2015-06-12 16:39:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ ክርስቲያን አገልጋዮች በመሆን አታላዩን ሃብት እንቢ እንዲሉ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ዘነግህ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል የዕለቱ ምንባብ ግብረ ሐዋርያት ምዕ. 11፣ 21-26, ምዕ. 13፣ 1-3፣ የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 10፣ 7-13 መሠረት በማድረግ መራመድ ማገልገልና ውፉይነት የተሰኙት ሦስት ቃላት ማእከል ያደረገ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ድኅነት የድኅነት ወንጌል ለማድረስ መውጣት መጓዝ ማገልገል ውፉይነትን ይጠይቃል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርትን አዲስ ዜና ያበስሩ ዘንድ ይልካቸዋል። ይክ ደግሞ ተራ ጎዞ እንዲያከናውኑ ሳይሆን ተልእኮ ይቀበላሉ፣ እርሱም ወንጌላዊ ተልእኮ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሲያብራሩ፦

አዲስ ዜና ውስጣዊ የለውጥ ጉዞ አማካኝነት ለማበሰር መውጣት

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የሚሰጣቸው ተልእኮ የተቀበሉትንና በውስጣቸው ያጣጣሙትን ሕይወታቸውን ያደረጉት በውስጣዊ መለወጥ የተሸኘ ነው። በምሥጢረ ጥምቀት የተቀበልከውን ለሌሎች ማቅረብና መስጠት ሳይሆን፣ ከገዛ እራስ ወጥቶ ቃሉን በቃልና በሕይወት ማበሰር ማለት ነው። ወንጌላዊ ልኡክነት ማለት ነው።

የኢየሱስ ደቀ መዝሙር አዲስ ዜና ለማበሰር አሻግሮ ለመሄድ የተጠራ ነው። ሆኖም ይኽ ተልእኮ ውስጣዊ መለወጥን ይጠይቃል። ደቀ መዝሙር ዕለት በዕለት ጌታን የሚሹ በዕለታዊ ሕይወታቸው እርሱም የሚፈልጉ በጸሎት በአስተንትኖ ከእርሱ ጋር የሚገናኙ መሆን አለባቸው። ዘወትር እግዚአብሔር የማይፈልግ ከሆነ ወደ ሌሎች የሚያደርሰው አዲስ ዜና ኃይል የሌለው ኮሳሳ ሆኖ ይቀራል።

የማያገለግል የኢየሱስ ድቀ መዝሙር ክርስቲያን አይደለም

ቀጥለውም አገልግሎት የተሰኘውን ቃል ጠቅሰው፣ የማያገለግል ደቀ መዝሙር ክርስቲያን አይደለም። ደቀ መዝሙር ኢየሱስ ያደረገውን ለማድረግ የተጠራ ነው። የተራራው ስብከት መርሃ ግብር የሚያደረግ፣ እኛ ፍርዳችን በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25 ያለው የስምምነት ሰነድ ይገልጠዋል፣ እግብር ላይ የመኖር ብቃታችን ፍርዳችን ነው። ክርስትናችን የተራራው ስብከት መርሃ ግብር ያደረገ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 25 ያለው ውል የሚከተል መሆን አለበት። ሕይወት ለአገልግሎት ካልሆነ መኖር ምንም ጥቅም የለውም፣ ክርስቲያን መሆን ሁሌ ማስቀደስ ተናዣዥ ቆራቢና ጸላይ ትእዛዛትን አክባሪ መሆን ብቻ የሚኖር ከሆነ ባዶ ነው። ሌላውን ማገልገል ሊታከልበት ይገባል። ለታመመው ለተጠማው ለተራበው በወህኒ ቤት ለሚገኘው ሁሉ፣ እየሱስ አድርጉ ያለንን መኖር። በሌሎች ዘንድ የሚገለጠውን ክርስቶስ ማገልገል።

በነጻ በማገልገል ኣታላዩን ሃብት እምቢ ማለት

ቅዱስ አባታችን በመጨረሻም ውፉይነት የሚለውን ቃል ጠቅሰው፣ በነጻ የተቀበላችሁት ሁሉ እናንተም በተራችሁ በነጻ አድሉት ብሎናል፣ ድኅነት በነጻ ታድሎናል፣ ማንም የመዳን ጸጋ ገንዘብ ከፍሎ የተቀበለ የለም፣ ማንም ለድኅነት የበቃሁኝ ነኝ ብሎ የተገባኝ ነው የሚል የለም። የተገባን ስለሆን ሳይሆን ጌታችን በነጻ ስላፈቀረን ነው። እግዚአብሒር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ አማካኝነት የፈጸመው የማዳን እቅድ ጸጋ ነው።

በነጻ ነውና የተቀበላችሁት እናንተም በተራችሁ በነጻ አድሉት የሚለው ጌታችን የተወልን ቃል ብዙውን ጊዜ እንዘነጋለን። ድኅነት በነጻ የታደለን ጸጋ መሆኑ የሚዘነጋ ክርስቲያን ሰበካ ቁምስና መንፈሳዊ ማኅበራት ማየት እንዴት ያሳዝናል። ድኅነት ከሃብትና ከሥልጣን ሳይሆን በሃብትና በሥልጣን ሳይሆን በነጻ የተሰጠ ጸጋ ነው።

ቅዱስ አባታችን ያስደመጡት ስብከት፣ ጉዞአችን ወንጌል ለማበሰር የተላክን መሆናችን የሚኖር፣ የክርስትና ሕይወት ለገዛ  እራስ የሚኖር ሕይወት ሳይሆን እንደ ኢየሱስ ስለ ሌሎች የሚኖር ሕይወት ነው፣ ይኽ ደግሞ አገልግሎትን ያመለክታል። እግዚአብሔር በነጻ በኢየሱስ አማካኝነት የሰጠንን የድኅነት ጸጋ በነጻ ማወጅ፣ ውፉይነት ማለት ነው። ተስፋችን በእኔ ባይነት በግል ምቾትን የዓለም በመሆን ላይ የጸና ከሆነ ፈራሽ ይሆናል፣ ፈራሽ ተስፋ ሆኖ ይቀራል። የሐሰቱን ተስፋ የሚያፈርሰውና የሚገስጸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.