2015-05-13 16:35:00

የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት፦ ውይይት ከምስልምና ሃይማኖት ጋር


የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ውይይት ከምስልምና ሃይማኖት ጋር በሚል ርእስ ዙሪያ ያዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን በማሳተፍ እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. በስዊዘርላንድ መጀመሩ የቫቲና ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ስለ ዓውደ ጉባኤው በማስመልከት የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ምስልምና ሃይማኖት በኤውሮጳ ለተሰኘው የተግባር ቡድን አስተባባሪ የዚህ በስዊዘርላንድ በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ ሂደት መሪ የቲዮሎጊያ ሊቅ አባ አንድረያ ፓቺኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የዚህ ዓውደ ጉባኤ ፍጻሜ በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች በትክክል ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር ውይይት ለማነቃቃት ያለመ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለማዘጋጀት ከሚል ካንድ ቀጣይ ጥናት ከውይይትና ግኑኝነት የመነጨ በመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ዘንድ የዛሬ ስድስት ዓመት በፊት የተነቃቃ መሆኑ ገልጠው። ይኽ በስዊዘርላንድ የሚካሄደው ዓውደ ጉብኤ አራተኛ ሲሆን፣ የምስልምና ኃይማኖት ላይ በማተኮር የሚወያይ በየሁለት ዓመት የሚዘጋጅ ዓውደ ጉባኤ መሆኑም ገልጠው፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ የስዊዘርላንድ ዓውደ ጉባኤ በፈረንሳይ የምስልምና ኃይማኖት ተከታዮች ወኪል ኦመሮ ሞሩንጒይ ፐሪያ በመሳተፍ በኤውሮጳ ዓውደ ሁነት በሂደትና በማደግ ላይ የሚገኝ አክራሪ የምስልምና ኃይማኖት አለ ወይ? የተሰኘ ጥያቄ ዙርያ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ከወዲሁ ገልጠዋል።

በአሁኑ ወቅት ጅሃዳዊነት በፖለቲካና በወታደራዊ ኃይል አማካኝነት እየተገለጠ ከመሆኑም ባሻገር ጅሃዳዊነት በመቀበል ከኤውሮጳ የተወጣጡ የምስልምና ሃይማኖ ተከታይ የኤውሮጳ ዜጎች ጭምር በማሳተፍ በተለያየ የዓለማችን ክልሎች ውጥረትና ግጭት እያስፋፋ ነው። ስለዚህ ይኽ ዓይነቱ አክራሪነት መነሻው መሠረታዊ ምክንያቱ ምን ይሆን ለሚለው ጥያቂ መልስ ለመስጠትና የዚህ ዓይነቱ ማለትም የአክራሪነት ጉዳይ ከወዲሁ ለመግታት እንዲቻል በኤውሮጳ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በኤውሮጳ ከሚገኘው ከምስልምና ኃይማኖት ጋር በተለያየ መልኩ ውይይት እያሳደግች ትገኛለች። ለመወያየት ሁለቱ ተወያዩ አካላት ሊተዋወቁ ግድ ነው፣ ይኽ ውይይት የሕይወት ውይይት እርሱም የሕይወት ባህል ማእከል ያደረገ በመሆኑ ከገጠመኝ የሚንደረደር ነው። በኤውሮጳ ይዘት ለሚኖሩት ለካቶሊክና ለምስልምና ኃይማኖት ተከታዮች የሚያገናኝ ሥፍራ ለመፍጠር ያለመ መርሃ ግብር ነው። በፈረንሳይ በሊዮንና በማርሲሊያ ሰበካዎች በተለያዩ ማኅበራዊ ርእሰ ሥር የሁለቱ ኃይማኖት ተከታዮች በማገናኘት የሚከናወን አወያይ መርሃ ግብር አስፈላጊ መሆኑ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።

 

የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች ሁለተኛው የጋራ በዓል 2015

እ.ኤ.አ. ከግንቦት 15 ቀን እስከ ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሁለተኛው የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች የጋር በዓል አብረን ወደ ባሻገር እንጓዝ በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ በኢጣሊያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ድጋፍ አማካኝነት እንደሚካሄድ የቫቲካን ረድዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድራያና ማሶቲ ገልጠው፣ ይኽ የጋራው በዓል በዓለማችን የሚታየው ኃይማኖት መሠረት ያደረገ ግጭትና ውጥረት አክራሪነት አሸባሪነት ጸረ ኃይማኖት መሆኑና ብዙኅነት እሴት እንጂ የግጭት ምክንያት ሊሆን አይችልም የተሰኘው እማኔ በማረጋገጥም፣ በኃይማኖትና በባህል የተለየውን ማጥፋት ጸረ ሰብአዊ መሆኑ ለማስተጋባት ያቀደ በዓል መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የዚህ በፊረንዘ የሚካሄደው ሁለተኛው በዓል አስተባባሪ ፍራንቸስካ ካማፓና ኮምፓሪኒ ገልጠው፣ በዚህ በዓል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያሪ ብፁዕ ወቅዱስ ታዋድሮስ ሁለተኛ በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፉዋድ ትዋል፣ የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ስታይንሳልትዝ እንዲሁም ከተለያዩ ሃይማኖቶች የተወጣጡ ምሁራን፣ የፖለቲካ አካላት እንደሚሳተፉ ገልጠዋል።

አብረን ወደ ባሻገር እንጓዝ የተሰኘው የዘንድርው በዓል ርእሰ ጉዳይ ካሸባሪነት ካክራሪነት ከኃይማኖት ግጭት ከዘረኝነት፣ ሰው ላደጋ ከሚያጋልጥ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ሁሉ ወዲያ አንመልከት፣ ወዲያ ስንመለከት ሰብአዊነት ጋር እንገናኛለን፣ ምንም’ኳ በባህል በኃይማኖት በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ቢኖርም፣ በሰብአዊነት መሆን ያለው ውሁደት የሚያነቃቃ በዓል ነው ብለዋል።

በኃይማኖቶች መካከል የሚታየው ልዩነት የግጭት ምክንያት ሳይሆን ከላቀው እሴት ጋር ለመገናኘት ውበትን ለማስተንተን የሚያግዝ፣ ሁሉም በጋራ በሰላም ለመኖር እንዲችል የሚደግፍ መሆን አለበት። ስለዚህ ይኽ የፊረንዘ በዓል የኃይማኖቶች ልዩነቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ገልጠው፣ ያለው ልዩነት ለመተዋወቅ ለመቀራረብና ለወንድማማችነት የሚያነቃቃ የሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች መለያ ማቀብ ለኃይማኖታዊ ግጭት ምክንያት ሊሆን እንደማይችልና፣ ሁሉም ፍጻሜ ላይ በማተኮር አብሮ ወደ ባሻገር የላቀው ላይ በማተኮር አብረው ለመጓዝ የተጠሩ መሆናቸው የሚያበክር በዓል ነው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.