2015-06-10 16:16:00

አለ አንድ የጋራ አካፋይ ነጥብ እርቅ ለማረጋገጥ ይሚቻል አይሆንም


በዚህ ኅብረአዊነት በተረጋገጠበት ዓለም፣ ዓለማዊ ትሥሥር በሚኖረው ኅብረተሰብ በምዕራብና በምስራቅ መካከል እርቅ ግንባታ ካንድ የጋራ አካፋይ እርሱም ማንኛውም ዓይነት አመጽ ጦርነት እምቢ በማለት ማግለልና ማውገዝ ከሚለው ሃሳብ ካልተንደረደረ፣ መቀራረብና እርቅ ለመጨበጥ ዘበት መሆኑ ካቶሊካዊ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ አነሳሽነት በኢጣሊያ ፊረንዘ ከተማ ምስራቅና ምዕራብ፣ የሥልጣኔ ውይይት በሚል ርእስ ሥር ባነቃቃው ዓውደ ጥናት እንደተሰመረበት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።

በዚህ ዛሬ እ.ኤ.አ. ሰነ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የሁለት ቀናት ዓውደ ጥናት በግብጽ የካይሮ አል አዝሓር መንበረ ጥበብ አቢይ ኢማም ሙሓማድ አል ታየብ የሚገኙባቸው የተለያዩ ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች የቲዮሎጊያ ሊቃውንት የሥነ ሃይማኖት ሊቃውንት መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ የዓውደ ጥናት አዘጋጅ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበርሰብ ሊቀ መንበር ማርኮ ኢምፓሊያዞ ከዓውደ ጥናቱ ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በሁለቱ በምዕራብም ሆነ በምስራቁ ዓለም ጦርነት ለረዥም ዓመታት የተለያዩ ውስጣዊ ውጥረቶችን አለ መግባባት ብሎም ከግል ጥቅም አንጻር በመንደርደር ሲከናወን ታይቷል እየታየም ነው። በመሆኑም ርእሰ አቃቂር ጭምር በማካሄድ ዓመጽ ጦርነት ሁሉ ማውገዝ የእርቅ ቀዳሚው ደረጃ ነው። በኤውሮጳ የታዩት ሁለቱ ዓበይት የዓለም ጦርነቶች ማስታወሱ ይበቃል።

በሁለተኛው ደረጃም ፈጣን በሆነ አካሄድ በክፉም በደጉም ዘረፈ ብዙ ለውጥ እየተረጋገጠበት ባለው ዓለም አዲስ ወቅታዊው ሁኔታ በጥልቀት ግምት የሚሰጥ ለወጣት ትውልድ አዲስ የሕንጸት ስልት ማቅረብ ለእርቅ ወሳኝ ነው። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንደሚለውም በዓለም በሁሉም አገሮች የምንገለገልበት የሕንጸት ስልት ኅዳሴ ያሻዋል፣ ምክንያቱም ወጣቱ ትውልድ የበለጠ ዓለም ለማነጽ የተጋ እንዲሆን መደገፍ አለበትና ብለዋል።

የግጭቶችና ጦርነቶች ምክንያት ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ነው። ስለዚህ ኃይማኖት የጦርነትና የግጭት ምክንያት ሆኖ አይታይም ለማለት ይቻላል። ምንም’ኳ አክራሪያን ታጣቂ ኃይሎች በኃይማኖት ስም የሚያካሂዱት ጦርነትና ግጭትም ይኑር የግጭቱ ዋናው መንስኤ ኃይማኖት አይደለም ምክንያቱም ኃይማኖት የሞትና የአመጽ መሣሪያ አይደለምና። ሁለቱ ሥልጣኔዎች ባለፉት ዘመናት ተገናኝተው አብረው ለመኖር ችለዋል፣ ይኽ ሁነት ዛሬም እውን ይሆን ዘንድ ተስፋው አለ። ስለዚህ በጋራ በዓለም ሰላምና እርቅ እንዲረጋገጥ የጋራ አካፋይ ሃሳብ ማቅረብ ይችላሉ።

በአሁኑ ሰዓት ዓለማችን ፍርሃትና ቀውስ ከቦታል፣ ስለዚህ ለፍርሃትና ለሚታየው ቀውስ እጅን ሰጥቶ መኖር ፍርሃትና ቅውስ እጅግ እንዲስፋፋና እንዲነግሥ የአብሮ መኖር መመዘኛ እንዲሆኑ ማድረግ ማለት ነው። በመሆኑም ፍርሃቱና ቀውሱን ለይቶ መፍትሄው ማፈላለግ፣  መፍትሔ ለመለየት ደግሞ የፍርሃቱና የቀውሱ መንስኤ መመለየት ግድ ነው። በፊረንዘ የተካሄደው ዓውደ ጥናትም ይኸንን ሃሳብ ነው ያሰመረበተ። አሸባሪያንና አክራሪያን በሚያረማምዱት ሃይማኖት ተገን ያደረገው ዓመጽና ጦርነት ለሚሰቃየው የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ዜጎች መደገፍ ለስቃያቸው ቅርብ መሆን ስለዚህ በደፈናው አነጋገር እስላም ወይንም የክርስትናው እምነት ከመውቀስና  ከእርስ በእርስ መወቃቀስ መራቅ ይገባናል፣ እርስ በእርስ ወቃቀስና መወነጃጀል አክራሪያኑ የሚሻው ሁነት ነው። የእርስ በእርስ መወቃቀስ ጉዳይ አክራሪያን ለሚያረማምዱት አመጽና ግጭት ለም መሬት ነው። በመሆኑም ከመወቃቀስ ተቆጥቦ በጋራ ጦርነትና አመጽ በማውገዝ ለእርቅ መቀራረብ ለሰላም ወሳኝ መሆኑ የፊረንዘው ዓውደ ጥናት እንዳሰመረበት ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.