2015-05-27 16:34:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የዓለም ክርስቲያኖች ማየቱ እንዴት ያሳዝናል


እ.ኤ.አ. ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል ዕለቱ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፊሊፖ ነሪ የምታከብርበት ዕለት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው የእዕለቱ ምንባብ ላይ ተንተርሰው ክርስቲያን በሕይወት አንድ ሥር ነቀላዊ ምርጫ እንዲያደርግ የተጠራ እንጂ ክርስትናዊ ሕይወቱን በማፈራረቅ እንዲኖር የተጠራ አይደለም፣ ክርስቲያን መሆንና አለ መሆን ባንድ ላይ አጠቃሎ መኖር አይቻልም፣ ሰማይና መሬት ባንድ ላይ አጠቃሎ ለመኖር እንደማይቻል ባስደመጡት ስብከት ገልጠው፣ ያ ሃብታም ወጣት የዘለዓለም ሕይወት አገኝ ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል ሲል ላቀረበው ጥያቄ አስርቱ ትእዛዛት ብቻ ሳይሆን ያለህ ምድራዊ ሃብት ሁሉ ለድኾች ስጥ፣ የተከማቸ ሃብት በሰማይ ታገኝ ዘንድ የሚል መልስ ከኢየሱስ ልክ እንዳገኘ ጴጥሮስ በመቀጠል ኢየሱስን እንተን መከተል ትርፋችን ምንድር ነው ሲል ይጠይቀዋል፣ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ወቅታዊነቱ የማይሟጠጠው ቃለ ወንጌል አበክረው፦

ክርስቲያን ሰማይንና ምድርን የሚያጠቃልል አይደለም፣ ለምድራዊ ሃብት የተገዛ አይደለም

ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ስለ ሃብት ሳይሆን የእግዚአብሔር መንግሥት ስለ መውረስ ጉዳይ ይነግራቸዋል። የእግዚአብሔር መንግሥት በስቃይና በመስቀል መንገድ የሚወረስ ልዩ ሃብት መሆኑ ይገልጥላቸዋል። ስለዚህ አንድ ክርስቲያን በምድራዊ ሃብት ላይ ሙጥኝ ሲል ሰማይንና ምድርን አጠቃሎ ለመያዝ ሲፈልግ ማፈሪያ ክርስቲያን ሆኖ ይቀራል። መስቀል ስደት የእግዚአብሔር መንግሥት ለመውረስ የሚመሩ መንገዶች ናቸው፣ ይኽ ማለት ደግሞ ገዛ እራስን መካድ፣ ዕለት መዕለት መስቀልን መሸከም፣ የደቀ መዛሙርት ፈተናም እርሱ ነው። አዎ ኢየሱስን መከተል ይመርጣሉ ነገር ግን የዚህ ምርጫ ገቢውና ትርፉ ምን ይሆን የሚለው ጥያቄ ማሰላሰል ይወዳሉ እንዲህ መሆኑም የያዕቆብና የዮሓንስ እናት እናስታውስ፣ ኢየሱስ በእርሱ ዘንድ ለልጆችዋ የላቀ የበላይ ስፍራ እንዲሰጣቸው ትጠይቃለች፣ አንዱን ቀዳሜ ሚኒስትር ሁለተኛው ደግሞ የኤኮኖሚ ሚንስትር፣ ኢየሱስን በመከተል ምርጫ የሚኖር ሕይወት የዓለም አመክንዮ የሚከተል አይደለም።

በኢየሱስ የእነዚያ ደቀ መዛሙርት ልብ ይነጻል፣ እርሱም በጰራቅሊጦስ ዕለት ሁሉንም ይገለጥላቸዋል። ኢየሱስን በነጻነት መከተል፣ በነጻ የሚሰጥ የድህነት ፍቅር፣ ከኢየሱስ ከድኽነት ጋር ወይንም ከዓለም ከሃብት ጋር አንዱን መምረጥ ነው ወዳጆቼ። አንዱን ከመምረጥ ይልቅ ሁሉን አግበስብሶ የሚኖር የፈረቃ ክርስቲያን መሆን አይቻልም።

ሃብት ከንቱነት ትዕቢት ከኢየሱስ የሚያርቁ መንገዶች

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ነቢይ ኤሊያስን ጠቅሰው፣ በሁለት እግሮች እያነከሱ መሄድ፣ የትኛውን መምረጥ ያዳግታል፣ የሚፈልገውን የማያውቅ፣ ኢየሱስ ግን የፊተኞች ኋለኞች የኋለኞች ፊተኞች ይሆናሉ ሲል ግሉጽን ነገሮናል። ትልቅ መሆን የሚፈልግ ካለ የሁሉም አገልጋይ ይሁን፣ ትልቅነት የሚመዘነው በአገልጋይነት እንጂ በተገልጋይነት አይደለም። የተናናሾች ሁሉ አገልጋይ።

በሰብአዊ ዓይን ሲታይ ኢየሱስን መከተል ትርፍ የለውም፣ ማገልገል የሚል ነውና። ኢየሱስ ፊተኛ የመሆን ጸጋ ካደለይ የኋለኛ ሆነህ መኖር አለብህ። ሃብት ያደለህ ከሆንክ አካፍሎ ተካፍሎ ለመኖር ተጠርተኻል ማለት ነው። ከኢየሱስ የሚያርቁን ሶስት ደረጃዎች አሉ ሃብት ከንቱነትና ትዕቢት፣ ሃብት ወደ ከንቱነት ይመራል፣ መታበይን ያስከትላል፣ ገዛ እራስ ከፍ ከፍ በማድረግ በመኖር ለሚያጋጥም ውድቀት ይዳርጋል።

የዓለም የሆነ ክርስቲያን ጸረ ምስክርነት ነው

በኢየሱስ የተመለከተው መንገድ ገዛ እራስ ዝቅ የማድረግ ልክ እርሱ እንዳደረገው ቀዳሚ መሆን የሚፈልግ የሁሉም አገልጋይ ይሁን የሚል ገዛ እራስ ባዶ ማድረግ የሚል ነው፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በዚህ መንገድ ነው ያነጻቸው። ነገሩን ቶሎ ሊረዳቸው ባለ መቻሉም ለማስገንዘቡ ረዥም ዓመታትና ጊዜም ፈጀበት፣ ውዶቼ ጌታ ኢየሱስ ባመለከተው መንገድ እንድንራመድ ዘንድ ኃይሉን እንዲሰጠን እንለምነው፣ የኋለኛ የመሆን ጥበብ ወንድሞችንና የእህቶችን በቤተ ክርስቲያን የማገልገል ጥበብ።

ካህን ጳጳስ ገዳማዊ ዓለማዊ ምእመንም ይሁን ሁላችን ክርስቲያኖች ነን። ክርቲያን ዓለምንና ኢየሱስ ሲከተል ማየቱ ምንኛ ያሳዝናንል፣ ክርስቲያን አንዱን ለመከተል የተጠራ እንጂ ሁሉን አጣምሮ ለመኖር የተጠራ አይደለም። ሁለቱን አጣምሮ መኖር ጸረ ምስክርነትና ሰዎች ከኢየሱስ የሚያርቅ መንገድ ሆኖ መገኘት ማለት ነው። ሁሉን ነገር ትተን ተከትለንሃል ክፍያችን ታዲያ ምንድር ነው? ትርፉስ ምንድር ነው? ትርፉ እርሱን መምስል ነው፣ ወደር የማይገኝለት እጅግ የላቀ ክፍያም እርሱን መምሰል። ኢየሱስን መምሰል። በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.