2015-05-01 14:09:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ እምነት የሐጢአትና የጸጋ ታሪክ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዘወትር ነግህ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል በላቲን ሥርዓት በዕለቱ ከግብረ ሐዋርያት ምዕ. 13፣ 13-25 እንዲሁም ከወንጌል ዮሐንስ ምዕ. 13፣ 16-20 የተወሰደው ምንባብ ተንተርሰው እምነት የሐጢአትና የጸጋ፣ የመገልገልና የማገልገል ታሪክ ነው በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጠጠረ ስብከት መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ታሪክና አገልግሎት፦ ቅዱስ አባታችን በለገሱት ስብከት በእነዚህ ሁለት የክርስቲያን የማንነት መለያ ላይ በማተኮር ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ ጴጥሮስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀደምት ደቀ መዛሙርት በጠቅላላ ታሪክ አልቦ የሆነ ኢየሱስ አልነበረ የሰበኩት፣ እነርሱ በሕዝብ ታሪክ ይኽም እግዚአብሔር በዘመናት ወደ የብስለት ወደ የሙላት ጊዜ  እንዲጓዝ በማድረግ አብሮት በተጓዘው በሕዝበ እግዚአብሔር ታሪክ ውስጥ ኢየሱስን አበሰሩ። እግዚአብሔር ወደ ሕዝብ ታሪክ ይገባል አብሮ ከሕዝቡ ጋር ይጓዛል። ክርስቲያን (እርሱነቱ) የገዛ እራሱ ንብረት አይደለም፣ በአንድ በሚጓዝ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የገባ ነው። ስለዚህ ክርስቲያን እራስ ወዳድነት ለማሰብና ለመገመት የማይችል ነው። ክርስቲያን በሙከራ ጠረጴዛ የሚኖር መንፈሳዊነት የሚከተል አይደለም፣ የአንድ ሕዝብ ወገን በአንድ ሕዝብ ታሪክ የገባ፣ ጌታ ዳግም እስከ ሚመጣበት ጊዜና ሰዓት በታሪክ የሚጓዝ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ገለጠ።

የጸጋና የሐጢአት ታሪክ

እምነት የጸጋ እንዲሁም የሐጢአት ታሪክ ነው። ቅዱስ አባታችን ጳውሎስ ንጉሥ ዳዊት እንደ አብነት ጠቅሰው፦ ስንት ሐጢአት፣ ስንት ወንጀለ ተፈጽመዋል። ቅዱሳን ከመሆናቸው በፊት አበይት ኃጢአተኞች ናቸው ነበሩ፣ ስለዚህ ታሪካችን ኃጢአተኛነትንና ቅዱስናን የሚያቅፍ ነው፣ የግሌ የሕይወት ታሪክ፣ ኃጢአተኛነቴም ያካተተ ነው። የግሌ ኃጢአትና የጌታ ጸጋ በእኔ ውስጥ ነው። በእያንዳንዳችን ውስጥ ነው። ጌታ በኃጢአተኛነት ጉዞአችን ለብቻችን ሳይተወን በምኅረቱ አብሮን በመጓዝ በጸጋው ይሸኘናል፣ ስለዚህ አለ ታሪክ የክርስትና ታሪክ ሊኖር አይችልም።

መገልገል ሳይሆን ማገልገል

ሁለተኛው የክርስትና መለያ አገልግሎት ነው። ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ እኛም ይኸንንን የአገልግሎት ተግባር እርስ በእርሳችን እንፈጽመው ዘንድ ነግሮናል። አዎ እኛ ራስ ወዳዶች ለእኔ ባዮች ነን፣ ይኽ ደግሞ ኃጢአት ነው፣ ከእራስ ወዳድነት ገዛ እራሳችንን ነጻ ማውጣት ይገባናል፣ የጌታን ምኅረት እንለምን፣ ጌታ ይለውጠን ዘንድ እንለምን፣ ለማገልገል ነው የተጠራነው፣ ክርስትያን መሆን ውጫዊ ሳይሆን ጭንብል ማጥለቅ ማለት ሳይሆን ኢየሱስ ያደረገው ማድረግ ማለት ነው። ኢየሱስ ያደረገውም ማገልገልን ነው። ለማገልገል ሳይሆን ላገለግል የሚል ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ ቅዱስ አባታችን እኔ ምንድር ነው የማድረገው፣ ሌሎች እንዲያገለግሉኝ ሌሎች ለገዛ እራሴ አገልግሎት የማውል ነኝ? ቁምስና ቤተሰብ ጓደኞቼ ለገዛ እራሴ ጥቅም እምገለገልባቸው ናቸው ወይንም ለማገልገል ፈጣን ነኝ? የሚል ጥያቄ አማካኝነት የለገሱት ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.