2015-04-27 19:54:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ; “ለሚጠይቃችሁ ሁሉ ለማንም ምሥጢረ ጥምቀት እንዳትነፍጉ፡


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለአሥራ ዘጠኝ ዲያቆናት መዓርገ ክህነት ሰጥተዋል፣ በሥርዓቱ ባቀረቡት ስብከትም “ለሚጠይቃችሁ ሁሉ ለማንም ምሥጢረ ጥምቀት እንዳትነፍጉ፡ ስብከታቸውም የሚሰለች እንዳይሆን አደራ፤ ርኅሩኆችና መሓሪዎች ሁኑ፣ ለእግዚአብሔር እንድታስደስቱ እንጂ ለገዛ ራሳችሁ ደስ እንዲላችሁ አትሥሩ” ሲሉ አሳስበዋል፣

በላቲኑ ሥርዓት ትናንትና እሁድ ስለጥሪ ጸሎት የሚቀርብበት ዓለም አቀፍ ቀን ሲሆን ይህ ዕለት ከታወጀ ትናንትና ለ52ኛ ጊዜው ተዘክሮዋለ፣ በዚህ ዕለት አሥራ ዘጠኝ ድያቆናት ክህነት ሲቀበሉም ታላቅ ደስታና እርካታ የሰጠና የታየበት አጋጣሚ ነበር፣

መዓርገ ክህነት ከተቀበሉት ዲያቆናት 13 በሮም ከሚገኘው ከማርያም ቅዱስ ልብ ዘርአ ክህነት የተመለመሉ ሲሆን  የተቀሩት 6ቱ ደግሞ የፍራንቼስካውያን ማሕበር ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የምሥራቅ ሲርዮ ማላብሬዚው ስርዓት የምትከተል ከህንድ ሃገረ ስብከት ታማራሳየርይ ናቸው። ከእነዚህ አዳዲስ ካህናት አብዛኛዎቹ የር.ሊ.ጳ ሃገረ ስብከት በሆንችው በሮም ሃገረ ስብከት እንደሚያገለግሉ ተገልጻል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል ክህነት ለተቀበሉት የክርስቶስን ተልእኮ በመግለጥ የክርስቶስን አብነት በመከተል እንደ ኢየሱስ ዘላለማዊ ካህን ወንጌሉን ለአሕዛብ መመስከርና በተለይም በአምልኮ መሪ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ብቻ ካህን እንደሆነ በማስተማር እንዲሁም በኢየሱስ አማካኝነት የተቀረው የእግዚብሔር ሕዝብ ካህን ተብሎ መጠራቱን በመግለጥ ግን ኢየሱስ ከሁሉም ደቀ መዛምርቱ አንዳንዶቹን ብቻ በመምረጥ በቤተክስርስቲያኑ መሪዎች በማድረግ ሌሎቹን እንዲያገለግሉ መምረጡና ይህም በክህነትና በእረኝነት የተልዕኮ አገልግሎት በማሰማራት እንዲያገለግሉ መሆኑን ቅዱስነታቸው አስተምረዋል።

በማያያዝም የእግዚብሔርን ቃል ሲያስተምሩና ሲሰብኩ ቀጥታ ወደ ልብ የሚደርስ ቃላትን ማስተማር እንጂ ረጅምና የሚሰለች ስብከት እንዳይሆን አደራ ብለዋል። ስብከት በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል አስተንትኖ በማድረግ ለአሕዛብ ከውስጥ ከልብ በሚመነጩትን ቃላት በደስታ አምነን የተቀበልነውን በደስታ ማስተላለፍና ማስተማር ለሌሎችም ለሕይወታቸው ደስታና ምርኩዝ መሆን እንደሚችል አሳስበዋል። ካህናት የሕይወታችሁ ጠረን ለሌሎች ምስክርነት መሆኑን መገንዘብና መልካም ከሆነ ሌሎቹንም መጠገንና ማሳደግ እንደሚችል አስተምረዋል። መልካም ቃላት ቢደረደሩ የሕይወት አብነትና ምስክርነት ካልታየበት ባዶና ወደ ልብ የማይደርሱና ልብን የማይነኩ እንዳውም ጭራሽ የሚያሳምሙና የሚያርቁ ቃላቶች ይሆናሉ። በመጨረሻም ጥምቀትና ምሕረትን ለሚጠይቅ ሁሉ መከልከል እንደሌለባቸው አደራ ሲሉ በሚስጥረ ጥምቀት ቤተክስርቲያን አዲስ ልጆችዋን እንደምታገኝና በሚስጥረ ንስሐም ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት የሓጢዓቱን ስርየት የሚያገኝበት በር መሆኑን ገልጠዋል።  

እኔም በክርስቶስ ስምና በሙሽራይቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን ስም በተደጋጋሚ የምለምናችሁ ምህረትን ለማድረግ አትሰልቹ በመንበረ ኑዛዜ ስር ለመፍረድ ሳይሆን ምህረትን ለመስጠት መቀመጣችሁን አትዘንጉ!! ለኛ ምህረትን በማድረግ የማይሰለቸውን አባት ተመልከቱ፤ የእርሱንም አርዓያ ተከተሉ ብለዋል፣  ከዚህም ባሻገር ሥርዓተ ቅዳሴና አምልኮ ሲፈጸም በዘልማድና በመቸኮል እንዳይሆን በማሳሰብ  ሥርዓተ ቅዳሴና አምልኮ ሲፈጸም የክርስቶስን ምስጥረ ሕማማት ሞትና ትንሳኤን በማስተንተንና በማሰላሰል መሆን እንዳለበት፤ በዚህም የክርስቶስ መሥዋዕት ለምዕመናን ወደ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ እንደሚያሻግር አስተምረዋል። ቅዱስነታቸው በማጠቃለል ካህን መልካሙን የክርስቶስ ምስራች ሳይታክት ለሌሎች መመስከርና ማገልገል መስራትና  መጸለይ ለክርስቶስ ፍቅርና ክርስቶስን ለማስደሰት መስራት እንዳለበትም አደራ ብለዋል። ምክንያቱም ካህናት ለበሽተኞች ቅብዓ ቅዱስን በመቅባት እንዲሁም ለማጽናናት በሚሄዱበት በተለያዩ ቦታዎች  የምስጋናና የጸሎት ሰዓታት ግዜያቸውን  የእግዚአብሔርንና የአለምን ሕዝብ በሙሉ የጸሎት ድምፅና ልመና የሚያቀርቡና የሚያስተላልፉ ናቸው። ስለዚህ ካህናት ምእመናንን እንደ አንድ ቤተሰብ በማሰባሰብ በቤተክርስቲያን በማሳተፍ ወደ እግዚአብሔር አባት በክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ማድረስ መሆኑን በማስተማር ስለዚህ የመልካሙን በግ እረኛ አንዲቷን በግ የጠፋችዋን ፍለጋ የሄደውን አብነት በመከተል መኖር እንጂ የራሳቸውን ምኞች ማየትና መጠበቅ አንደሌለባቸውም አስገንዝበዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.