2015-07-13 16:15:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስብከት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከአንድ ሚሊዮን በላይ በተሳተፈበት በፓራጓይ ኑ ጉአዙ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፦

“ጌታ ዝናቡን … ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች” (መዝ. 84.13 ተመ.)። ዛሬ በእግዚአብሔርና በሕዝቡ፣ በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ያለው ምጥስጢራዊ ሱታፌ እናከብራለን፣ ዝናብ የእጆቻችን ሥራዎች በሚፈጸምባት በዚህች ምድር ለእግዚአብሔር ኅላዌ ምልክት ነው፣ ይኽ ዓይነቱ ሱታፌና ውህደት ዘወትር ፍሬ ይሰጣል ሕይወት ይሰጣል፣ ይኽን የሚያረጋግጠው እማኔም ዘወትር የምንኖርበት መሬት የሚለውጥ የሚመስን በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ እንተማመን ዘንድ የሚያበቃ አምናለሁኝ ማለት ነው።

ይኽ እማኔ  በማኅበረሰብ በቤተሰብ ውስጥ የሚቀሰምና ቅርጽ የሚይዝ ነው። እማኔውም ኢየሱስን በመከተል ፈጽሞ ለማያታልለው ኢየሱስ ደቀ መዝሙሮቹ ለመሆናችን በብዙዎች ሕይወት ምስክርነት ሆኖ የሚገለጥ ነው። ደቀ መዝሙር በኢየሱስ እንዲታመን የእርሱ ጓደኛ እንዲሆን የኢየሱስ ዕጣ ፈንታና ሕይወት እንዲካፈል በኢየሱስ የተጠራ ነው። “ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን እያውቅምና፣ እናንተ ግን ወዳጆቼ እላችኋለሁ፣ በአባቴ ዘንድ የሰማሁትን ሁሉ ነግሬአችኋለና” (ዮሐ. 15፣15) የዛሬው ወንጌል ስለዚሁ ዓይነት ደቀ መዝሙርትነት ነው የሚናገረው። የክርስቲያን መታወቂያ ወረቀት (የማንነት መለያ) ለይቶ ያቀርብልናል። ክርስቲያን ገዛ እራሱን የሚያቀርብበት የሚያስተዋውቅበትና የሚያረጋግጥበት መለያ ነው።

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን ይጠራል፣ ግልጽና ትክክለኛ የሆነ መመሪያ በመስጠትም ይልካችዋል፣ አልፎ አልፎ ቅጥ የሌለው በቀላሉ ሊተገበር የማይቻል እንደ ምልክትና ትእምርት ብቻ ሆኖ ተመስለው የሚታዩት ሊኖሩት የሚገባቸውን ጠባይና አኳኃን ሁሉ ያቀርብላችኋል። ኢየሱስ ግልጽ ነው። በተቻላችሁ መጠን የሚቻላችሁን አድርጉ፣ ልትከተሉትና ልትኖሩት ሞክሩ ብሎ አይደለም የሚያቀርብላቸው “…ለመንገድም ከበትር ብቻ በቀር እንጀራም ቢሆን ከረጢትም ቢሆን መሐለቅም በመታጠቂያችሁ እትያዙ … ለማረፊያ በሚሰጥዋችሁ ቤትም ግቡ…(ማር. 6፣ 8-11 ተመል.) በማለት ይመክራቸዋል፣ በእውነቱ ይኽ ምክር ፈጽሞ የማይቻል ሆኖ ሊሰማን ይችላል።

ኢየሱስ በሰጣቸው ትእዛዝ የተጠቀመባቸው እንጀራ ገንዘብ ከረጢት በትር ነጠላ ጫማ እጀጠባብ እንዲሁም ብዙን ጊዜ በክርስትና ሕይወት የምንዘነጋው መስተንግዶ የሚለው ቃል እናገኛለን። ይኽ ቃል ለክርስትያናዊ መንፈሳዊነት ማእከል ነው። በሚያስተናግዱዋችሁ ቤት ግቡ፣ ክርስቲያን ማስተናገድና መቀበልን የሚኖር ነው።

ኢየሱስ ሕግና ትእዛዝ አሸክሞ እንደ ኃያላን እንደ ባላባት እይንደለም የላካቸው፣ ባንጻሩ የክርስትና መንገድን ነው የሚያመለክትላቸው። ይኽ መንገድም የልብ መለወጥ የሚል ነው። የገዛ እራስ ልብ መለወጥና የገዛ እራስ ልብን ለውጦ የሌላውን ልብ ለመለወጥ ማስተናገድ። ከራስ ወዳድነት በገዛ እራስ ከመዘጋት ከግጭትና ከውጥረት ከመለያየት ከመታበይ አመክንዮ ወደ የሕይወት በነጻ መስጠት ወደ ሚለው የፍቅር አመክንዮ መሸጋገር የሚል ነው። ከበዳይነት አንገላታችነት ከጨቋኝነት ሌላውን እንዳሻህ መቆጣጠር ከሚለው አመክንዮ ወደ አስተናጋጅነት ተቀባይ መሆን ስለ ሌላው ማሰብ ወደ ሚለው አመክንዮ መለወጥ የሚል ነው።

እነዚህ ሁለት አመክንዮዎች ሕይወትንና ተልእኮን ለመኖር የሚመረጡ ናቸው። ሁለቱን ማጣመር አይቻልም። ብዙውን ጊዜ ሁለተኛው አመክንዮ ሳይሆን አንደኛው አመክንዮ ገዛ እራስ ማእከል ማድረግ የሚለው የራስ ወዳድነት አመክንዮ አማካኝነት ሕይወትናን ተልእኮን እንኖራለን፣ እቅድና መርሃ ግብር በሚል መሠረት ተልእኮን እንኖራለን፣ ሌሎችን በምንደረድረው ቃልና በምናቀርባቸው የውይይት ርእሰ ጉዳዮች አማካኝነት በገዛ እራሳችን ስልትና ጥበብ ሌላውን አጠማዞ በሰብአዊ አታላይነት አማካኝነት ለመለወጥና ለመማረክ እንሞክራለን፣ በዛሬው ወንጌል ጌታችን በግልጽ ይናገራናል፣ ልንከተለው የሚገባንን መንገድና አመክንዮ በቃልና በሕይወት መስክሮልናል እርሱም ወንጌላዊ አመክንዮ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሌላውን ሊቀበል ማስተናገድ የሚኖር በተለይ ደግሞ ለተናቁት በተለያየ ችግር ለተጠቁት ማስተናገድና መቀበል የሚችል የክፍት ልብ እናት ነች። ሌላውን የምትቀበል ቤት እንድትሆን የፈለገውም ኢየሱስ ነው። አስተናጋጅ ሌላውን ተቀብሎ የማስተናገድ ባህል፣ ተስፋ የቆረጠው የቆሰለውን ተቀባይነት እንዳገኝ ሆኖ እንደ ቤቱ ሊኖርበት በሚቻለው መጠለያ ተቀብሎ መፈወስ፣ ስለዚህ በሮችን ሁሌ ክፍት ማድረግ፣ በተለይ ደግሞ የልቦቻችን በሮች ክፍት ማድረግ።

መስተንግዶ ለተራበው ለተጠማው ለመጽአተኛው ለተራቆተው ለታመመው ለታረዘውና ለእስረኛ (ማቴ. 25፣ 34-37 ተመል.) በደዌ ለተጠቃው በአካል መስለል ለተጠቃውን የእኛ አመለካከት የሌለው፣ እምነት ይኖረው ወይንም እምነቱን ያጠፋ በእኛ ምክንያት እምነቱ ያጠፋ፣ የሚሰደደውን በሥራ አጥነት የተጠቃውን ሁሉን ማስተናገድ። የምንኖርባት ምድር እጅግ ሃብታም የሚያደርጋት የባህል ብዙኅነት ማስተናገድ፣ ኃጢአተኛውን ሁሉ ማስተናገድ፣ ኃጢአተኞች መሆናችን አንርሳ።

ከኃጢአታችን በፊት እጅግ የሚጎዳ ቀስ እያለ ድምጹን ያጠፋ የጨለመ ዝምታ የሚወልድ ስቃይ አለ፣ ይኽ ጨለምተኛው ዝምታና ብቸኝነት ቀስ እያለ በልባችን ቆፎው የሚያርኖ የክፋት ተግባር የሚወልድ ነው። ሕይወታችንና ልባችንን የሚመነዥግ። የብቸኝነት ሕይወት፣ ብቸኝነት እንዲከሰት የሚያደርጉ ምክንያቶች ብዙ ናቸው። ከሌሎች ከእግዚአብሔር ከማሕበርሰብ የሚነጥሉ፣ በገዛ እራሳችን ውስጥ እንድንዘጋ የሚያደርጉ አኗኗር የሚወልድ ነው። ቤተ ክርስቲያን ግን ወንድማማችነት የሚኖርባት እናት ነች። ተቀባይና አስተናጋጅ ወንድማማችነት እግዚአብሔር አባት ለመሆኑ እጅግ የላቀ ምስክርነት የሚኖርባት ነች። “እርስ በእርሳችሁ ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ሁሉ ያውቋችኋል” (ዮሐ. 13፣35 ተመል.)።

እንዲህ ባለ መልኩም ኢየሱስ አንድ አዲስ የምሉእ ሕይወት የውበትና የእውነት የምሉእነት አድማስ ያቀርብልናል። እግዚአብሔር አድማስን ፈጽሞ አይዘጋም፣ የልጆቹ ስቃይና ሕይወት ቸል አይልም፣ በዚህ ሳይታጠርም አንድ አዲስ አድማስ ይከፍትልናል፣ እርሱም ልጁን ልኮልናል፣ ስጣታ በማድረግ አቅርቦልናል፣ ኢየሱስ ያንን ድምጽ የለሽ የስቃይ ዝምታ የሚወልደውን ብቸኝነት ያግሎታል።

በአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮአችን ስንደክም ኢየሱስ የሚሰጠንን ጥልቅ ሕይወት እናስተውል (ወንጌላዊ ኃሴት 265 ተመል.)።

መስተንግዶን ግድ ለማለት አይቻልም፣ በግድ አስተናግደኝ ብሎ ነገር የለም፣ መስተንግዶ አስተናጋጅነት ድኾች የመሆናችንና የነጻነታችን ምልክት ነው። ስለዚህ መስተንግዶ ግዳጅ ሳይሆን ሕይወት ነው። ቁምስናዎቻችን ቤተ ጸሎቶቻችን የተከፈተ በር ያላቸው ሆነው ማየቱ እንዴት ደስ ያሰኛል፣ እኛና እግዚአብሔር የምንገናኝበት ቅዱስ ሥፍራ በመሆናቸውም ዘወትር የተከፈተ በር ሊኖራቸው ይገባል። እንደ ማርያም የሚያስተናግድ የማርያም እናትነት መንፈስ የሚኖርባቸው ቅዱሳን ሥፍራዎች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን እንደ ማርያም እናት ነች። ሌላውን ለመቀበልና ለማስተናገድ የእግዚአብሔር ቃል ለማስተናገድ ተግባር አብነትም ማርያም ነች።

መሬት የሚዘራውን ዘር የሚቆጣጠር ሳይሆን የሚያስተናግድ ነው። ዘሩን ተቀብሎ የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ በማቅረብ ፍሬ እንዲሰጥ ያደርገዋል። “ጌታ ዝናቡን … ምድርም ፍሬዋን ትሰጣለች” (መዝ. 84.13 ተመ.)። በዚህ መንፈስ ሌላውን መቀበልና ማስተናገድ በማርያም አብነት እግብር ላይ እናውል። እንዲህ ይሁንልን።








All the contents on this site are copyrighted ©.