2015-06-01 16:56:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ማክበር


የአንድ ሕዝብ ሥልጣኔ መለኪያው ሕይወት ለማቀብ ያለው ብቃት እርሱም ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የሚያከበርና የሚያቅብ የሕይወት ባህል የመኖር ብቃቱ ነው። የአዛውንት የድኻው የስደተኛው የተጠማው በተለያየ ችግር የተጠቃው ሰው ልጅ ሕይወት መከላከል የሥልጣኔ የሥነ ባህል የሥነ ምርምር ባጠቃላይ የሥልጣኔና የእድገት መለኪያ መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፣ ሥነ ምርምርና ሕይወት የተሰየመው ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እቃቤና አክብሮት የሚል አላማ በተለያየ መልኩ የሚያረማምደው እንቅስቃሰኤ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት የተሳተፉትን ተቀብለው በለገሱት ምዕዳን እንዳሰመሩበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።

ሥነ ምርምር ዘወትር ሕይወትን የሚያገለግል ሥነ እውቀት

አንድ ተጠቅሞ መጣል በሚለው አመክንዮ የሚመራ ባህል በተስፋፋበት ዓለም የክርስቶስ ፍቅር የተናቁት የአዛውንት የተጠሙትን የተነጠሉትን ሁሉ ያንን ከጥንት ጀምሮ የሕይወት ክብር የሚለው እሴት አማካኝነት ለመደገፍ ለማፍቅር ይገፋፋናል። የሕይወት ፍቅር የሕይወት ባህል ያ የማይታበለው በማንም ሊሰረዝና ውድቅ ሊሆን የማይችለው የሕይወት ክብር የሥነ ምርምር ሂደት የሚሸኝ ባህል መሆን አለበት። ሥነ ምርምር የድንቅና የውበት አገልጋይ፣ እርሱም በሕይወት ተአመር የሚደነቅና ውበቱን የሚያጤን መሆን አለበት። ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምና የሰው ልጅ ብርሃን፣ ሥነ ምርምር የሕይወት አገልጋይ እንዲሆን የሥነ እውቀት ጎዳና ብሩህ ያደርጋል። ይኽ ብርሃን ችላ ሲባልና ከብርሃኑ ይልቅ ጨለማ ሲመረጥ፣ ከሕይወት ጋር መገናኘቱ ቀርቶ በመኻንነት ባህል መኖር ይጀመራል።

ጽንስ ማስወረድ ልክ ስደተኞች ለሞት አሳልፎ እንደ የመስጠት ጸረ የሕይወት ጥቃት ነው

ሥነ ምርምር ለሰው ልጅ አገልግሎት እንጂ ሰው ለሥነ ምርምር አገልግሎት የተፈጠረ አይደለም። በማለት ቅዱስ አባታችን አንድ ኅብረተሰብ ቅን የሚያስብለው ተቀዳሚው ጉዳይ ያንን ቀዳሜ የሕይወት ባህል ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የሚለውን ክብር የማክበር ብቃቱ ነው። የአንድ ኅብረሰብ ሥልጣኔ የሚለካው ለሕይወት ያለው ክብር ነው። በተለይ ደግሞ ኮሳሳ የሆነው ሕይወት በቀላሉ ለአደጋ ሊጋለጥ የሚችለውን ሕይወት ያለው የላቀው የማቀብና የመከላከል ደረጃ ነው።

ጽንስ ማስወረድ በሕይወት ላይ የሚጣል ጥቃት ነው። በተለያየ ችግር ተገፋፍተው ለስደት የሚዳድረጉት በባህር ጉዞ ወደ በለጸገው ዓለም የሚሰደዱትን በባህር ጉዞ ሕይወታቸው ለአደጋ ሲጋልጠ ዝም ብሎ ማየቱ ልክ ጽንስ እንደ የማስወረድ ተግባር ነው። ሕይወት በሁሉም ደረጃ ማቀብና መከላከል ሲባል በተለያየ መልኩ በሕይወት ላይ የሚጣለው ፈተና፣ በጉልበት ሥራ የሚያጋጥም የሞት አደጋ። በተመጣጠነ የምግብ እጥረት የሚያጋጥም ሞት፣ አሸባሪያን የሚፈጽሙት የሞት ጥቃት፣ አመጽ ጣፋጭ ሞት የሚያረማምደው የሞት ባህል፣ አማካንነት የሚፈጸመው ጽንስ ማስወረድ መቃወም ማለት ነው። ሕይወትን ማፍቀር ስለ ሌላው ማሰብ ያንን በሰው ልጅ በኑባሬ ያለው ከነገር ማዶ የማቅናት ባህርይ ማክበር። ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ማክበር ማለት ማንኛውም ጸረ የሕይወት ተግባር መቃወም ማለት ነው።

ከኢአማንያን ጋር መወያየት

የታደሰ የሕይወት ባህል የመተማመንና የእርስ በእርስ መከባበር በሚለው ውሳኔ የሚጸናው ድራዊ ግኑንነት ማረጋገጥ ሰላም ምህረትና ውህደት የሚል አድማስ ማቅረብ ያግዛል። ከሁሉም ባህሎች ከጠቅላላ ሥነ ምርምር ኢአማንያን ነገር ግን ለሰብአዊ ሕይወት ምሥጢር ክፍት ከሆኑት ጋር ጭምር ለመወያየት አትፍሩ፣ የሕይወት ባህል ለማስፋፋት ክፍት መሆን ያስፈልጋል በማለት ያስደመጡት ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.