2015-05-22 16:45:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የትህትና ጸጋ በመኖር ከፋፋይ መንፍስ በጽናት መቃወም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ግንቦት 21 ቀን በመቀጠል የኢየሱስ ስቃይ ቤተ ክርስቲያን በእርሱና በእግዚአብሔር አንድ ትሆን ዘንድ የተለፈለ ዋጋ ነው። ስለዚህ የወቅቱ ክርስቲያኖች የአንድነት ጸጋ ለመማጠንና በመካከላቸው ከፋፋይ መንፈስ ሽኩቻ ውግያ ምቀኝነትና ቅናት ሰርጎ እንዳይገባ በጽናት የክፋት መንፈስ የሚዋጋ ነው። በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ አስተንትኖ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትልቁ ጸሎት እርሱ ከአባቱ ጋር እንዳለው አንድነት ቤተ ክርስቲያንም አንድ ትሆን ዘንድ፣ ክርስትያኖች አንድ እንዲሆኑ የሚል ነው። የዚያ የኃሰትና የመከፋፈል መንፈስ አባት ለሆነው የኃሰት መንፈስ ፋታ አትስጡ በማለት፣ ወደዚያ የጽርሃ ጽዮን መንፈስ ሁኔታና በዚያ ሥፍራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስቃይና ለመስቀል ሞት ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት ለደቀ መዛሙርት በአደራ የሰጠው ቃል በጥልቀት በማስተዋል በሰጡት ጥልቅ ስብከት፦

የአንድነት ክቡር ዋጋ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቱ ስለ ደቀ መዛሙርት ብቻ ሳይሆን በእርሱ ቃል ስለሚያምኑት ሁሉ እንደሚጸልይ ያረጋገጠው ቃል እንዴት አጽናኝ ነው። ይኽ ቃል ብዙውን ጊዜ ሰምተነዋል፣ እስቲ ዛሬ በጥልቀት እናስተውለው አደራ። ሁላችን ኢየሱስ የተናገረውን ቃል ልብ እንላለን ወይ? ኢየሱስ ስለ እኛ፣ ስለ እኔ ጸልየዋል ይጸልያልም። ይኽ ደግሞ በእርሱ ላይ ለሚኖረን እማኔ መሠረት ነው። እግዚአብሔር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቁስልና ግርፋት ያያል፣ ይኽ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትልቅ ጸሎት ነው። ይኽ ደግሞ እርሱ ስለ እኛ ለመጸለይ የከፈለው መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ ነው። በስቃዩና በልቡ ስለ እኔ፣ ስለ እኛ ጸልየዋል፣ አሁኑም ይጸልያል።

የመከፋፈል ገጽታ

ኢየሱስ ስለ ሕዝበ እግዚአብሔር አድነት ስለ ቤተ ክርስቲያን አድነት ይጸልያል። ሆኖም ኢየሱስ የዓለም ከፋፋይ የግጭትና የጦርነት የምቀኝነት የመቀናናት መንፈስ በቤተሰብ በመንፈሳዊ ማኅበራትና በገዳማት በሰበካዎች በጠቅላላ በቤተ ክርስቲያን ሳይቀር የሚታየው መንፈስ አቢይ ፈተና የሆነውን ጉዳይ ጠንቅቆ ያወቀዋል። እጅ መቀሰር ሌላውን ማጥላላት ሐሜት የመከፋፈል መንፈስ እንዳይኖር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ወደ አብ አርጓል።

ልክ እንደ ኢየሱስና አባቱ እንድ መሆን አለብን። ይኽ የሁላችን ክርስቲያኖች ተጋርጦ ነው። መከፋፈል መለያየት በመካከላችን ቦታ እንዳይኖረው እንጠንቀቅ፣ እንትጋ፣ ለከፋፋይ መንፈስ ለኃሴት አባት በመካከላችን እድል አንስጥ፣ ዘወትር አንድነትን እንሻ፣ እያንዳንዱ እንደ መሆኑ በቤተ ክርስትያን መኖር፣ አንተን የማረው ኢየሱስ እንዴት ሌላውን አይምርም? ሁሉም የማረ ጌታ ነው። እንድ እንድንሆን ስለ እኛ ጸልየዋል። ቤተ ክርስቲያን ይኽ ጸሎት እጅግ ያስፈልጋታል።

አንድነት ጸጋ እንጂ ሙጫ (ማጣበቂያ) አይደለም

አንድነት በሙጫ ተጣብቆ የሚከወን አይደለም፣ ኢየሱስ የሚጠይቀው አንድነት አንድ መሆንን፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ስለዚህ በዚህ ምድር እስካለን ድረስ አንድ ለመሆን መታገል አለብን አንድ የመሆን ትግል። ይኽ ማለት ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ መስጠት ማለት ነው። ምክንያቱም እርሱ ልክ በአብና በወልድ ዘንድ ወዳለው አንድ መሆን ይለውጠናል ያሉት ቅዱስ አባታችን ያስደመጡት ስብከት ሲያጠቃልሉ፦ ኢየሱስ በእርሱ እንሆን ዘንድ አደራ ብሎ ነው ወደ አባቱ ያረገው። በእኔ ሁኑ፣ በእርሱ መሆን፣ ሁላችን በእርሱ እንሆን ዘንድ ይኸንን ጸጋ አባቱ ይጸግወን ዘንድ እንጸልይ። አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለወደድኸን የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸንም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ። ኢየሱስ ስለ እኛ እንዲህ በማለት ነው ወደ አባቱ የጸለየው። ሁሉም የእርሱን ክብር ካለ ማቋረጥ ያስተነትን ዘንድ እርሱ በአባቱ እንዳለ ሁሉ እኛም በእርሱ እንድሆን እንጸልይ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.