2015-06-08 16:21:00

የብፅዕና አዋጅ


የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብራዚሊያዊ ካህን የእግዚአብሔር አገልጋይ ፍራንቸስኮ ዲ ፓውላ ቪቶርና እንዲሁም የቅዱስ ልበ ኢየሱስ አገልጋዮች ደናግል ማኅበር ተባባሪ መሥራች የፖላንድ ተወላጅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ክላራና በ 1936 ዓ.ም. በስፐይን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት የእምነት ሰማዕትነት የተቀበሉትና በላኦስ ከ 1954 እስከ 1970 ዓ.ም. በእምነታቸው ምክንያት ለሞት የተዳረጉትን ሰማዕታት በቅርቡ ብፁዕና እንደሚታወጅላቸውና ሌሎች ሦስት ካህናትና አንዲት የኢጣሊያ ዜጋ ገዳማዊት ጭምር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ገድለ ክብራቸው እውቅና እንዲትሰጥበት ያቀረቡትን ሰነድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተቀብለው እንዳጸደቁት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፅዕና የሚታወጅላችው የእግዚአብሔር አገልጋይ ብራዚላዊ ካህን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 12 ቀን 1827 ዓ.ም. ተወልደው በብራዚል ትረፖንታስ እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 1905 ዓ.ም. በሰማይ ቤት የተወለዱና የእግዚአብሔር አግልጋይ የፖላንድ ተወላጅ ክላራ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 18 ቀን 1863 ዓ.ም. ተወልደው እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 1916 ዓ.ም. በሰማይ ቤት የተወለዱ ሌሎች ብፅዕና የሚታወጅላቸው በስፐይን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት የደም ሰማዕትነት የተቀበሉት የእግዚአብሔር አገልጋይ አባ ፈደሪኮ ዳ በርጋና ሌሎች 25 የንኡሳን ፍራንቸስካውያን ማኅበር ገዳማውያን ካህናትና ወንድሞች እንዲሁም በላኦስ እራት ዓለማውያን ምእመናን የሚገኙባቸው የፈረንሳይ የውጭ ወንጌላዊ ልኡካን ማኅበር አባላት አባ ተዮ ቲየንና 10 የማኅበረ ውፉያን ለቅድስት ድንግል ማርያም ልኡካነ ወንጌል አባላት መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.