2015-06-12 16:26:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የቃል ኪዳን መሠረተ ትርጉሙ ለሚያሳንስ ኅልዮ እምቢ ማለት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ የካቶሊክ ብፁዓን ጳጳሳት በየአምስቱ ዓመት ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ውህደት ለመመስከር፣ ለማጽናት፡ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸውን፡ አንድነታቸውን ለመመስከር እዚህ ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለመሳለና ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ወቅታዊውና አንግብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች አስደግፈው ከቅዱሱ ኣባታችን ጋር መክረው መሪ ቃል የሚያገኙበት መንፈሳዊ ጉብኝት ምክንያት እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. አገረ ቫቲካን የገቡትን የኤስቶኒያና ለቶኒያ ብፁዓን ጳጳሳትን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው ለኤስቶኒያና ለቶኒያ ብፁዓን ጳጳሳት የቃል ኪዳን መሠረተ ትርጉሙ ለሚያሳንስ ኅልዮ እምቢ በማለት ቤተሰብ ማነቃቃት ያለው አስፈላጊነት ላይ በማነጣጠር በለገሱት መሪ ቃል፦ 

ቤተሰብ ተዛማጅና ኢግብረ ገብ ባህል ባደፈጠበት ኅብረተሰብ ውስጥ የሚገኝ የኅብረተሰብ ማእከል መሆኑ ማስተጋባት

ቤተሰብ በብዙኅነት አብሮ መኖር የምንማርበት ሥፍራ ነው። ስለዚህ የቤተሰብ እሴት ማነቃቃት ወሳኝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አሳስበው ቤተሰብ ክብርና ሰብአዊ ነጻነት የሚጻረር ኅልዮ እማካኝነት ባህላዊ ሥነ ልቦናዊ ጭቆና ለተጋረጠበት ኅብረተሰብ በተለይ ደግሞ በዚህ በአሁኑ ወቅት ኢግብረ ገብና ተዛማጅ ባህል ባደፈጠበት ኅብረተሰብ ያ የእግዚአብሔር ጸጋ የሆነው በአርአያውና አምሳያው በፈጠራቸው በወንድና በሴት መካከል በሚረጋገጠው ጥልቅ ግኑኝነት አማካኝነት የሚጸና የኅብረሰብ መሠረትና ማእከል መሆኑ ከምን ግዜም በበለጠ መመስከር የሁሉም ምእመንና የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ዓላማ መሆን አለበት እንዳሉ ኦንዳርዛ ገለጡ።

የቃል ኪዳን መሠረተ ትርጉሙ የሚያሳንስ ኅልዮ የፍችና የመለያየት ምክንያት ነው

በአሁኑ ወቅት ቤተሰብ ስሜታዊ ትርጉም እየተሰጠው እርሱም ሲፈለግ የሚጸና ካልሆነም እንዳሻህ ለመተርጎምና እንደየ ጊዜው ቅርጹን መቀያየር እየተለመደ ነው። ይኽ ዓይነት ዘመን አመጣሽ የቤተሰብና የቃል ኪዳን መሠረተ አልቦ ትርጉም በክርስቲያኖችም ዘንድም ሳይቀር ተጽዕኖ እያሳደረ ነው፣ ይኽ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የሚታየው በቀላሉ መፋታት ችግር ሲያጋጥም መለያየት ልሙድ እንዲሆን እያደረገ ነው። ስለዚህ ሁሉም ቤተሰብ ያለው የላቀው ትርጉሙ እንዲገነዘብ ቤተ ክርስቲያን ለወጣቱ ትውልድ ጥልቅ የጥሪ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማቅረብ የቃል ኪዳን የምሥጢረ ተክሊል ትርጉም በማቅረብ ማነጽ ያለው አስፈላጊነት በፍችና በመለያየት ምክንያት ለተለያየ አደጋ ለሚጋለጡት ሕፃናት መንከባከብና የእግዚአብሔር ምኅረት ፈጽሞ እንደማይለያቸውም መመስከር ማለት መሆኑም እንዳብራሩ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በኤስቶኒያና በለቶኒያ የሚታየው እርሱም በድኽነትና በኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ሳይፋቱ ነገር ግን ዕለታዊ ኑሮ ለማሸነፍ ሲባል ባልና ሚስት እናትና አባት ተለያይተው እንዲኖሩ ለተገደዱት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ልዩ በሆነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ቅርብ በመሆን በማነጽ የአባት ወይንም የእናት መራራቅ እያስፋፋ ያለው ሁነት ልጆች የማሳደጉ አቢዩ ኃልፊነት በአባት ወይንም በእናት ብቻ የሚከናወን በመሆኑ ከባድ ሆኖ ይገኛል፣ ስለዚህ አደራ ቤተ ክርስቲያን ለእነዚህ ዜጎች ቅርብ ትሁን። ካህናት ልኡካን ገዳማውያን ሁሉም ለሕዝበ እግዚአብሔር የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ጥዑም መአዛ ሆነው ቅርበት እንዲኖር የተጠሩ መሆናቸው አደራ መቼም ቢሆን እንዳይዘነጉ ማሳሰባቸው ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ ገለጡ።

ዓለማውያን ምእመናን በቤተ ክርስትያንና በኅብረተሰብ ዘንድ ኃላፊንታቸው እንዲወጡ የተጠሩ ናቸው። ኃላፊነታቸውን በሚገባ በሙላታ እንዲኖሩና እንዲወጡም በቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት አማክኝነት ሊታነጹ ይገባል። ዓለማዊ ምእመን በእረኞችና በተለያዩ የማኅበራዊ ክፍሎች መካከል ግኑኝነት እንዲኖር የሚያግዙ ናቸው፣ የቤተ ክርስትያን ልብ ለእነርሱ ቅርብ መሆኑ የሚያረጋግጥላቸው እንክብካቤ አደራ እይዳይለያቸው በማለት የለገሱት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኦንዳርዛ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.