2015-05-06 16:05:00

የኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያንና የቅዱስ አባታችን ግኑኝነት


የኤውሮጳ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረትና የመላ ኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት ነጻነት በክርስትና እምነት እይታ በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከግንቦት 7 ቀን እስከ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. እ.ኤ.አ. በ 1972 ዓ.ም. ወዲህ በጸናው የጋራ ኮሚቴ አማካኝነት በኢጣሊያ ሮማ ከተማ ምሉእ ዓመታዊው ዓውደ ጉባኤ እንደሚያካሂድ ሲገለጥ፣ የዚህ ዓውደ ጉባኤ ተሳታፊያን እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀትር በፊት ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር እንደሚገናኙ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ነጻነት በክርስትና እምነት እይታ ዘንድ ተመስሎውና ጥልቅ ትርጉሙ የፖሊቲካውና የማኅበራዊው ዓለም ተረድቶት እምነት ለነጻነት መረጋገጥ ድጋፍ እንጂ እክል አለ መሆኑ ማስተዋል እንዲኖረውና በዚህ ሊካሄድ ተወስኖ ባለው ጉባኤ ሃይማኖትና ነጻነት ርእስ ሥር ጥልቅና ሰፊ ትንተናና አስተምህሮ የሚሰጥበት የሚቀርብ ሲሆን፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ምክትል ሊቀ መንበር ብፁዕ ካሪዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በሚስደምጡት ንግግር ተጀምሮ ቀጥለውም የኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት ምክትል ሊቀ መንበር በጎተንበርግ የሲዊድን ቤተ ክርስቲያን የበላይ መንፈሳዊ መሪ መጋቤ ካሪን ቡርስትራድ በመቀጠልም በፓሪስ የኦርቶዶክስ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ እንዲሁም በፓሪስ የካቶሊክ ተቋም መምህር መጋቤ ኒኮላስ ካዛሪያ አስተምህሮ እንደሚያቀርቡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የክርስቲያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ለጉባኤው ነጻነትና ማኅበራዊ እማኔ በሚል ርእስ ሥር እንዲሁም ብፁዕ አቡነ አንጀሎ ማሳርፍራ የቤተ ክርስቲያን ድምጽ በማኅበራዊ መድረክ በሚል ርእስ ዙሪያ አስተምህሮ እንደሚቀርብ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

ጉባኤው የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረትና የኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት በሚያቀርቡት የጋራ ሰነድ አማካኝነት እንደሚጠናቀቅ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ የስምምነቱ ሰነድ ይዞታ የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶና የኤውሮጳ አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ክሪስቶፈር ሂል በጋራ ጋዜጣዊ መገልጫ እንደሚሰጡበት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.