2015-06-03 16:18:00

ጳጳሳዊ የተልእኮ ወንጌል ተግባር፦ ኵላዊ ወንጌላዊ ልኡክነት መደገፍ


ጳጳሳዊ የተልእኮ ወንጌል ተግባር “ኵላዊ ወንጌላዊ ተልእኮ ዛሬ ነገም እንዴት መደገፍ” በሚል ርእስ ሥር የተመራ ጠቅላይ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ሰነ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደጀመረ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ ገልጠው አያይዘውም በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ በተለያዩ አገሮች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን የሚወክሉ በጠቅላላ ከአንድ መቶ በላይ የሚገመቱ ልኡካን እየተሳተፉ መሆናቸውና ተጋባእያኑ ትብብርና መደጋገፍ ሁሉም የሁሉም በሚል መንፈስ ሥር ክርስቲያን ተቋድሶ መኖር በሚል መለያ ኩላዊነትን በተግባር ለመኖር የተጠራ በመሆኑ የታደለ የተልእኮ ወንጌል መሣሪያ ነው በሚል ራእስ ሥር በቡድን ተከፋፍለው ውይይት እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል።

የዚህ ጳጳሳዊ የተልእኮ ወንጌል ተግባር ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፕሮታሰ ሩጋምብዋ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የዚህ ጳጳሳዊ የተልእኮ ወንጌል ተግባር መለያው ኵላዊነት የሚል ነው። ይኽ የካቶሊካዊት የቤተ ክርስቲያን ኵላዊነት የሚያመለክት ሲሆን፣ ሆኖም መሠረቱ ወንጌልን ለሁሉም አሕዛብ አድርሱ በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርት የሰጠው ተልእኮ ነው። ኵላዊነት ወንጌል ነው ወንጌላዊነትም ነው። በዚህ ዝክረ 50ኛው ሁለተኛው የቫቲካን ጉብኤ በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት ወደ አሕዛብ የተሰኘው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ድንጋጌ እንዴት ባለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እግብር ላይ እየዋለ መሆኑ ሰፊ ግምገማ የሚካሄድበት ጠቅላይ ጉባኤ ነው ብለዋል።

አስፍሆተ ወንጌል በበለጠና በታደሰ መንፈስ ለማነቃቃት አዳዲስ ግፊቶችን በጥልቀት ለመለየት የሚወያይ ጉባኤ ነው። ተልእኮው የዓለማችን ወቅታዊው ሁኔታ በማንበብ ለወቅታዊው ዓለም ሊናገር የሚችል እንዲሆን ማድረግ። እንዲህ ሲባል የተልእኮው አንኳር መቀየር ሳይሆን እንኳሩን በወቅታዊው ቋንቋ ማቅረብ ማለት ነው። ቤተሰብ የተልእኮ ተወናያን ነው። ዓለማዊ ምእመን ጭምር፣ ስለዚህ ክርስቲያን ሁሉ ለአስፍሆተ ወንጌል የታደለ መሣሪያ ነው። አዳዲስ አቢያተ ክርስቲያን አዳዲስ ሰበካዎች በሁሉም መስክ መደገፍ ያለው አስፈላጊነት የሚያበክር ጉባኤ እንደሚሆን ገልጠዋል።

በርግጥ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ምጽዋት በተለያየ ምክንያት እየቀነሰ መምጣቱ የሚካድ አይደለም፣ ሆኖም በተለያየ መስክ የሚሰማሩ መንግሥታዊ ያልሆነ የተራድኦ ማኅበራት ብዛት ከፍ እያለ በመሆኑ ሕዝብ የሚሰጠው ድጋፍ ለሁሉም ለማዳረስ የሚያደረገው ጥረት የሚያረጋግጥ አወንታዊ ገጽታ ያለው ሁነት ነው። በተለያየ መልካም ዓላማ ተነቃቅቶ ለሕዝብ ጥቅም ድጋፍ ሰጭ መንግሥታዊ ያልሆኑ ማኅብራት መኖርና መስፋፋት መልካም ነው። ለአስፍሆተ ወንጌል ለወንጌላዊ ተልእኮ የሚሰጠው ድጋፍ ለማበረታታት የሰበካዎች ጥረት ያስፈልጋል፣ ወንጌላዊ ተእልኮ ያለው አስፈላጊነት ሁሉም እንዲረዳው የሚያበቃ ወንጌላዊ ቅስቀሳ ያስፈልጋል፣ ሆኖም በዓለም ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ መዘንጋት የለብንም ብለዋል።

በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተእልኮ አንድ ነው። የክርስቶስ ተልእኮ ነውና። ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅጥ የጥሪ እጥረት ተጋርጦባት ይገኛል። ስለዚህ የወንጌላዊ ልኡክነት አላማ አንዱም ጥሪ ለማነቃቃት የሚደገፍ ነው። ማነቃቃት ሲባል በቃልና በሕይወት ነው። ስለዚህ ልኡካነ ወንጌል ታማኝና አሳማኝ የወንጌል ምስክር ሆነው እንዲገኙ የሚጠይቅ አገልግሎት ነው። ክሁሉም በላይ ስለ ጥሪ ካለ ማቋረጥ መጸለይ ያስፈልጋል። የጥሪ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማጠናከር ያለው አስፈላጊነተ አበክረው፣ ጉባኤው ተጋባእያኑ ክቅዱስ አባታችን ጋር ተገናኝተው ቅዱስነታቸው በሚሰጡት ምዕዳን እንደሚጠናቀቅ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.