2015-04-24 16:09:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጥምቀት ቅዱስ ስም በዓል


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳከበረችና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የጥምቀት ስማቸው ኾርገ በመሆኑም በዚህ ዕለት የቅዱስ ስማቸው በዓል መከበሩንም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የቅዱስ አባታችን የጥምቀት ስም በዓል ምክንያት የጳጳሳዊ የአበይት የሊጡርጊያ በዓላት መምኅር ብፁዕ አቡነ ጉለርሞ ካርኸር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ያንን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳስብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የወቅቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብየ እንድገስልጣቸው ያበቃኛል የክፋት መንፈስ የሚቃወሙ በክርስቲያናዊ መንፈስና እምነት ተሞልተው የክፋት መንፈስ በመገሰጽ የክርስቶስ ፍቅር በሁሉ ሰው ልብ ዘንድ እንዲነግሥ የሚመክሩ የሚጸልዩ በክርስቶስ ስም መልካም የሚዘሩ ናቸው። ገና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ የሚኖሩት መንፈሳዊነት እንደነበርም አስታውሰው፣ ይኽ ጥልቅ እምነት አሁንም እየኖሩትና በኵላዊ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው እያስተጋቡት ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አቡን ሊቀ ጳጳስ ተብለው ከመሰየማቸው በፊትና ከዛም የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተብለው በእግዚአብሔር ፈቃድ ከመሾማቸው በፊት የኢየሱሳውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር አባል ናቸው በመሆኑን ገዳማዊ ካህን ናቸው። ስለዚህ መጠሪያቸው አባ የሚል ነው። ይኸንን የአባትነት ጥሪታቸው በአሁኑ ወቅት በኩላዊነት ደረጃ እየኖሩት ነው ብለው፣ የመንፈስ ነጻነት የተካኑ፣ ውስጣዊ ኃይል የተሞሉ የመንፈስ ነጻነት የሚኖሩ ናቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ በአደራ የሰጣት ተልእኮ በእሳቸው አማካኝነት በመላ ዓለም እንዲስተጋባ እግዚአብሔር የቀባቸው ናቸው። ትህትናቸው የሚኖሩት ክርስቲያናዊ ወንጌላዊ ደስታ ለሁሉ ቅርብ በተለይ ደግሞ ለተናቁት ለተረሱት በከፋ ድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚኖሩት ለውጫዊ የከተሞቻችንና የህልውናችን ክፍሎች ቅርብ በመሆን የሚኖሩት በመህናቸውም ቤተ ክርስቲያን ለወንጌላዊ ኃሴት የተጠራች መሆንዋ እግዚአብሔር በሳቸው አማካኝነት እየገለጠልን ነው።

የጥምቀት ስማቸው በሚከበርበት ዕለት የእግዚአብሔር ኃይል እናስተነትናለን ብለው፣ ቅዱስ አባታችን ጸላይ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው። በእግዚአብሔር ቃል ፊት በቅዱስ ቁርባን ፊት አስተንታኝ ጸላይ፣ ይኽ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት፣ ከእግዚአብሔር ጋር በሕዝበ እግዚአብሔር ፊት ከእግዚአብሔር ጋር በሕዝበ እግዚአብሔር ፊት፣ መሆን በቃልና በሕይወት የሚያውቁ አባት ናቸው። በሳቸው አማካኝነት ብርቱ የእግዚአብሔር ህላዌ እየተስተዋለና እይተስተጋባም ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.