2015-05-01 14:12:00

የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን ድርገት ሰነድ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተቀባይነት አገኘ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መዋቅሮች ኅዳሴ እንዲረጋገጥ በዚሁ ሂደት ያቋቋሙት የብፁዓን ካርዲናሎች ምክር ቤት ሥር የአገረ ቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ኅዳሴ የሚከታተል በሳቸው የተመረጡት አባላት ያቀፈው የመገናኛ ብዙኃን ኮሚቴ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ያቀረበው የኅዳሴ ሰነድ እንደተቀበሉት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የዚህ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የቫቲካን የቴለቪዥን ጣቢያ ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ አቨኒረ ለተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ፓውሎ ኑሲነር፣ የአገረ ቫቲካን መስተዳዳር የቴሌ ግኑኝነት ጉዳይ ሥር የሚመራው የድረ ገጽ አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ሉቾ አድሪያን ሩይዝ፣ የቺቪልታ ካቶሊካ (የካቶሊካዊ ሥልጣኔ) መጽሔት ዋና አስተዳዳሪ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮና የማኅበራዊ ግኑኝነት ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፖል ቲገ የሚያቅፍ መሆኑ በማስታወስ፣ ለቅዱስ አባታችን የቀረበው የኮሚቴው ሰነድ ዙሪያ ቀደም በማድረግ የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 13 እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2015 ዓ.ም.  ስብሰባ ማካሄዱ አስታውቀዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.