2015-05-13 16:46:00

አይቮርይ ኮስት፦ ብሔራዊ ዕርቅ


የአይቮርይኮስት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በ 2015 ዓ.ም. በአገራቸው የሚካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ ምክንያት የአገር አንድነት እርቅና ሰላም ትጥቅ መፍታት የተለያዩ የፖለቲካ ሰልፎች በውስጣቸው አንድነት እንዲያጸኑ፣ እውነትን መከተል፣ ፍትህ እኩልነት ይቅር መባባል ለአገር ሰላምና አንድነት ወሳኝ መሆኑ የሚያስገነዝብ መልእክት ማስተላለፉ የአይቨርኮስት ብፁዓን ጳጳሳኣት ምክር ቤት መግለጫ ይጠቁማል።

ከሕዝባዊ ምርጫው በኋላ እ.ኤ.አ. ከ2010 እስከ 2011 ዓ.ም. የታየው ሦስት ሺሕ ያገሪቱ ዜጋ ለሞት የዳረገው ውጥረትና ግጭት ዳግም እንዳይከሰት ጥሪ ያስተላለፈ መልእክት ሲሆን፣ ያለፈው አገርና ሕዝብ ለስቃይ የዳረገው ውጥረት በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት ሊካሄድ ከታቀረበው ምርጫ በኋላ ሊቀሰቀስ የሚቻል መሆን ከወዲሁ የሚያስገነዝብ ሁነት መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት በማስጠንቀቅ፣ የአገርና የሕዝብ ጥቅም በማስቀደም የፖለቲካ አካላት የሕዝብ ድምጽ የሚያረጋግጠው ውሳኔ በመታዘዝ እግብር ላይ የሚያውሉ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ ያስተላለፈ መልእክት መሆኑ የአይቨሪኮስት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግልጫ አስታወቀ።

መንግሥትና ተቃዋሚው የፖለቲካ ሰልፍ

የአይቮርይኮስት ብፁዓን ጳጳሳት እ.ኤ.አ. ከግንቦት 4 ቀን እስከ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው 101 ኛው ዓመታዊ ጠቅላይ ጉባኤ ፍጻሜ ባወጣው ሰነድ  ምንም’ኳ በአገሪቱ ማኅበራዊ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደግፍ የውይይት የእውነትና የእርቅ ድርገት አማካኝነት ብዙ ውጤት የተጨበጠ ቢሆንም ቅሉ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በመንግሥትና በተቃዋሚው የፖለቲካው ሰልፍ መካከል ያለው የአለ መተማመን አዝማሚያ ከፍ እያለ ይኽ ደግሞ የእርሻ ፖለቲካ ጉዳይ እንደ አብነት በመጥቀስ የሕዝብና የአገር ጥቅም ባተኮረ ውይይት አማካኝነት መፍትሔ እንዲያገኝ ካልተደረገ የውጥረትና የግጭት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የጉባኤ የፍጻሜ ሰነድ እንዳስገነዘበ የአይቮርይኮስት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ አስታወቀ።

ለመገናኛ ብዙሃንና ወጣት የሰላም ጥሪ

የአይቮርይኮስት ብፁዓን ጳጳሳት በጉባኤው የፍጻሜው ሰነድ ጋዜጠኞች ባጠቃላይ የመገናኛ ብዙኃን በሚያቀርቡት ጽሑፍና ሐተታ በሚሰጡት ዜና አማካኝነት የግጭትና የውጥረት መንስኤ ከመሆን ተቆጥበው አለ ምንም ፖለቲካዊ ጥቅምና ፍላጎት የእውነት አገልጋይ በመሆን መንግሥትና ተቃዋሚው የፖለቲካ አካላት ያለባቸው አቢይ ኃላፊነት የሚያበክር እርሱም ሕዝብና አገር ማገልገል ማለት መሆኑ በማብራራት የሰላም መሣሪያ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ ማቅረባቸው ከአይቮርይኮስት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተሰራጨ መግለጫ ይጠቁማል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.