2015-05-06 18:53:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ስለቤተሰብ በምናሰላስለው የትምህርተ ክርስቶስ ጉዞአችን ዛሬ ስለ የክርስትያን ትዳር መልካምነት እንመለከታለን፣ የክርስትያን ቃል ኪዳን በቤተ ክርስትያን በተለያዩ አበባዎች አሸብርቆና ደስ የሚሉ አልባሳት በመልበስ እና የተለያዩ ፎቶግራፎች በማንሳት እንደነገሩ የሚደረግ ሥርዓት አይደለም፣ የክርስትያን ትዳር በምሥጢረ ተክሊል በቤተክርስትያን የሚፈጸምና ለአዲስ የቤተሰብ ማኅበር ምሥረታ ጅማሬ የሚሰጥ ታንሽዋን የቤተሰብ ቤተክርስትያን የሚያማቋቋም ምሥጢር ነው፣

ይህም ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፈውሶን ሰዎች በጻፈው መልእክት ጠቅለል ባለ መንገድ “ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።” (5፤32) ሲል ስለ ምሥጢረ ተክሊል ይናገራል፣ በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍቶ ቅዱስ ጳውሎስ በባልና ሚስት ያለውን ፍቅር በክርስቶስና በቤተክርስትያን መካክል ባለው ፍቅር ይመስለዋል፣ የማይታሰብ ክብር ነው፣ ነገር ግን እንደእውነቱ ከሆነ በእግዚአብሔር የተደነገገው ዓላማ ይህ ነው፣ ብዙ ጥንዶችም ምንም እንኳ ደካማዎችና ኃጢአተኞች ቢሆኑም በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ይህንን እውን አድርገዋል፣

በክርስቶስ የሚገኘውን አዲስ ሕይወት ሲገልጥ ቅዱስ ጳውሎስ ክርስትያኖች ሁላቸው ክርስቶስ እንዳፈቀራቸው እንዲያፈቅሩ የተጠሩ መሆናቸውን እንዲህ ሲል ይገልጠዋል “ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ” (5፡21) ይላል፣ ትርጉሙም አንዱ ለሌላው እንዲያገልግል ይሁን ማለት ነው፣ ከዚህ ቀጥሎ የባልና ሚስት ግኑኝነት ከክርስቶስና ቤተ ክርስትያን ግኑኝነት እንደሚመሳሰል ይገልጣል፣ ፍጹም ያልሆነ ማመሳሰል እንደሆነ ግልጥ ነው ነገር ግን ታላቁና አብዮታዊ የሆነውን መንፈሳዊ ትርጉሙን መገንዘብ አለብን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋ ለሚተማመኑ ባልና ሚስት ምንኛ ያህል ትልቅ ጸጋ በቀላሉ እንደሚሰጣቸውም እንገነዘባለን፣ አያይዞ ቅዱስ ጳውሎስ ባል ሚስቱን “እንደ ገዛ አካሉ” አድርጎ እንዲያፈቅራት ይጠይቃል (ኤፈ 5፡28) ይህም ክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን እንዳፈቀራትና ሕይወቱን ለቤተክርስትያኑ መሥዋዕት እንዳደረገ መሆን አለበት (5፡25) ይላል፣ ወደ በዚሁ አደባባይ ለምትገኙ ባለቤቶች አንድ ጥያቄ ላቅርብላችሁ! ለመሆኑ ይህንን ትረዱታላችሁ ውይ? ማለትም ክርስቶስ ቤተ ክርስትያንን ባፈቀረው መንገድ ሚስቶቻችሁን እንድታፈቅሩ ትጠየቃላችሁ! ይህ ቀልድ አይደለም! ቍም ነገር ነው! ይህ ምሳሌና አምሳል ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌነት ለሴት ልጅ የተሰጠው ፍቅርና መብት የማኅበረ ክርስትያን ታላቁ መግለጫ ነው፣ ይህ የወንጌላዊ ሕዳሴ ዘር የሆነ አንዱ ለሌላው ማበርከት የነበረበትን መሠረታዊ አገልግሎትና አክብሮት ያቀርባል፣ ምሥጢረ ተክሊል ታላቅ የእምነት ሥራ ነው፣ በእግዚአብሔር ፍጥረት ታላቅነትና መልካምነት የማመን ብርታት ምስክርነት በመስጠት እና ይህንን ሁሌ ከገዛ ራስና ከቤተሰብ ወደሌሎች እየሰፋ የሚሄደውን ፍቅር በታማኝነት መኖር ነው፣ የክርስትያን ጥሪ አልገደብና አለመጠን ማፍቀር ሲሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ቃል ኪዳንን በሚያቆም ነጻ ምርጫ ይመሠረታል፣

ቤተ ክርስትያን በእያንዳንዱ የክርስትያን ቃልኪዳን በሙላት ትገኛለች፣ ቃልኪዳኑ የጸናና ፍሬ ያፈራ እንደሆነ ትደሰታለች ያልተሳካ እንደሆነ ደግሞ ታዝናለች፣ ይህ ሲሆን ግን ጠለቅ ያለ አስተንትኖ በማድረግ ገዛ ራሳችንን እንደእረኞችና ምእመናኖች ይህንን ጥያቄ መጠየቅ አለብን፣ ይህ የክርስቶስና ቤተ ክርስትያን የማይፈታ ኪዳናዊ ታሪክ ከቃልኪዳንና የሰውልጆች ቤተሰብ ታሪክ ጋር አብሮ እየተጓዘ ነውን?ይህንን ኃላፊነት ለመቀበልና ለመወጣት ዝግጁዎች ነንን? ማለትም እያንዳንዱ ቃል ኪዳን ክርስቶስ ከቤተክርስትያኑ ጋር ባለው ፍቅር ጐዳና እየተጓዘ ነውን? ይህ ታላቅ ነገር ነው፣

በዚሁ በንጽሕናው በታወቀውና ዳግም በተቋቋመው የፍጥረት ጥልቅ ምሥጥር የምሥጥረ ተክሊል ሁለተኛ ታላቅ አድማስ ይከሰታል፣ ቃል ኪዳን የእግዚብሔርን ሕግ ጠብቆ ለማበሰር ጥልቅ የሆነ እንደ የተልዕኮነት ጥሪ መታዘዝን ይጠይቃል። ይህም ማለት በልባችን የእግዚኣብሔር ብራኬና ጸጋውን ለመቀበል ቦታ መክፈትና መስጠት ማለት ነው፣ ለዚህም ነው ክርስቲያን ሙሽሮች የቤተክርስቲያን ተልዕኮነትን ጥሪያቸውን ይሳተፋሉ፣ ይህንንም ለመፈጸም ድፍረት ያስፈልጋል፣ ለዚህ ነው እኔ አዲስ ለተጋቡ ሙሽሮች ሁሉግዜ እኝው ደፋሮቹ እላለሁኝ ምክንያቱም ሙሽሮች ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንዳፈቀራት ለዘላለም ለመፋቀር ድፍረትና መስዋዕትነትን ስለሚጠይቅ ነው፣

በቃል ኪዳን ስነ ስርዓት የሚከበረው ምስጥረ ተክሊል ከኅላፊነቱ በማስወገድ የሚመሰረተውን የቤተሰብ ጥምረት ከቤተክርስቲያን ታላቅ የፍቅር ተልዕኮ ማራቅ አይቻልም፣ እንዲህ ሲሆን ነው የቤተክርስቲያን ውበትና ሕይወት ሊበለጽግና ሊጠናከር የሚችለው፣ በኃላፊነት ካልተጠበቀና የተልዕኮነትን መሳተፍ ካልተጠበቀ ደግሞ እንዲሁ የቤተክርስቲያን ውበትና ሕይወት ሊወድቅና ሊበላሽ እንደሚችል ነው፣ ቤተክርስቲያን ለሁሉም የእምነት ስጦታዎችዋን ስታካፍል አብረውን የፍቅርና የተስፋ ስጦታዎች ይጠቃለላሉ። ቤተክርስቲያንም ደግሞ ታማኝ ልጆችና ምሥጢረ ተክሊልን በመታዘዝና በመጠበቅ የሚኖሩ ሙሽሮችም ያስፈልጓታል፣ የእግዚአብሔር ልጆች በየዕለቱ በሚጓዙት የእምነት ጉዞ ፍቅር ተስፋ ደስታና ድካም እንደሚያጓጥማቸው ሁሉ በትዳርና በቤተሰብም ውስጥ እንዲሁ እነዚህ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፣

የመንገድ ጉዞ ምንግዜም እንዲህ ነው የፍቅርን መንገድ ከወሰድን ስናፈቅር ክርስቶስ እንዳፈቀር ለዘላለም ይሁን፣ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ከመጠበቅና ከመንከባከብ አይሰለችም በዘላለማዊ ፍቅር ቤተክርስቲያንን ያፈቅራቷል ይጠብቃታል እራሱን እንደሚጠብቅ ይንከባከባታል። ክርስቶስ በሰው ዘንድ የሚገኙትን ያሉትን የተለያዩ ቁስሎችና ሸክሞች ከማንሳት ወደ ኋላ አላለም፣ ይህ ድርጊቱ በጣም ልብ የሚነካና ደስ ሲያሰኝ በውስጣችን ኃይልን በመጨመርና ርሕራሔውን በመግለጥ ከአንዱ ወደ ሌላው ከአንዱ ቤተሰብ ወደ ሌላው ቤተሰብ የሚተላለፍ የፍቅር መግለጫና ሙላት ነው፣ ቅዱስ ጳውሎስ እውነቱን ነው እንዲህ ሲል ይሕ በእውነቱ ትልቅ ምሥጢር ነው፣ ወንድና ሴት ደፋር ልጆቹ ይሕንን የፍቅር ስጦታ ለሌሎች በመመስከር ሲያስተላልፉት እነዚህ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ከቤተክርስቲያን ባሻገር ለአለምም ትልቅ ሃብት ናቸው፣ እግዚአብሔር እነዚህ የፍቅር አገልጋይ የቤተክርስቲያንን ሃብት ልጆች አብዝቶ አብዝቶ ይባርካቸው ይቀድሳቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.