2015-04-29 18:59:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! እግዚአብሔር በመጀመርያ በፈጠረው የሰው ልጅ ሴትና ወንድ ጥንድ ያደረግነው አስተንትኖ በኦሪት ዘፍጥረት የሚገኙትን ሁለት ትረካዎች ከተመለክተን በኋላ አሁን በቀጥታ ስለ ኢየሱስ እንመለከታለን፣

ወንጌላዊው ዮውሓንስ በወንጌሉ መጀመርያ ላይ በቃና ዘገሊላ ስለተካሄደው ሠርግና እመቤታችን ድንግል ማርያምና ኢየሱስ ከመጀመርያዎቹ ተከታዮቹ ጋር እዛ እንደነበሩ ይገልጣል (ዮሓ 2፡1-11)፣ ኢየሱስ በበዓሉ ብቻ በመገኘት ሳይሆን የበዓሉን ፍሥሓ በመጀመርያው የወይን ተአምር ከታላቅ ሓፍረት ያድናቸዋል፣ ክብሩን ከገለጠባቸው ተአምሮች የመጀመርያው የሆነንውን በሠርግ ድግስ ይፈጽመዋል፤ ይህም ለአዲስ ሕይወት ለምትጀምረው ቤተሰብ ታላቅ ዝንባሌ የታየበትና በእመቤታችን ድንግል ማርያም አሳቢነትና አማላጅነት የተፈጸመ ተአምር ነው፣ ይህ ታሪክ የሚያሳስበን ነገር ካለ በኦሪት ዘፍጥረት የተጻፈውን ታሪክ ማለት እግዚአብሔር የፍጥረት ሥራን ከፈጸመ በኋላ ታላቁን የሰው ልጅ ፍጥረት ማለትም ወንድና ሴት አድርጎ መፍጠሩን ነው፣ እዚህም ኢየሱስ ተአምራቶቹን በዚሁ የእግዚአብሔር ታላቅ ሥራ በአንድ ወንድ ልጅና ሴት ልጅ የሠርግ በዓል ይፈጽመዋል፣ እንዲህ በማድረጉም ኢየሱስ የኅብረተሰብ ታላቅ ሥራ ቤተሰብ መሆኑ ሲገልጽ ይህም አንድ ወንድ ልጅና ሴት ልጅ ሲፋቀሩ ማለት ነው፤ እውነትም ታላቅ ሥራ፤

ከቃና ዘገሊላ ሠርግ ተአምር በኋላ ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል ነገር ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተግባር ለዘለዓለም የሚኖር መልእክት ትቶልናል፣ ዛሬ ቃል ኪዳን ዘወትር ሲታደስ የሚኖር ባልና ሚስት በሕይወታቸው እስካሉ ድረስ በተለያዩ የሕይወት ዘመናቸው ኑሮ የሚታደስ ነው ለማለት ቀላል ነገር አይደለም፣ እንደምንመለከተው ከሆነ ከዕለት ወደ ዕለት በቃል ኪዳን የሚጋቡ ሰዎች ቍጥር እየቀነሰ ነው፤ ይህ እውነት ነው፤ ወጣቶች ሊጋቡ አይፈልጉም፣ በሌላ በኩል ደግሞ በብዙ አገሮች የቃል ኪዳን መበታተንና መፋታት እየታየ ሲሆን አዲስ የሚወለዱ ሕጻናት ቍጥርም በእጅጉ እየቀነሰ ነው፣ እንደ ጥንድ ይሁን እንደቤተሰብ አብሮ መኖር እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ በልዩ ፍጥነትና ብዛት መፋታትን ያስከትላል የዚሁ ሰለባ የሚሆኑ ደግሞ በቅድምያ ከአብራካቸው የተገኙ ልጆች ናቸው፣ እዚህ ላይ ማስታወስ ያለብን እውነትም የዚሁ መለያየት የመጀመርያ ሰለባ በመሆን የሚሰቃዩ የቤተሰቡ አበባና ፍሬ የሆኑ ልጆቻቸው ናቸው፣ ሕጻናቱም ከዚህ የሚማሩት ቃል ኪዳን ለጊዜው መሆኑና መለያየት እንደሚቻል ነው፣ እንዲህ በመሆኑም የዘመናችን ልጆች ቃል ኪዳን የማይፈርስና ቤተሰብ ማቆም እስከሞት መሆኑን ትተውታል፣ እዚህ ላይ ሁላችን ማስተንተን ያለብን ወጣቶች ትዳር ለማቆም የማይጥሩትና እጅግ የሚዘገዩት ዋና ምክንያት ይህ መሆኑን ነው፣ በዘመናችን የጊዝያዊነት ባህል ሰርጸዋል፤ ሁሉም ጊዝያዊ ነው፤ ለጊዜው እንጂ ቅዋሚ የሚባል ነገር የለም እስከ ማለት ደርሰዋል፣

በዛሬው ጊዜ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ የሚገኘው ወጣቶቻችን ትዳር ለማቆም ቤተሰብ ለመምሥረት አለመፈለጋቸው ነው፣ ወጣቶች ለምን አይዳሩም? ለምንስ ከኃላፊነት ለመሸሽ በቃል ኪዳን ትዳር ከመመስረት ይልቅ ለጊዜው አብሮ መኖርን ይመርጣሉ? ከተጠመቁ ክርስትያኖችም ሳይቀር በቃል ኪዳንና በትዳር ያላቸው እምነት እየቀነሰ የሚገኘው ለምንድር ነው? ይህንን ነገር በመላ ጐደል ልንረዳው ለምንድር ነው ወጣቶች በቤተሰብ የማይተማመኑ ብለን በማስተንተን ትክክለኛውን መንገድ እናፈላልግ፣

ምንም እንኳ አሳሳቢ ቢሆንም የዚህ ጉዳይ ችግሮች የምጣኔ ሃብት ብቻ አይደለም፣ ስለዚህ ጉዳይ ከሚተነትኑ አብዘኛዎቹ በመጨረሻዎች የዘመናችን ዓመታት የሴት ልጅ ነጻነትን በሚመለከት ብዙ ስለተጋነነ ነው የሚሉም አሉ፣ ነገር ግን ይህ አስተያየትም ትክክል አይደለም፣ ይህ ምናልባት ስድብ ይመስላል! ግን እንደዛ አይደለም! ሴት ልጅን ለመቆጣጠርና ለመግዛት የሚንቀሳቀስ ተባዕታዊ እንቅስቃሴ ነው፣ አዳም የፈጸመውን መጥፎ ስሕተት ማለትም እግዚአብሔር ለምን ከተከለከለ ፍሬ በላህ ሲባል የሰጠችኝ እርሷ ናት ያለውን እንደግማለን፣ ጥፋቱ የሴትየዋ ነው! ምስኪንዋ ሴት! ሴት ልጆችን ልንከላከልላቸው ይገባናል፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ሁሉም ወንዶችና ሴቶች የጓደኝነት መተማመን ያስፈልጋቸዋል፤ ጽኑ ቃል ኪዳንና ደስተኛ ቤተሰብ ያስፈልጋቸዋል! ወጣቶች ከሚፈልግዋቸውና ከሚመኝዋቸው ዕሴቶች ከፍተኛውን ቦታ የያዘ ቤተሰብ መምሥረት ነው ነገር ግን እንዳይሳሳቱ በመፍራት አብዛኛዎች ስለትዳር ሊያስቡም አይፈልጉም፣ የተጠመቁ ክርስትያኖችም ሳይቀር ያ ወደር የሌለው እስከ ሞት አብሮ ለመኖር ጸጋ በሚሰጥና በማይደገም  ቃል ኪዳን ስለሚቆመው ትዳርና ስለሚሰጠው ክርስትያናዊ ምስክርነት ሊያስቡም አይፈልጉም፣  ያ የምሥጢረ ተክሊል ጸጋ በመስጠት አንድ የሚያደርግና ቤተሰብ የሚያቆም የክርስቶስን ቃል ላለመቀበል ታላቁ ምክንያት ምናልባት ይህ ጥርጣሬና የመሳሳት ፍራቻ ሊሆን ይችላል፣

የክርስትና የቃል ኪዳን ቡራኬ ቀስቃሽ ምስክርነት የክርስትያን ሙሽሮች መልካም ሕይወትና የቤተሰባቸው ደስተኛ ኑሮ ነው፣ ከዚህ የሚበልጥ የምሥጢረ ተክሊል መልካምነት ሊገልጥልን የሚችል ሌላ ነገር የለም፣ በእግዚአብሔር የተባረከ የቃል ኪዳን ትዳር ያ እግዚአብሔር ከፍጥረት ጀምሮ አዳምናን ሔዋንን በአንድነት እንዲኖሩ የሰጣቸው ቡራኬን ይጠብቃል፣ እንዲህ በመሆኑም ለመላው የቃል ኪዳን ሕይወት ኑሮ የሰላም የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ነው፣ ለምሳሌ በክርስትና መጀመርያዎቹ ዘመናት ያ በብሉይ ኪዳን ማንኛው ወንድ በሆነ ምክንያት ሴቲቱን በአሳፋሪና ዝቅ በሚያደርግ ሁኔታ ሊፈታት እንደሚችል የሚፈቅደውን ሕግ ሽሮታል፣ የቤተሰብ ወንጌል የሆነው ምሥጢረ ቃል ኪዳንን የሚያበስረው ይህ ወንጌል ይህንን የመፍታት ባህል አሸንፎታል፣

የባለትዳሮች መሠረታዊ እኩልነትን የሚገልጠው ይህ የወንጌል ቃል ዘር ዛሬ አዳዲስ ፍሬዎች መፍራት አለበት፣ በዚሁ ሳቢ የሆነ የምስክርነት ጐዳና አንዱ ሌላውን የሚያከብርበት እና የሟሟላት ጐዳና ማኅበረሰባዊ የትዳር መብት ምስክርነት እጅግ አመርቂና ተፈላጊ ሊያደርገው ይችላል፣

ስለዚህ ክርስትያኖች እንደመሆናችን መጠን ይህንን አመለካከት ማጠንከር አለብን፣ ለምሳሌ ሴትና ወንድ ለሚሠሩት እኩል ሥራ እኩል ክፍያ እንዲኖረው መደገፍ አለብን፤ ለምንድር ነው ሴቶች ከወንዶች ዝቅ ያለ ክፍያ እንዲኖራቸው እንደ ሕግ የምንቀበለው? ይህ መሆን የለበትም፤ እኩል መብት እንዲኖራቸው ይሁን፣ እኩልነትን አለመቀበል እንቅፋት ነው፣ ከዚህ ሌላ ደግሞ የሴት ልጆች እናትነትና የወንዶች አባትነትን እንደ ታላቅ ሃብትና ስጦታ ልንገነዘበው፤ ከሁሉ አስቀድመን ደግሞ ይህ ለሕጻናቱ መሆኑን ማወቅ አለብን፣ ይህንን መስመር ሳንተው በብዙ ችግሮች ለሚሰደዱና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ማስተናገድ በተለይ በድህነት በችግር እንዲሁም በቤተሰብ ዓመጽ ለተጐድ ማስተናገድ አለብን፣

ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ኢየሱስን በሠጎቻችን በዓል እንደክብር እንግዳ ለመጥራት መፍራት የለብንም፣ በቤተሰባችን መሃከልም ከእኛ ጋር አብሮ እንዲጓዝና ቤተሰባችንን እንዲጠብቅልን ለመጥራቱ አንፍራ፣ እናቱ ማርያምን እንጥራት፣ ክርስትያኖች በጌታ ስም ትዳር ሲያደርጉ የእግዚአብሔር ተጨባጭና ቻይ ፍቅር ይለውጣቸዋል፣ ክርስትያኖች ትዳር የሚያቆሙት ለገዛራሳቸው ብቻ አይደለም፤ በጌታ ስም ትዳር ሲመሰርቱ ለመላው ማኅበርሰብ ለመላው ዓለም ነው መልካም ሥራ የሚፈጽሙት፣

ስለዚሁ ደስት የሚያሰኝ የክርስትያን ትዳር ጥሪ በሚቀጥለው ትምህርተ ክርስቶስ እናገራለሁ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.