዓይነት ችግርና አለ መግባባት ውይይት ብቸኛ መፍትሔ መሆኑ የሚመሰክር ታሪካዊ ሁነት ነው። ዓመጽና ጦርነት መልስ ሊሆን እንደማይችል የሚያረጋግጥ ተግባር ጭምር ነው። ይኽ የተጨበጠው ውጤት በሶሪያ ላለው ዓመጽ መፍሔ እንዲያገኝ ለሚደረገው ጥረት አቢይ ድጋፍ ነው ብለዋል።

ኢራን የውይይቱ አሟይ ተቀዳሚ አካል በመሆንዋ የተካሄደው ውይይት ውጤት ሊያስገኝ በቅቷል። በመካከለኛው ምስራቅ ለሚታየው ውጥረት መፍትሄ ለማፈላለግ ለሚደረገው ጥረት ድጋፍም ነው። የውጥረትና የግጭት መፍትሄ የጋራ መሆን አለበት፣ ካልሆነ አንዳዊ ገጽታ ያለው ሆኖ ሌላው ተገዳጅ የሚያደረግ ይሆናል። እንዲህ ባለ መሆኑ መፍትሔው ለመላ ዓለም በተለይ ደግሞ ለመካከለኛው ምስራቅ ተስፋ የሚያነቃቃ አወንታዊ ውጤት ነው ብለዋል።

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ምክር ቤት የተደረሰው ስምምነት ተቀብሎ ያጸድቀው ዘንድ ተስፋው አለ ይኽ ደግሞ የተገባ የዴሞክራሲ የአሠራር ሂደት ነው። የስምምነቱ ሰነድ የመጀመሪያ ደረጃ ነው። ሆኖም ከብዙ የውጣ ውረድ ዓመታት በኋላ የተደረሰ በመሆኑ ለቀጣይ መቀራረብና ስምምነት ለመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋት ድጋፍ መሆኑ ገልጠዋል።

ኢራን የተከተለችው የውይይት መንገድ ለተለያዩ እስላም አገሮች አብነት ነው። በሺዒዎችና ሱኒዎች ፖለቲካዊና ኃይማኖታዊ ውይይት እንዲኖር የሚያሳስብ፣ የውይይት መንገድ ነው። ግጭትና የግጭት ተወናያን አገሮች ከተለያዩ ከሚደግፉዋቸው አገሮች የሚያገኙት የጦር መሥሪያ ድጋፍ ሞትና ጥፋት ብቻ የሚወልደው ነው፣ ለጦርነት ተወናያን አገሮች አመጽና ግጭት በሚታይባቸው አገሮች ሊሰጥ የሚገባው የላቀው ድጋፍ ወደ ውይይት ማቅረብ ነው።

ቅድስት መንበር የተደረሰው ስምምነት መልካም ፈቃድ መሆኑ በማብራራት ስምምነቱ ገንቢ በሆነ መንገድ ገቢራዊ እንዲሆን ተስፈኛ ብቻ ሳትሆን ሁሉም ለተሟላ ሰላም እንዲጸልይ ጥሪ ታቀርባለች በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አዚህ ላይ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.