2015-06-24 19:00:00

እ.አ.አ ጥቅምት ወር ላይ 2015 ለሚካሄደው አጠቃላዩ የጳጳሳት ሲኖዶስ የሥራ መመርያ


አምና በጥቅምት ወር በቫቲካን በተካሄደው ልዩ የካቶሊካውያን ጳጳሳት ሲኖዶስ የጀመረውን ስለቤተሰብ የሚውያይ የጳጳሳት ሲኖዶስ ለአጠቃላዩ ሲኖዶስ ለማዘጋጀት ሲደረግ የነበረው ጥናት ትናንትና ኢንስትሩመንቱም ላቦሪስ መወያያ ሰነድ በማቅረብና ለዘመደ አዳም ሁሉ በተለይ ደግሞ በመንፈሳዊና ሥጋዊ ችግር ውስጥ ያሉትን ቤተ ሰቦች ተስፋ መስጠት እንዳለበጥ ገልጠዋል፣

ስለቤተሰብ ሲታሰብ ያሉ ተግዳሮች የቤተሰብ ጥሪና ተልእኮን ስለሚያጠቃልል እፊታችን ጥቅምት ወር ሊካሄድ ለታቀደው ለ14ኛው መደበኛ አጠቃላይ የጳጳሳት ሲኖዶስ መወያያ እንዲሆን ትናንትና የቀረበው ኢንስትሩመንቱም ላቦሪስም ከእነዚህ መስመሮች የወጣ አልነበረም፣ እንደሚታወቀው ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በተካሄደው ልዩ የጳጳሳት ሲኖዶስ አበው ያቀረብዋቸውን አደራዎችና ሓሳቦችን ቅዱስነታቸው ተቀብለው በመላው ዓለም ለሚገኙ ካቶሊካውያን እንዲወያዩባቸውና ጥያቄዎች ካልዋቸው በየክልላቸው ተወያይተው እንዲያቀርቡ በወሰኑት መሠረት ይህ ትናንትና የቀረበው መወያያ ሰነድም እነዚህን ሁሉ ያካተተ ነበር፣ ስለዚህ ይህ መንሻ በመሆኑ ከዜሮ እንደማይጀምር ብሩህ በመሆኑ በሰነዱ የቀረቡ ነጥቦች ባለፈው ልዩ ሲኖዶስ የቀረቡትን ጥያቄዎች እንዲያው ያኔ ብዙ ክርክር ያነሱ ቃልኪዳን አፍርሰው ሌላ ትዳር የመሠረቱ ቅዱስ ቍርባን ሊቀበሉ ምን ይደረግ የሚሉና አንገብጋቢ የሆኑ የግብረሰዶማውያን ሁኔታን የሚዳስሱ ቍ.52 53 እና 54 ሳይቀሩ በሰነዱ ቀርበዋል፣

ጠቅለል ባለ መንገድ ሰነዱ ቤተሰብ በአንድ ወንድና ሴት የሚቆም መሆኑን አበክሮ በመግለጥ በተለያዩ ምክንያቶች የቆሰሉትን ቤተሰቦች ደግሞ ልዩ እንክብካቤ መደረግ እንዳለበት ያመለክታል፣ በምዕራቡ ዓለም እየጐላ የመጣው በአንድ ዓይነት ጾታ ባላቸው ሰዎች ወይንም ሴቶች የሚደረገው ትዳር በቤተክርስትያን ምንም ዕውቅና የማሰጠው ሆኖ ከነጭራሹ ቤተሰብ ብሎ መናገርም የማይገባ ነው፣ ቤተሰብ በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚቆም ለፍቅርና ለፍሬ እግዚአብሔር የባረከው ነው ይላል፣

የዘመናችን ችግሮች ብዙ በመሆናቸው መጠን በቤተሰብ ላይ የሚያሳድሩት ጫና ቀላል አለመሆኑ፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ብተለያዩ ምክንያቶች የቃል ኪዳን ብቃትን የሚመረምሩ ብዙ ጊዜ በመውሰዳቸው የሚያጥሩበት መንገድ መፈለግ እንዲሁም በጉድፍቻ ልጅ ለማሳደግ የሚፈልጉ ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ሲገልጥ በዘመናችን እንደ ወረረሽኝ በተለቪዥንም ይሁን በኢንተርነት ከሚደረገው ፖርኖግራፊ በተለይ ደግሞ ለሴቶችና ለሕጻናት የጾታ ምዝመዛ ስለሚያስከትል መወገድ ያለበት መሆኑን ይገልጻል፣

የሰነዱ ይዘት አብዛኛው በመላው ዓለም ከሚገኙ ካቶሊካውያን ረኪበ ጳጳሳት ቤተሰቦች ዩኒቨርሲቲዎችና ክልላዊ ስብሰባዎች የተሰበሰቡ ናቸው፣ ይዘቱም በሶስት ይከፈላሉ፣ አንደኛው የቤተሰብ ተግዳሮችን በደምብ ማዳመጥ፤ ሁለተኛው የቤተሰብ ጥሪን በደምብ አጥንቶና አስተንትኖ ምንነቱን ማወቅ፤ ሶስተኛው ደግሞ የቤተሰብ ተልእኮ ዛሬ የሚል ነው፣

ሰነዱ በአንደኛው ነጥብ የሚያተኵርበት በቤተ ክርስትያን በቃል ኪዳን የሚፈጸሙና በማዘጋጃ ቤት የሚፈጸሙ ትዳሮች በቁጥር እየቀነሱ መሆኑ በአንጻሩ ደግሞ መለያየት መፋታትና ልጅ አለመውለድ እያደጉ መሆናቸውን ሲሆን በተለይ ደግሞ ወጣቶች ትዳር ላለመመስረት ያላቸውን ፍራቻ አስወግደው ትዳር የሚመሠረቱበት ባህል እንዲፈጠር ያሳስባል፣ ባዮሎጂካዊ ጥናት ብቻ ሳይሆን የትዳር ሁኔታን በሥነ ሰብአዊ እና ባህላዊ ጥናትን ጠለቅ ባለመንገድ በማድረግ ትዳር በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች መካከል የሚቆም መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል አለበለዚይ ይህንን በማውገድ ራሱ ችግር የሚፈጥር እንጂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም በማለት የሲኖዶሱ አባቶች ጉዳዩን በጥብቅ እንዲያጠኑት ያሳስባል፣

በሌላ በኩል ደግሞ በዘመናችን ሰው ሰራሽ የሆኑ ነገሮች ትዳርን እያቆሰሉና እየበታተኑ ስለሆነ የአብራክ ፍሬ የሆኑ ልጆቻችን እጓለማውታ ሆነው እንዲቀሩ የሚያደርጉ ቤተሰብን የሚበትኑ ጦርነት ስደት የዕፀፋርስና የአልኮል ጥገኝነት ሥራ አጥነት ድህነት አምልኮ ንዋይ ተጠቅሞ የመጣል ባህል ናቸው፣ የዚህ ሁሉ ሰለባ የሚሆኑ ልጆቻችን ናቸው፣ በተጨማሪም ለሽማግሌዎችና ለአካል ጉዳተኞች ልዩ እንክብካቤ በማድረግ ስደተኞችን ልዩ ሐዋርያዊ ግብረተልእኮ በማቋቋም መርዳት ያስፈልጋል፣

በቤተሰብም ይሁን በማኅበረሰብ የሴት ልጅ ቦታ ወሳኝ ስለሆነ በሚገባ ተጠንቶ የሴት ልጅ በማኅበረሰብ ተገቢ ቦታዋ እንዲሰጣት ይሁን ይላል፣

በሁለተኛው ክፍል ሰነዱ የሚያቀርበው ዋነኛ ነጥብ ምሥጢረ ተክሊል የእግዚአብሔር ስጦታ በመሆኑ እስከ ሞት የማይፈታ ምሥጢር መሆኑ እንጂ ምንም ዓይነት ጫና እንደማይፈጥር ይገልጣል፣ ይህ ምሥጢር ለሁለቱ ባለቃልኪዳን የፍቅር መተሳሰርያ ልጆች በመውለድ ዘርን ይቀጥላል፣ በምሥጢረ ተክሊል አንድ የሆነች ቤተሰብ ታናሽ ቤተክርትያን በመሆን የስብከተወንጌል መነሻም ናት፣ ቤተ ክርስትያንም ቤተሰቦችን በችግር ግዜም ይሁን በሥቃይ ለሚጐኙ እጐናቸው ሆና እንትድረዳቸው ይሁን፣ እንዲህ በማድረግ ቤተሰብ ለሚያምኑት ወንጌል አለምንም ፍራቻና ኃፍረት ሊመሰክሩ ይችላሉ፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ በእግዚአብሔር ዕቅድ ቤተሰብ ግዳጅ ሳይሆን የእግዚአብሔር ስጦታና ጸጋ መሆኑን መገንዘብና መመስከር ያስፈልጋል፣

ሰነዱ በሶስተኛው ክፍል ቤተሰብን እንዴት አድርገን መዘጋጀት ማስተማርና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ እንዳለብን በዚህም ተስፋን አለምንም ማቅማማት ለሌሎች ማስተላለፍ እንዳለብን ይገልጣል፣ ወላጆች በልጆቻቸው እድገትና ትምህርት ኅሊናዊ ኃላፊነት እንዳላቸው በመገንዘብ ካለወላጆች ፍቃድ ምንም ዓይነት ትምህርት በግድ ለልጆች መሰጠት እንደሌለበትም ያሳስባል፣

በመጨረሻም ክርስትያኖች የዓለም ብርሃንና ጨው እንደመሆናቸው መጠን በሁሉ ማኅበረሰባዊ እንቅስቃሴዎች መካፈልና መመስከር እንዳለባቸው ሲያመለክት በተለይ በፖሎቲካና ሌሎች ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች በመሳተፍ ቤተሰብን መንከባከብና መርዳት እንዳለባቸው ያመለክታል፣

አለምንም ቃልኪዳን ተሰባስበው ለሚኖሩ እንዲሁም እንዲሁም ትዳር አቍመው እንደቤተሰብ ለሚኖሩትም ወደ ምሥጢረ ተክሊል እንዲደርሱ መርዳትና መበረታታት እንዳለባቸው አደራ ይላል፣

በሌላ በኩል ደግሞ በቃል ኪዳን በምሥጢረ ተክሊል ትዳር አቁመው የተፋቱና እንደገና ትዳር ላቆሙ በሚመለከትም በተቻለ መጠን ወደ የመጀመርያ ትዳራቸው እንዲመለሱ ጥንቃቄ በታከለበት መንገድ መርዳት እንደሚይስፈልግ ያሳስባል፣ ሁላቸው ይቅርታና ምሕረት ለመስጠትና ለመቀበል ባለመብት ናቸው፣ በተለይ ግን በመለያይትና በመፋታት ሳቢያ ሰለባ የሚሆኑ ልጆች ስለሆኑ ለእነዚህም ልዩ እንክብካቤ ያስፈልጋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከቃል ኪዳን ውጭ ያሉ እንደገና ወደ ምሥጢረ ቍርባን ለመቅረብ ለሚፈልጉና ሌላ ችግር ላላቸው ቤተሰቦች ለመርዳት ካህናት ለምክርና ለእንክብካቤ ብርቱ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ያመለክታል፣

በቃል ኪዳን ዙርያ የሚታየው ሌላ ነጥብ ደግሞ ቃል ኪዳንን በተለያዩ ምክንያቶች ኢባቁዕ ለማለት የሚደረጉ ጥናቶችና ሰበካዊ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቶች ለሁሉም በነጻ የሚደረግበትና ከማንኛው መጠራጠር ነጻ መሆን እንዳለባቸው ያሳስባል፣

ቤተክርስትያን በሥርዓተ አምልኮዋና ሐዋርያዊ እረኝነት እስካሁን በምትከተለው ተልእኮ ቃል ኪዳንን ትተው ለሄደው እንደገና ሌላ ትዳር የመሥረቱ ሰዎች ከምሥጢራት በተለይ ደግሞ ከምሥጢረ ቍርባን እንደተከለከሉ ነው፣ ይህን በተመለከተ የሲኖዶስ መወያያ ሰነዱ ማለት ኢንስትሩመንቱም ላቦሪስ እንዲህ ይላል፣ መሠረታዊው ነገር ለሁሉም የሚሆኑ የእረኝነት መመርያዎች መስጠት ማለትም ማንም ከቤተክርስትያን አገልግሎት የተገለለ ሆኖ እንዳይሰማው ማድረግ ሲሆን በተለይ ደግሞ ተለያይተው እንደገና ሌላ ትዳር የመሠረቱ ቤተሰቦች ጉዳይ በሥርዓተ አምልኮም ይሁን በእረኝነት እንዲሁም በትምህርትም ይሁን በፍቅር ሥራ እንደገና መጠናት አለበት፤ ምክንያቱም አንድም ከቤተ ክርስትያን እንደተባረረና ከቤተ ክርስትያን ውጭ ሆኖ እንዳይሰማው፣ ይህንን በተመለከተ ሲኖዶሱ በደምብ አጥንቶ መሪ ቃል እንዲሰጥ ነው፣ በሰነዱ ሰፍሮ እንዳለው ከቃል ኪዳን ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ወደ ቅዱስ ቍርባን ለመቅረብ የጸጸት ጉዞና የንስሓ ሁኔታዎች በጳጳስ መሪነት ተጠንቶና የቃለ ኪዳኑ ኢበቋዒነትም እግምት ውስጥ ተወስዶ እንዲሁም ራስን ተቆጣጥሮ በተዓቅቦ የመኖር ሁኔታዎችን በመመልከት ውሳኔ መወሰድ የሃገረስብከቱ ጳጳስ ኃላፊነት ቢሆንስ የሚል ሓሳብም ያቀርባል፣

በክርስትያኖችና በሌላ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ስለሚደረገው ቃልኪዳንም አስፈላጊ ሕጋጋት ማቅረብ እንደሚጠበቅ እንዲህ በማድረግም አንዱ ሌላውን ለግላዊ ሃይማኖታዊ ጉዞው እንቅፋት ላይሆነው ይችላል፣ በማለት ከመጥመቅ በምሥጢረ ቅዱስ ቍርባን እስከ መሳተፍ ሊደረጉ የሚገባቸውን ጥርት ባለ መንገድ ሕጎች እንዲኖሩ ያሳስባል፣

በመጨረሻም ሕይወት ከመጸንስ ጀምሮ እስከ ባህርያዊ ሞት ድረስ ተገቢ እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋትና ወላጆች ልጆቻቸውን እመረጡበት ትምህርት ማስተማር ኃላፊነታቸው እንደሆነ በማመልከት የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ትምህርቶችን በመጥቀስና እ.አ.አ ታሕሳስ 8 2015 የሚጀመረው የምሕረት ዓመትም ለዚሁ ሲኖዶስ የተስፋ ብርሃን እንዲሆነውና ሁሉንም በምሕረት ዓይን በመመልከት እንዲደረግ አደራ በማለት ይደመድማል፣     








All the contents on this site are copyrighted ©.