2015-07-03 17:49:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ ከሓምሌ 5-13 ቀን 2015 ዓም በላቲን አመሪካ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከተነገ ወዲያ እሁድ እ.አ.አ ሓምሌ 5 ቀን  2015 ዓም እስከ ሓምሌ 13 ቀን በላቲን አመሪካ የሚታወቀው የደቡብ አመሪካ ክፍል ሶስት አገሮች ውስጥ ሓውጾተ ኖልዎ ወይንም ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ሲመለከት በኤኳዶር ከሓምሌ 5-8 ቀን  በቦሊቭያ ከሓምሌ 8-10 ቀን እንዲሁም  በፓርጉዋይ ከሓምሌ 10-12 ቀን 2015 ዓም እንደሆነ ተገልጠዋል፣

የቅድስ መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ይህንን የዓለም ክፍል ማለት ላቲን አመሪካን የተስፋ አህጉር ሲሉ የሰየምዋት ሲሆን ቅዱስነታቸው በዚሁ ሓዋርያዊ ጉብኝት ሰባት የአየር በረራዎችና ሃያ ሁለት ንግግሮችና ስብከቶች እንደሚያደርጉ አመልክተው በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ እንደሚጠባበቃቸው በተለይ በመጨረሻ በፓራጉዋይ በሚያደርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እስከ ሁለት ሚልዮን ምእመናኖች ተሳታፊ ይሆናሉ የሚል ግምት እንዳለም ገለጠዋል፣  ይህ የር.ሊ.ጳ ጉዞ በትረ ሥልጣን ዘመንበረ ጴጥሮስ ከያዙ ወዲህ ዘጠነኛ ዓለም አቀፍ ጉዞ ሲሆን እንደመሪ ቃል የሚጠቀሙትም ቅዱስ ወንጌልን መስበክ የሚሰጠን ደስታ የሚል ሲሆን ብፁዕነታቸው እንዳመልከቱትም ይህንን እጅግ ረዥም ጉዞ ለመረዳት ባለፈው ታሕሣስ 12 ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጓዳሉፐ እመቤታችን ድንግል ማርያም ክብረ በዓልን አስመልክተው ያሉትን ማስታወስ ያስፈልጋል፣ ያኔ ቅዱስነታቸው ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይህንን አህጉር በሚመለት ያሉትን እንደገና በመድገም ‘ላቲን አመሪካ የተስፋ አህጉር’ ይህንን ያሉበት ምክንያት ሲገልጹም “ከዚህ አህጉር ክርስትያናዊ ባህልንና ሲቪላዊ ግስጋሴን አጣምሮ የሚይዝ አዲስ የሥልጣኔ ሞደል ይጠበቅበታል፣ ይህም ፍትሕና እኩልነትን ማእከል ያደረገ ዕርቅን በማስቀደም ሳይንሳዊና ተክኖሎጂካዊ ሥልጣኔን ከሰው ልጆ ጥበብ ጋር በመዋሃሃድ እንዲሁም በብዙ ሥቃይ የተገኘው ተስፋቸውን በደስታ ሊለውጡ ይችላሉ” ብለው ነበር፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአፓረሲዳ ሰነድ አዋጆችም ቅዱስነታቸው የሚያራምዱትን ግብረ ተልእኮ ስለሚመሳሰል ማለትም የጸጋ ቀዳምነት የእግዚአብሔር ምሕረትና ሓዋርያዊ ብርታት የሚሉ ይገኛሉ፣ ራሱ የላቲን አመሪካ አህጉር በእንቅስቃሴ ያለ በመሆኑ በባህልም ይሁን በፖሎቲካ በምጣኔ ሃብትም ይሁን በማኅበረሰብ ብዙ ለውጥ ሊያመጣ የሚጠበቅበት በመሆኑ እውነትም የተስፋ አህጉር ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.