2015-04-20 16:29:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሕንጸት ወጣት ትውልድ ለሚነጥለው ባህል ፈውስ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ ልብ የካቶሊክ መንበረ ጥበብ ወጣት፣ የከተሞቻችንና የህልውና ጥጋ ጥግ ማእከላዊ ማድረግ በሚል ርእሥ ሥር ለሚያካሂደው 91ኛው ዓመታዊ ዓውደ ጥናት ምክንያት በማድረግ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ፊርማ የተኖረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ይኽ የቅዱስ ልብ ካቶሊካዊ መንበረ ጥበብ ለወጣት ትውልድ ቅርብ መሆኑ ለሚለው የምሥረታው ዓላማ ታማኝ በመሆን በሕንጸት አማካኝነት ያንን ወጣት ትውልድ የሚነጥለውን ለተለያየ አደጋ ለሚያጋልጠውን ባህል ለመዋጋት የሚያበቃ የሚሰጠው ፈዋሽ ባህል እንዲያበረታታ በማሳሰብ፣ ነጣይ ባህል ለመዋጋት ለሚያግዘው የሕንጸት ባህል ሰብአዊና ኤኮኖሚያዊ አቅሙ ካለ መንም ቁጠባ እንዲያውል አሳስበው፣ ለሕንጸት የሚያፈሰው መላ ኃይሉ ጸረ ነጣይ ባህልና ለአደጋ ከሚያጋልጥ ባህል ለሚፈውስ ሕንጸት የሚውል መሆን እንዳለበት ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ የመንበረ ጥበቡ ዋነኛ ዓላማ መሆኑ የመንበረ ጥበብ ታሪክ ጠቅሰው እንዳሰመሩበት የቅድስት ምንብር መግለጫ አስታወቀ።

ወጣት ትውልድ የማኅበራዊ ሕይወት ዋና ተወናያን የመሆን ጥሪው ዳግም እንዲቀዳጅ የሚያንጽ መሆን እንደሚጠበቅበት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ገልጠው፣ የቤተ ክርስቲያን ጥረትና ወጣት ትውልድ ለተገባ ዓላማ ማነጽ በሚለው ተግባር የተጠመደ መሆኑ ቅዱስ ልብ ካቶሊካዊ መንበረ ጥበብ ምስክር ነው ብለው፣ ወጣት ትውልድ ከዚህ መንበረ ጥበብ በሥነ ምርምር ብቻ ሳይሆን በግብረ ገብና በባህል ጭምር ታንጾ ለአገርና ለሕዝብ ጥቅም ለማኅበራዊ ጥቅም መረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ ተቀዳሚ ሚና እንዲኖረው የሚያበቃ መሆኑም በማስታወስ ሕንጸት የመለያየት የመነጣጠል ሌላውን የመዘንጋት ቸል የማለት ባህል ለመዋጋት የሚያበቃ ራእይ የተካነ መሆን አለበተ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ገለጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.