2015-05-25 16:49:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በዓለም የሴቶች ተሰጥኦ በሙላት መገለጥ አለበት


እ.ኤ.አ. ከግንቦት 22 ቀን እስከ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ካቶሊካውያን ሴቶች ማኅበርና ስለ ሕይወትና ቤተሰብ ቃል ኪዳናዊ የሴቶች ማኅበር በመተባበር ያዘጋጁት ሴቶች ወደ ድኅረ 2015 ዓ.ም. የልማት ዕቅድ በሚል ርእስ ሥር የተመራ ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ መካሄዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኮድዎ አፒያ ቱርክሶን አማካኝነት ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት ይኽ ተቀባይነት ያለው የልማት እቅድ ተጋርጦው በመለየት በዚሁ ዙሪያ የሴቶች ብቃትና ተሳትፎ ላይ አተኩሮው በማኖር የተወያየው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ሕይወት ቤተሰብ ልማት፦ የሰብአዊ መብትና ክብር በማነቃቃት ረገድ የሴቶች ሚና በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው አንደኛው ጉባኤ ያስገስኘው ውጤት የዳሰሰ ጭምር መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታውቁ።

ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ማክበርና መከላከል

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለተግባእያኑ ባስተላለፉት መልእክት፣ ሁሉም ለሕይወት መብትና ክብር በመቆም ሕይወት ከመጸነጽ እስከ ባህርያዊ ሞት በክብርና ከሁሉም ስቃይ ማለትም ከእርሃብ ዓመጽና ስደትና መከራ ነጻ ሆኖ እንዲኖር ይደገፍ ዘንድ በማሳሰብ፣ ጉባኤው ካቶሊካውያን ሴቶች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚሰጡት አስተዋጽኦና የሚያነቃቁት የሕይወት ክበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድኽነት ለማጥፋት እ.ኤ.አ. 2015 ዓ.ም. እግብር ላይ የሚውል የልማት ዕቅድ ርእስ በማድረግ ድኅረ 2015 ዓ.ም. የልማት ዕቅድ ላይ በማነጣጠር ፍቅር በሓቅ የተሰኘው የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ጠቅሰው የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት ጋር ውስጣዊ ግኑኝነት ያለው አገልግሎት ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።

በዓለም የሴቶች ተጋርጦና ችግር

ሴቶች በዓለም ያለባቸው ተጋርጦና ችግር ሰፊና የተለያየ ነው። አሁንም ቢሆን በዚያ ነጻ በሚባለው በበለጸውገው ምዕራቡ ዓለም በሥራ መስክ አድልዎ እንደሚያጋጥማቸው ቅዱስ አባታችን ባስታላለፉት መልእክት ጠቅሰው፣ ብዙውን ጊዜ ቤተሰብ እጮኛ እናት ሚስት የቤተሰብ እናት መሆን ወይንም ሥራ እንዲመርጡ፣ አንዱን ብቻ እንዲመርጡ ሲገደዱ ይታያል። ብዙ ሴቶች እናት አያት ሳይሆኑ እንዲቀሩ የሚያስገድድ ሁኔታ ተደቅኖባቸው ይታያል። በደቡቡ ዓለም ሴቶች ቤተሰብ በእርሃብ በጥማት እንዳይሰቃይ የሚያስቡ የቤተሰብ ጥም ለማርካት ላይ ታች ሲሉ የሚሞቱ ልጅ በመገላገል ላይ እያሉ የሚሞቱ፣ ቤተሰብ ውሳኔና ፍላጐት አማካኝነት ባስገዳጅ ሲዳሩ ይታያል፣ ሴቶች በመሆናቸው ብቻ ፍላጎታቸው የመግለጥ መብትና ክብር ተነፍገው ለተለያየ ችግር እንደሚዳረጉ ማስታወሳቸው አኵይላኒ ገለጡ።

በዓለም የሴቶች ተሰጥኦ በሙላት መገለጥ አለበት

እግዜብሔር ሴት ልጅን በጸጋው አትረፍሯታል፣ ሌላውን የመረዳት ጥልቅ አስተዋይ ግጭት አለ መግባባት ባለበት ወቅት የማስታረቅ ብቃት የተካነች የሌላው ስቃይና ቁስል በማኅበራዊ ደረጃም ይሁን የመፈወስ የማቅለል ልዩ ብቃት የታደለች ምኅረትና የዋህነት የታደለች ነች። ሴት ይኸንን ሁሉ የታደለቸውን የእግዚአብሔር ጸጋ በሙላት እግብር ላይ እንዲውል ብትደገፍና ይኽ ያላት ተሰጥኦ በሙላት በዓለም ቢገለጥ ለሁሉም የሚበጅ ነው። የዚህ ጸጋ ተጠቃሚው እያንዳንዱ ዜጋና ማኅበረሰብ ይሆናል በማለት ቅዱስ አባታችን በመልእኽታቸው ሁሉም የሴቶች መብትና ክብር ጥበቃ ዘርፍ ተሰማርተው የሚያገለግሉት ማኅበራት የሴቶች መብትና ክብር የሚያነቃቁ ሁሉ በሰብአዊነት መንፈስ ተመርተው ወዳጅን ጎረቤትን ማገልገል የሚጠመዱ እንዲሆኑ አደራ ብለው። ከዚህ ጋር በማያያዝም የሚሰጡት አገልግሎት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት ሥነ ባህላዊ ብቃት እንዲሁም ርህራሄና የዋህነት የተካነ ሲሆን የተትረፈረፈ ውጤት ያስገስኛል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።
All the contents on this site are copyrighted ©.