2015-05-06 16:01:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ወጣት ትውልድ ለሰላም ባህል ማነጽ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ከ 11 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ወጣቶችና ታዳጊ ወጣቶች ጋር በመገናኘት ከወጣቶቹ የሚቀርቡትን የተለያዩ ጥያቂዎች አንድ በአንድ በማዳመጥ መልስ ያካተተ ምዕዳን እንደሚለግሱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ ወጣት ትውልድ ለሰላም ባህል በማነጽ ካለንበት የተሻሻለ መጻኢ ለመገንባት በሕዝቦች በባህሎች መካከል መቀራረብ የሚያነቃቃ ሰላም የተረጋገጠበት ዓለም ህልም እንዳልሆነ በጽናት ቅዱስ አባታችን የሚያበክሩበት ዕለት እንደሚሆን ስለ ሚካሄደው ግኑኝነት በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የሥነ ልቦና ሊቅ ማሪያ ሪታ ፓሪሲ ሲገልጡ፣ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ከወጣት ጋር መወያየት ወጣቱ የሚያቀርበው ጥያቄ መሠረት በማድረግ ምዕዳን ለመለገስ የሚሹ እንጂ ቀድሞ በጽሑፍ የተዘጋጀ ምዕዳን ማቅረብ ብዙዉን ጊዜ የማይሹ ናቸው፣ ይኽ ደግሞ ለወጣት ትውልድ ንግግር ከማሰማት ይልቅ ወጣቱ ከሚያቀርበው ጥያቄ በመንደርደር ምክርና አስተምሆር መለገስ ያለው አስፈላጊነት የሚመሰክር ስልት ነው ብለዋል።

የሰላምና የውይይት ባህል ያለው አስፈላጊነት ቅዱስ አባታችን በመደጋግ የሚሰጡት አስተምህሮ በወጣቱ ትውልድ ዘንድ እንዲሰርጽ ማድረግ ወጣቱ ትውልድ ለሰላም ባህል በማነጽ በቤተሰብ በቁምስናዎች በትምህርት ቤቶች በተለያዩ ማኅበራዊነት በሚኖርባቸው ክልሎች ዘንድ የሰላም ባህል ማስፋፋት እንደሚሆንና እያንዳንዱ ወጣት ለሰላም ባህል ማነጽ መላ ኅብረተሰብ ለሰላም ባህል ማነጽ ማለት ነው። ግኑኝነትና ሰላም በእያንዳንዱ ልብ የሚጀመር ቢሆንም ቅሉ በልብ ተዘግቶ የሚቀር አይደለም ሰላም የሚኖር ሰላም ያስተላልፋል፣ ሰላም አለኝ ብሎ ሰላሙን የማያካፍል በሰላም መኖሩ ያጠራጥራል፣ የአንዱ ሰላም የሁለት የሦስት እየሆነ የማኅበርሰብ የአገር ሰላም ይሆና፣ ብለው የሚካሄደው ግኑኝነት ሰላም ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት አቢይ ድጋፍ መሆኑም አያጠራጥርም ሱሉ የሰጡት ያካሄድት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.