2015-04-20 16:39:00

ዝክረ አሥረኛው ዓመት የቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሲመት


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ራትዚንገር በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ብላ የሰየመችበት ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ ዝርከ 10ኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለትከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ቅዱስነትቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮ ተከታይ ሆነው እንደተመረጡ ገዛ እራሳቸውን ትሁት የእግዚአብሔር ማሳ አገልጋይ በማለት ከሕብዘ እግዚአብሔር ጋር በማስተዋወቅ የተከተሉት የአገልጋይነት ተልእኮ ፍሬው አሁን እየታየ ነው ብለዋል።

የሳቸው መመረጥ ጸረ እግዚአብሔር ብሎም እግዚአብሔርን ቸል የሚል ባህል፣ እግዚአብሔር ይኑር አይኑር ግድ የማይል በኤውሮጳና በበለጸገው ዓለም ለተስፋፋው ባህል ለመዋጋት የሚበጅ መሪ ሥልጣናዊ ትምህርት በጥልቀት የተንጸባረቀበት ብሎም በእምነትና በምርምር መካከል ያለው ግኑኝነት በጥልቀት የሚያንጽ ሥልጣናዊ ትምህርት የተስተጋባበት በደረሱዋቸው ዓዋዲ መልእክቶቻቸው አማካኝነትም የፍቅር ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ ፍልስፍናዊና ሐዋርያዊ ግብረ ኖላዊ ትርጉም በማስተላልፍ በቤተ ክርስቲያን ዘረፈ ብዙ አገልግሎት እንዲኖር እድርገዋል፣ የሥልጣናዊ ትምህርቶቻቸው ውጤት በቤተ ክርስትያንና በኅብረተሰብ በማኅበረ ክርስቲያን ዘንድ አሁን እየታየው ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.