2015-05-29 16:55:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የዓለምና ፈሪሳዊ የሆነ ክርስቲያን ሕዝብ ከኢየሱስ እንዲርቅ ያደርጋል


ከእግዚአብሔር ጋር ስላላቸው ግኑኝነት ብቻ የሚያሰላስሉ፣ እምነትን በልዋጭ የሚሉ እምነትን መያዣ የሚያደርግ፣ የዓለም የሆኑ ሥርዓትና ሕግ ማክበር ብቻ የሚሉ ክርስትያኖች ሕዝብን ከኢየሱስ እንዲርቅ ያደርጋሉ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ዘነግህ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. በዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው ባሰሙት ንግግር፦

ግድየለሽና ውስጣዊ ግለኝነት የሚል ክርስቲያን

ቅዱስነታቸው የዕለቱ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 10 ከቁጥር 46-52 የተነበበውን ጠቅሰው፣ የጤሜዎስ ልጅ ዓይነ ስውሩ በርጤሜዎስ ኢየሱስን የዳዊት ልጅ ሆይ ራራልኝ እያለ ኢየሱስ ይፈውሰው ዘንድ እየጮኸ ሲለምን፣ ደቀ መዛሙርት ዝም ሊያሰኙት የፈጸሙት ተግባር ሦስት ዓይነት ማኅበረ ክርስቲያን እንዳለ ያመለክትልናን።

ራስ ወዳድ ዝግ እኔና ኢየሱስ ከኢየሱስ ጋር ስላላቸው ውስጣዊ ግለኛ ግኑኝነት ብቻ የሚሉ

እነዚህ የሌላው ጩኸት የማይሰሙ ለሌላው ችግር እዝነ ልቦና የሌላቸው በግዴለሽነት የተጠቍ ኢየሱስን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የሚያቀርቡት ጩኸት የማይሰሙ፣ የገዛ እራሳቸው ማኅበርሰብ ብቻ ሕይወታቸው ያደረጉ፣ ድህነት የሚያስፈልጋቸው ቤተ ክርስቲያን የምታስፈልጋቸው ሰዎች ለሚያሰሙት ጩኸት ጀሮ ዳባ ልበስ ያሉ፣ ራስወዳድነት የተሞሉ ለሌላው ምንም ዓይነት ቦታ የማይሰጡ ለገዛ ራሳቸው ብቻ የሚኖሩ የኢየሱስ ድምጽ ለማዳመጥ የተሳናቸው በማለት እንደገለጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እምነትን በልዋጭ የሚሉ እምነት መያዣ የሚያደርጉ ክርስቲያኖች

እርዳታ የሚፈልጉ የሚያቀርቡት ጩኸት የሚያዳምጡ ነገር ግን ጩኸቱን አዳምጠው ለመተባበርና ለመደገፍ ሳይሆን። እርዳኝ ራራልኝ የሚለውን ድምጽ ሰምተው ዝም ለማሰኘት የሚሞክሩ ክርስቲያኖች፣ ልክ እንደ ደቀ መዛሙርት በርጤሜዎስን ዝም ለማሰኘት እንደሞከሩት ዓይነት ተግባር የሚኖሩ ክርስቲያኖች፣ ይኽ ዓይነቱ ክርስትና ኢየሱስን ፈልገው የሚጮኹት እምነትን የሚፈልጉ ድህነት የሚያስፈልጋቸው ከኢየሱስ እንዲሸሹ ያደርጋሉ።

እምነትን በልዋጭ እንደ መያዣ የሚኖሩ ለኢየሱስ ቅርብ ናቸው፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ናቸው፣ የእግዚአብሔርና ሃይማኖተኛ ሰዎች ይመስላሉ፣ ሆኖም ግን ኢየሱስ ከቤተ መቅደሱ ያባራቿል፣ ምክንያቱን የእግዚአብሔር ቤት የገበያ ሥፍራ የሚያደርጉ ናቸውና። እርዳኝ የሚለውን ድምጽ የማያዳምጡ ሕዝበ እግዚአብሕርን ለገዛ እራሳቸው ትርፍ የሚያውሉ ናቸው። ሕዝብን ከኢየሱስ ያርቃሉ። ምስክርነት የማይሰጡ ክርስቲያን። የስም ክርስቲያኖች የደጀ ሰላም ክርስቲያኖች፣ በውስጣቸው ክርስትያን ያልሆኑ፣ የዓለም የሆኑ። ክርስቲያን ነኝ የሚል ነገር ግን እንደ ዓለም ፍላጎት የሚኖር። ይኽ ደግሞ ኢየሱስን ፈልገው የሚጮኹትን ከኢየሱስ የሚያርቁ ናቸው።

ፈሪሳዊነት ሕግ እጥባቂዎች ሥርዓት አፍቃሪዎች ሊሸከሙት የማይፈልጉትን ከባዱ ሸክም በሕዝብ ላይ የሚያኖሩ፣ ስለ እነዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው በወንጌል ማቴዎስ ምዕ. 23 ዘንድ እንገኘዋለን። አስመሳዮች ሕዝብ ለገዛ ራሳቸው ምቾትና ትርፍ የሚያውሉ ይላቸዋል። እነዚህ ደግሞ ኢየሱስን ፍለጎ የሚጮኸው ከኢየሱስ እንዲርቅ ያደርጋሉ።

የሚያምኑት ብቻ የሚኖሩ ክርስቲያኖች

ሌሎችን ወደ ኢየሱስ ለማቅረብ በቃልና በሕይወት የሚጥሩ፣ እምነታቸውን አለ ፈረቃ የሚኖሩ፣ በቃልና በተግባር ክርስቲያን የሆኑ፣ እምነታቸውን በተግባር የሚኖሩ ሕዝብን ወደ ኢየሱስ የሚማርኩ፣ የሚጮኸውን ድህነት ጸጋ መንፈሳዊና አካላዊ ጤና የሚያስፈልገውን ወደ ጌታ የሚያቀርቡ  እምነታቸው የሚኖሩ ክርስቲያን።

የኅሊና መርመራ

ቅዱስነታቸው ያስደመጡት ስብከት ውዶቼ የዛሬው ቃል ኅሊናችን እንመረምር ዘንድ ይጠራናል። ክርስትያንነታችን ምን ተመስሎው እንመርምር፣ እርዳታ ፈልጎ የሚጮኸውን ወደ ኢየሱስ የሚያቀርብ ወይንም ከኢየሱስ የሚያርቅ ክርስትና የሚኖሩ ነን? በሚል ጥያቄ ማጠቃለላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.