2015-06-20 12:31:00

“Laudato si’ - ይሴባሕ”፣ አናባቢ


“Laudato si’ - ይሴባሕ”፣ አናባቢ

ይኽ ጽሑፍ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውዳሴ ላንተ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት የሚያቀርበው ጥልቅ መልእክት በሙላት ለመጨበጥ እንዲቻል የሚያገለግል መሣሪያ ነው። እያንዳንዱ የዚህ ጽሑፍ ገጽ ለእያንዳንዱ ምዕራፍ የሚወክል፣ ዓላማው የሚገልጥ፣ አንዳንድ ቅዉም ሃሳቡንም የሚያቀርብ ነው። በቅንፍ የሚቀመጡት ሃሳቦች ወደ ዓዋዲው መልእክቱ ያሚሸኙ ናቸው። በመጨረሻው ገጽ የዓዋዲው መልእክት ማውጫ ይገኛል።

ጠቅላል ባለ አመለካከት

“ከእኛ በኋላ ለሚመጡት፣ በማደግ ላይ ለሚገኙት ሕፃናት ምን ዓይነት ዓለም ነው ለማስተላለፍ የምንሻው?”(160)። ይኽ ጥያቄ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አሳቢነት ለተደረሰው የዓዋዲው መልእክት እንኳር ነው። በመቀጠልም ይኽ ጥያቄ ለየት በማድረግ ምኅዳር ብቻ የሚመለከት አይደለም፣ ምክንያቱም ጥያቄው በከፊል አገላለጥ የሚያቀርበው ጉዳይ አይደለምና”፣ ስለዚህ ይኽ ጥያቄ ደግሞ ስለ ኅልውና ወደ ሚመለከተውና በማኅበራዊ ሕይወት ወደ ተመሰረተበት እሴት ይመራናል፣ “ወደ ዓለም የመምጣታችን ፍጻሜ ምንድር ነው? የሥራችንና የትግላችን ዓላማ ምንድር ነው? እኛ መሬትን ለምን እናስፈልጋታለን?”፣ “እነዚህን ጥያቄዎች የማናቀርብ ብንሆን ኖሮ - ቅዱስ አባታችን ይላሉ - ስለ ምኅዳር በተመለከተ በሃሳብ መጠመዳችን ምንም አይነት መንስኤና ክትለት ባልኖረው ነበር።

ዓዋዲው መልእክቱ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ውዳሴ (ክብር) ላንተ ጌታዬ “Laudato si’, mi’ Signore የተሰኘው የምህለላ ርእስ በመውሰድ ያ የፍጥረት ማኅሌት መሬት የሁላችን የጋራ ቤት መሆንዋ ያስታውሰናል፣ መሬት “እንደ እህት ከእርሷ ጋር ኅላዌን የምንቋደስ፣ በእቅፏ እንደምታኖረን ውብ እናት” (1) ነች። እኛም ለገዛ ራሳችን መሬት ነን (ኦሪ. 2፣ 7 ተመልከት)። መላ ሰውነታችን በፈለክ አካላት የተገነባ ነው። ያ እስትንፋስ የሚሰጠንም አየርዋ ነው። የእርሷ ውኃም ኅይው ያደርገናል ያረካናልም”(2)።

በአሁኑ ሰዓት መሬት ለበደል ለዝርፍያ ተዳርጋ ይኸው ሰቆቃዋ ታሰማለች ስቃይዋንም ከእነዚያ በዓለም ከተተዉት ጋር ሆኖ ይስተጋባል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም እነርሱን እናዳምጣችውም ዘንድ ያሳስቡናል፣ ሁላችንና እያንዳንዳችን፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ፣ ክልላዊ ማኅበረሰብ፣ አገሮችና ዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ፣ ለአንድ ሥነ ምኅዳራዊ ለውጥ መቀዳጀት ይማጸናሉ። ይኽ ደግሞ እንደ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አነጋገር ውበትን ግምት እንሰጥ ዘንድና የሁላችን “የጋራ ማደሪያ የሆነውን ለመንከባከብ” ለሚደረገው ጥረት አካሄዳችን እንለወጥ እንዳሉት አገላለጥ ነው። በተመሳሳይ መልኩም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም “ሰለ አካባቢ የሚመለከት ተፈጥሮን የመንከባከብና እጅግ አሳዛኝ በዓለምና በፈለክ ላይ እየደረሰ ስላለው ሁነት የሚገነዘብ ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው አስተዋይነት የተካነ በሳል ቅንነት እንዳለም ይገነዘባሉ (19)። ስለዚህ በመላው ዓዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት ተቀባይነት ያለው ተስፈኛ እይታ በማቅረብ ለሁሉም ግልጽና ተስፋ የተሞላው መልእክት ያስተላልፋሉ፣ “አሁንም የሰው ልጅ የሁላችን የጋራ የሆነውን ቤት ለመገንባት ብቃት አለው” (13)፣ “የሰው ልጅ አሁንም የአወንታዊ ገላጋይነት ሚና ብቃት ያለው ነው” (58)። “ሁሉም ባክኖ አልቀረም ምክንያቱም ሰብአዊ ፍጥረት ከፍ ላለ ውድቀት ብቃት ያለው ቢሆንም ቅሉ ይኸንን ሁሉ ተሻግሮ መልካም ወይንም ውድቀት ለመምረጥ ዳግም የመመለስ ብቃት አለው” (250)።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ክርስቲያኖች ለየት ባለ መልኵ በፍጥረት ዘንድ ያለው ኃላፊነታቸውና በተፈጥሮና በፈጣሪ ፊት ያለባቸው ግዴታ የእምነታቸው ክፍል መሆኑ ይገነዘባሉ” (64) የተሰኙትን የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቃላት ዋቢ በማድረግ መልእክታቸው ለካቶሊክ ምእመናን በቀጥታ የሚያስተላልፉ ቢሆንም ቅሉ “የሁላችን የጋራ ቤት በሚመልከት ርእሰ ጉዳይ ከሁሉም ጋር ለመወያየት ሃሳቡን ያቀርባሉ” (3)፣ ውይይት የተሰኘው ቃል በዚህ ሰነድ በተደጋጋሚ በተከተል ተመልክቶ ይገኛል፣ በምዕራ 5 ችግሮችን ለመግጠምና መፍትሔ ለይቶ ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት መሣሪያ ሆኖ ይገለጣል። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገና ከመጀመሪያ “ሌሎች አቢያተ ክርስቲያንና ማኅበረ ክርስቲያን - እንዲሁም ሌሎች ሃይማኖቶች - ሥነ ምኅዳር ርእስ ዙሪያ ያለባቸው ጥልቅ ስጋትና ስለ ጉዳዩ በተመለከተ ያቀረቡት የላቀው አስተንትኖ ያስታውሳሉ (7)። እንዳውም ክቡር የውህደት ፓትሪያርክ በርጠለመዎስ በዚሁ ዘርፍ የሰጡትን አስተዋጽዖ በቁጥር 8 እና 9 በስፋት በመጥቀስ፣ በግልጽ አቢይ ግምት እንደሰጡበት ተመልክቶ ይገኛል። ባጠቃላይ ር.ሊ.ጳ. በግልም ሆኖ በማኅበር በመታቀፍም፣ የመንግሥት ተቋሞች ጭምር በሥነ ምኅዳር ዙሪያ አቢይ ጥረት የሚያደርጉት ተቀዳሚ ተወናያን የሆኑትን ሁሉ “ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የሥነ ምርምር ሊቃውንት፣ የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ሊቃውንትና ማኅበራዊ ድርጅቶችም ጭምር በዚሁ ጉዳይ በተመለከተ የቤተ ክርስቲያን አስተሳሰብ ሃብታም እንዲሆን ማድረጋቸው እውቅና በመስጠት አመስግነው (7)፣ ሁሉም “ሃይማኖቶች ለአንድ ምሉእ ሥነ ምኅዳርና ለሁሉም ሰው ዘር የተሟላ እድገት በተመለከተ የሚሰጡት አስተዋጽዖ እውቅና እንዲሰጥበት ይጋብዛሉ (62)።

የዓዋዲው መልእክት ውጥን በ ቁጥር 15 የተመለከተ ሆኖ በስድት ምዕራፍ ተጠቃሎ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት በግልጽ ሊያገለግሉ የሚችሉ በሥነ ምርምር የተደረሱት የበለጡ ውጤቶች (ምዕ. 1) ማዳመጥ ከሚለው ሃሳብ በመንደርደር ከቅዱስ መጽሓፍ ጋር እና በአይሁደ-ክርስትና ባህል (ምዕ. 2) አማካኝነት የችግሩን ሥርወ መንስኤውን በመለየት (ምዕ. 3) መነጻጻር ወደ ሚለው ሃሳብ ይሸጋገራል። ዓዋዲው መልእክቱ የሚያቀርበው ሃሳብ (ምዕ. 4)፣ ምኅዳር ከሚመለከቱ ጥያቄዎች ጋር ትሥሥር ያለው ፈጽሞ ከዚህ ሊነጠል የማይቻል “በግልጽ ሰብአዊና ማኅበራዊ መሥፈርት የሚያጠቃልል ምሉእ ሥነ ምኅዳር (137) የሚል አንድ ሃሳብ ያቀርባል። በዚህ አስተያየትም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ (ምዕ. 5) በሁሉም ማህበራዊ ሕይወት፣ ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ደረጃ ግልጽ የሆኑ ውሳኔዎች ቅርጽ ለማስያዝ የሚያበቃ ቅን ውይይት ማነቃቃት የሚል ሃሳብ ያቀርባሉ፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም በሕንጸት በመንፈሳዊ በቤተ ክርስቲያን በፖለቲካና በቲዮሎጊያ ደረጃ ሃሳብ በማቅረብ፣ ማንኛውም እቀድ ከአንድ ከታነጸ ኃላፊነት ከተሞላው ኅሊና ካልተነቃቃ ውጤታማ ሊሆን እንደማይችል ያብራራሉ። ሰነዱ ሁሉም “በአንድ ፈጣሪና አባት በሆነው እግዚአብሔር” (246) ላይ እምነት ካላቸው ጋር ተካፍሎ የመኖር መሥዋዕት በተሰኘውና ሁሉም በዚያ የዓዋዲው መልእክት መክፈቻና መዝጊያ ባደረጉት ውዳሴ ላንተ በተሰየመው የማኅሌት አዝማች ምት የተካነ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑት በሚወክልና ሁሉም ኃይማኖቶችን  በሚያቅፍ በሚያቅርቡት  ሁለት የጸሎት ሃሳብ አማካኝነት ይጠቃለላል።

ሰነዱ አንድ ጽኑ ውህደት በሚያሰጡት በተለያዩ አስተያየቶች በሚዳሰሱት በአንዳንድ ርእሰ ጉዳዮች ሥር የተጣመረ ሲሆን፣ ይኽም “የዓለም ድኾች መካከልና ቤተሰቦች መካከል ያለው ውስጣዊ ግኑኝነት፣ በዓለም ያለው ሁሉ ውስጠ ትሥሥር ያለው ነው እማኔ ሲሆን፣ ለአዳዲስ መመዘኛዎችና ከዕደ ጥበብ የሚገኘው የተለያየ የሥልጣንና የብቃት አግባብ ሓያሲ፣ ለአዲስ የኤኮኖሚና የእድገት ግንዛቤ የሚያበቃ አግባብ እንዲፈጠር ጥሪ የሚያቀርብ፣ የሁሉም ፍጥረት ክብር የሚል፣ የሥነ ምኅዳር ሰብአዊነት ትርጉሙ፣ ቅንና እውነተኛ ውይይት ያለው አስፈላጊነት፣ ጥንቃቄ የሚያሻው ጥልቅ ዓለም አቀፋዊና ክልላዊ ፖለቲካ ኃላፊነት አስወጋጅ ባህል የሚተነትንና አዲስ የአኗኗር ሥልት የሚል ሃሳብ” (16) ያካተተ ነው። በዚህ አስተያየትም “ማንኛውም በፍጠርት ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ ‘ጸረ የሰብአዊ ክብር ነው’” (92)፣ ነገር ግን “በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ርህራሄና ተቆርቋሪነትና አሳቢነት ከሌለ “ከሌሎች የፍጠረት መሆናውያን ጋር እውነተኛ ስሜት የተካነ ውስጣዊ አንድነት እንደማይኖር ነው” (91)። 








All the contents on this site are copyrighted ©.