2015-05-22 16:49:00

ደቡብ ሱዳን፦ እጅግ አስጊ ሁኔት


ሁለት ሳምንት ባልሞላው የጊዜ ገደብ ውስጥ በደቡብ ሱዳን ተከስቶ ባለው የርእስ በእርስ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ሕጻናት መገደላቸው፣ መታገታቸውና ለተለያየ ጸያፍ ተግባር መጋለጣቸው፣ ለውትድርናው ዓለምና ለአመጽ መዳረጋቸው የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት የሰጠው መግለጫ ሲያመለክት፣ ይኽ በዚያች በመንግሥት ወታደሮችና የደቡብ ሱዳን ነበር ርእሰ ብሔር ራይክ ማቻር ደጋፊያን ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተቀጣጠለው ግጭት እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በዚያ ክልል ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙት ለራስ ደኅንንደት ስማቸው ያልተገለጠው አንድ ወንጌላዊ ልኡክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባክሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቅል ድርጅት ልኡካን የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑት የተራድኦ ማኅበር አባላት ልኡካነ ወንጌል አገሪቱን ለቀው ለመውጣት እየተገደዱ መሆናቸው አስታውቀዋል።

በደቡብ ሱዳን ያለው ሁኔታ ከሚያዝያ ወር ወዲህ እጅግ እየከፋ መምጣቱ የለጡት ልኡካነ ወንጌል አባል አክለው፣ የውጥረቱ ምክንያት በነዳጅ ድፍድፍ ማእድን ሃብታም የሆነውን ክልል ለመቆጣጠር የሚል፣ የሥልጣን ሽኩቻ ጭምር ያቀጣጠለው መሆኑ ገልጠው፣ ተከስቶ ባለው ግጭት ሳቢያ ለሞት አደጋ የሚጋልጠው ቤቱንና ንብረቱን አጥቶ ለመፈናቀል አደጋ እየተጋለጠ ያለው ሕዝብ ብዛት ቍጥር ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ ነው ብለው፣ እርሃብ እየተዛመተ በመሆኑም ሕዝቡ ከዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት የሚያቀርበው የምግብ እርዳታ ተጠባባቂ ሆኖ፣ በጦርነት በእርሃብ ለሞት የሚዳረገው ሕዝብ ብዛት ለአመጽ የሚዳረጉት ሴቶችና ላቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናት ሴቶች ለወሲብ አመጽ መጋለጣቸው ገልጠዋል።

የሥልጣን ሹኩቻ ያነቃቃው ጦርነት ወደ የጎሳ ግጭት እያዘገመ፣ የሚያሳዝነውም አዲሱ ትውልድ እንዲህ ባለ ሁኔታ ገና ከወዲሁ እምሮው በመበከል የአገሪቱ መጻኢ የሚያኮላሽ ሁኔታ ሲስፋፋ ማየቱ፣ ስልጣን ጎሰኝነት ከአገርና ሕዝብ ጥቅም በላይ አመዝኖ ማየቱ እጅግ ያሳዝናል። ስለዚህ ይኸንን ሁሉ ግምት በመጠት የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ባስቸኳይ የደቡብ ሱዳን ሁኔታ መፍትሄ እንዲያፈላልግ አደራ በማለት ሁሉም ስለ ደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲጸልይ ተማጥነው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.