2015-05-08 16:13:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ፍቅር ተጨባጭና ተገናኝም ነው። ብህትውና ከፍቅር አያገልም


ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል በዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው፦ የፍቅር መመዘኛ ቅዉም ህሳብ ላይ በማተኮር ፍቅር ተጨባጭ ተገናኛ በመሆኑ በማንኛውም ዓይነት ጥሪ የሚኖርና ሲሆን ብህትውና ከፍቅር አያገልም እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እውነተኛ ፍቅር ተጨባጭና ጽኑ ነው

የዕለቱ ከዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 15፣ 12-17 የተነበበው ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ፍቅር እንሆን ዘንድ ይጠራናል፣ በዚህ ምንባብም እውነተኛው ከሃሰተኛው ፍቅር የሚለይ ሁለት ዓይነት የእውነተኛ ፍቅር መመዘኛዎችን እናገኛለን፣ ቀዳሚው መመዘኛ ተግባር የሚል፣ በቃል የሚኖር ሳይሆን በተግባር የሚኖር፣ ይኽ ፍቅር አንዴ ልባችንን ነካ አድርጎ የሚበን ልበ ወለዳዊ ፈጠራዊ ስሜት ሳይሆን በተጨባጭ የሚገለጥ ተግባር ነው። ኢየሱስ የእርሱ የሆኑትን ሲያስጠነቅቅ፣ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚሉ ሳይሆን የአባቴን ፈቃድ ሰምተው የሚፈጽሙ ትእዛዜንም የሚተገበሩ ናቸው መንግስተ ሰማያት የሚገቡት ይላል። እውነተኛው ፍቅር ተጨባጭ ግብርአዊ ጽኑ የዘወትር የማይፈራረቅ ቀጣይ የሆነ ፍቅር የሚል መሆኑም ያስገነዝበናል። ፍቅር ተራ የስሜት ግለት ማለት አይደልም። የጌታ ፍቅር እናስታውስ፣ ስቃይ የሚያጋጥመው መስቀል መሸከም የሚል ፍቅር ጭምር ነው። የፍቅር ተግባር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ማቴዎስ ምዕ. 25 ገልጦልናል፣ የሚያፍቅር የብፅዕና ውል የሚኖር ነው። ውሉም ተጠምቼ ተርቤ ታምሜ … የሚል ነው፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እቅድ የተራራው ስብከት ነው። ሌላ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የለም።

የመጀመሪያው መናፍቅነት በፍጹም ማወቅ ብሎ ነገር የለም የሚለው እግዚአብሔር የሩቅ አምልክ በማለት፣ በተግባር የማይገለጥ ሃሳብ ነው የሚል ነው። ባንጻሩ የአብ ፍቅር ተጨባጭ ፍቅር ነው፣ አንድ ልጁን ሥጋችን ለብሶ ለማዳናችን መላኩ የሚያረጋግጥ ተግባር ነው።

ባህታውያን ገዳማውያን መናንያን

ሁለተኛው የፍቅር መመዘኛውም ፍቅር ተገናኝ ነው የሚል ሲሆን ፍቅር ገዛ እራሱ የሚሰጥና የሚቀበልም ነው፣ ይኽ ደግሞ ተገናኝ መሆኑ ያመለክትልናል። በተገሎ የሚኖር ፍቅር የለም፣ የአብ ፍቅር ከወልድና ለወልድ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ይከወናል። ተገናኝም ይሆናል፣ ገዳማውያን ባህታውያን መናንያን ከፍቅር ተገለው የሚኖሩ አይደሉም። እውነተኛው ፍቅር በተነጠለ ሕይወት እንድንኖር አያደርግም፣ ፍቅር ራስ ወዳድነት ማለት አይደለም።

ፍቅር ያልተወሳሰበ ቢሆንም ቅሉ ቀላል ነው ማለት አይደለም፣ ምክንያቱም ራስ ወዳድነት ማራኪ ነው

በጌታ ፍቅር መሆን በእርሱ ፍቅር መቅረት ማለት የተገናኝ የተወያይነት ብቃት ማለት ነው፣ እርሱም ከጌታ ጋርና ከወንድሞቻችን ከአካባቢያችን መገናኘት የሚል ነው። ይኽ ቀላል ሆኖ እያለ ራስ ወዳድነት ማራኪ በመሆኑ ምክንያት ከባድ ይሆናል። በጌታ ፍቅር መቅረት በእርሱ ፍቅር መሆን ምን ማለት ነው? እምነግራችሁም የእኔ ኃሴት በእናን የእኔ ኃሴት የእናንተ እንዲሆን ነው። ጌታችን ኢየሱስ፦ በአብ ፍቅር የሚኖር ክርስቶስ ደስተኛ ነው ይለናል፣ እኛም በእርሱ ስንቀር ከእርሱ ጋር ስንሆን ደስታችን ሙሉ ይሆናል፣ ይክ ደስታ ከመስቀል ጋር አብሮ የሚመጣ ሊሆንም ይችላል፣ ንገር ግን የጌታ በመሆኑ ሙሉ ደስታ አለው፣ ይኽ ደስታ ማንም ሊነጥቀው እንደማቻለውም ኢየሱስ አረጋግጦልናል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ጌታ ዓለም ሊሰጠው የማይቻለው የኃሴት ጸጋ ያድለን ዘንድ እንጸልይ በማለት የለገሱት ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታወቀ።
All the contents on this site are copyrighted ©.