2015-05-11 15:54:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለሞዛምቢክ ብፁዓን ጳጳሳት፦ የግኑኝነት ባህል አነቃቁ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቪሲታ አድ ሊሚና እርሱም፦ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት በየአምስቱ ዓመት በቫቲካን ሓዋርይዊ ጉብኝት ለማከናወንና ከመንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ያላቸው ውህደት ለመመስከር ብሎም ለማጽናት፡ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸው ለመመስከር እዚህ ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለመሳለምና የቤተክርስትያናቸው ወቅታዊና አንግብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች በማስድገፍ ከቅዱሱ አባታችን ጋር በመነጋገር መሪ ቃል የሚቀበሉበት ሐዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት ቅድስት መንበር የገቡትን የሞዛምቢክ ብፁዓን ጳጳሳት ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።

ቅዱስነታቸው ከሞዛምቢክ ብፁዓን ጳጳሳት በሞዛምቢክ ስለ ምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነት ዘርአ ክህነት ተማሪዎች ብሎም ስለ ሞዛቢምክ ወቅታዊ ሁኔታ ከተወያዩ በኋላ በለሰጉስት መሪ ቃል፦ ውጥረትና ግጭት የሞዛምቢክ ማሕበራዊ ጉዳይ ለአደጋ ያጋለጠ ሲሆን፣ በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከዚያ ስቃይ ብቸኝነት የተወሳሰበ ማሕበራዊና ሰብአዊ ችግር ከሚታይበት የከከተሞቻችንና የህልውና ጥጋ ጥግ ክፍል ከሚገኙት ምእመናን ጀምራ በምታቀርበው የቃልና የሕይወት ምስክርነት አማካኝነት ከአገሪቱ መንግሥት ጋር የሕይወት ባህል ጥበቃ፣ ቤተሰብ ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ትተባበር ዘንድ ማሳሰባቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ፦ ውጥረትና ግጭት ምንኛ የሞዛምቢክ ማኅበራዊ ዘርፍ፣ ቤተሰብ የወጣት ትውልድ መጻኢ ለከፋ አደጋ ማጋለጡ አስታውሰው፣ ይኽ እ.ኤ.አ. ከ 1990 ዓመታት ጀምሮ በአገሪቱ የሚታየው ውጥረት ለርእር በእርስ ጦርነት እንደዳረጋትም አስታውሰው፣ ይኽ ችግር ያዛመተው ጸረ ሰብአዊ ተግባር የትዕቢት የእኩልነት መጓደል ማህበራዊ መከፋፈል የመሳሰሉት ችግሮች የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳትና በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ካለ ማመንታት ወንጌላዊ ኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን ጠቅሰው ወጣቱ ትውልድ የማመዛዘን ሁኔታዎች በጠቅላላ በአተኵሮ ለማጤንና እሴቶች እግብር ላይ ለማዋል እንዲችል አብራ በመጓዝና በማነጽ ትቃወም ዘንድ አደራ፣ ይኽንን ለማነቃቃትም በመናብርተ ጥበብና በትምህርት ቤቶች ሕንጸትና አስፍሆተ ወንጌል በማጣመር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንድታነቃቃ ማሳሰባቸው አስታወቁ።

ሕይወትና ቤተሰብ በመከላከል ዓላማ ከመንግሥት ጋር መተባበር

በፖለቲካው ዓለም የሞዛምቢክ ብፁዓን ጳጳሳት ከአገሪቱ መንግሥት ጋር መልካም ግኑኝነት እንዲኖራቸው ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን ይኽ ማለት ደግሞ የፖለቲካና የመንግሥት ጥገኞች መሆን ማለት ሳይሆን፣ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት የሚል እሴት ላይ የጸና ቤተሰብና የሕይወት ባህል ጥበቃ ዘርፍ ጤናማ ትብብር እንዲኖራቸው ማለት መሆኑ አብራርተው፣ ወንድማማችነት ሰላም ለማረጋገጥና እርስ በእርስ ለመከባበር የታደለ ሁነት መሆኑ እንዳበከሩም ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ ገለጡ።

ቤተ ክርስቲያን ከተፈናቃዮች ጎን ትሁን

ሞት ስቃይ ውድመት ያስከተለው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት አለ ቤትና ንብረት አለ መጠለያ የቀረው ተፈናቃዩ የሞዛምቢክ ዜጋ ቅዱስ አባታችን ዘክረው፣ ቤተ ክርስቲያን የዚህ ሕዝብ ስቃይና መከራ ተካፋይ በመሆን እንደ ኢየሱስ ወደ ሚሰቃየው ማቅናትና አብራ ለመሆን የተጥራች ነች እንዳሉ አኵይላኒ አስታወቁ።

ውህደትና አድነት የተረጋገጠባት ቤተ ክርስቲያን ወደ ምእመናን ለመድረስ ብቃት ያላት ነች

ቅዱስ አባታችን ለሞዛምቢክ ብፁዓን ጳጳሳት አንድነትና ውህደት አደራ በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ የቤተሰብ መንፈስ እንዲጸና ለውሉደ ክህነት እንክብካቤ፣ ለካህናት ችግር ቅርብ መሆን በተለይ ደግሞ ችግርና ስቃይ ሲያጋጥማቸው ቀርባ መንፈሳዊና ሰብብአዊ ድጋፍ ለማቅረብ ይተጉ ዘንድ አደራ፣ ለችግር ከታጋለጠው ካህን ጋር የሚኖረው ጊዜ ፈጽሞ የባከነ ጊዜ አይሆንም፣ ስለዚህ አደራ ካህናት ለብቻቸው እንዳይተዉ። በዚህ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እየኖረቸው ባለው የውፉይ ሕይወት ዓመት የእምነት ምስክርነትና የአገልግሎት ዓመት እንዲሆን ለድኾች ቅርብ መሆን ሁሉም ገዳማትና መንፈሳዊ ማኅበራት ጭምር ለድኾችና ለተናቁት በሁሉ ዘርፍ ቅርብ በመሆን፣ እምነት በቃልና በሕይወት እንዲመሰክሩ አደራ፣ በመጨረሻም ቅዱስነታቸው ብፁዓን ጳጳሳት ወደ መእመናን እንጂ ምእመናን ወደ እነርሱ እስኪመጡ ካለ መጠበቅ፣ እንደ ኢየሱስ ወደ ሕዝብ በማለት ከምእመናን ጋር በመኖር የጠፋችው በግ ድምጽ ሆነው እንዲገኙ፣ የቅንና የገንቢ ውይይት አብነት እንዲሆኑ በማሳሰብ የለገሱት መሪ ቃል እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አስታወቁ።
All the contents on this site are copyrighted ©.